ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮም ከተማ በሚገኘው የሮም ከተማ ሕዝቦች ጠባቂ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስል አተገብ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮም ከተማ በሚገኘው የሮም ከተማ ሕዝቦች ጠባቂ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስል አተገብ።  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና መላው ምዕመን በግንቦት 22/2012 ዓ.ም የመቁጸሪያ ጸሎት ይደረጋል!

በዓለማቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ አሁን የምንገኝበት የግንቦት ወር “የማርያም ወር” ተብሎ እደሚጠራ ይታወቃል። ይህ የግንቦት ወር በወር ደረጃ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ “የማርያም ወር” በመባል የሚታወቅ ወር ሲሆን የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማኅበረስብ ክፍሎች ዘንድ  ነገ ቅዳሜ ግንቦት 30/2020 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30 ላይ ቫቲካንን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የተሰየሙ  ቤተመቅደሶችን ጨምሮ በመላው ዓለም በሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመና ዘንድ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት የመቁጠሪያ ጸሎት እንደ ሚደረግ ተገልጿል። በዚህ የመቁጠሪያ ጽሎት ላይ በአሁኑ ወቅት ዓለማችንን እያሸበረ እና በፍጥነት እየተቀጣጠለ የሚገኙውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ይወገድ ዘንድ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅነት የምንማጸንበት የጽሎት ቀን እንዲሆን በቫቲካን መወሰኑ ይታወሳል።

የቫቲካን ዜና

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የኮርና ቫይረስ ወረርሽኝ በተከሰተበት በአሁኑ ወቅት መላው የሰው ልጆች መለኮታዊ እርዳታ እንዲያገኝ አንድ ላይ እንዲጸልዩ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን የመቁጠሪያ ጸሎት ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ከዓለማቀፋዊቷ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ጋር በጋራ በመሆን ነገ ቅዳሜ ግንቦት 22/2012 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12፡30 በቫቲካን የአትክልት ስፍራ ቦታ ከሚገኘው በፈረንሳይ አገር መሚገኘው በሉርድ ማርያም አምሳል በተሰራው እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሐውልት ከሚገኝበት ፍርኩታ ወይም የተቦረቦረ ዋሻ አጠገብ የሚደርገው የመቁጸሪያ ጸሎት በመገናኛ ብዙሃን አውታሮች እንደ ሚተላለፍ ተገልጿል።

ይህ የጸሎት መረዓ ግብር የሚከናወነው “ሁሉም ከኢየሱስ እናት ከማርያም ጋር በአንድ ልብ ሆነው ያለ ማቋረጥ ተግተው ይጸልዩ ነበር” (የሐዋርያት ሥራ 1፡14) በሚል መሪ ቃል የሚከናወን ጸሎት ነው። ይህ የጸሎት መረዓ ግብር የተዘጋጀው ቅዱስ ወንጌልን በአዲስ መልክ የማስተዋወቅ ኃላፊነት በተሰጠው ጳጳሳዊ ምክር ቤት እንደ እንደ ሆነም ተገልጿል።

29 May 2020, 19:47