ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እውነተኛ የሆኑ ሰላም አስከባሪዎች ዘላቂ እርቅ እንዲፈጠር ያደርጋሉ” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዚያ 07/2012 ዓ.ም  በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ያደረጉት ሳምንታዊ አስተምህሮ በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መተላለፉ ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ላይ በተጠቀሰው እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራራው ላይ አድርጎት በነበረው ስብከት ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ የተራራው ላይ ስብከት ውስጥ በሰባተኛው ክፍል ላይ በተጠቀሰው “ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 5፡9) በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “እውነተኛ የሆኑ ሰላም አስከባሪዎች ዘላቂ የሆነ እርቅ እንዲፈጠር ያደርጋሉ” ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉትን አስተምህሮ እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የሚያተኩረው “ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፣ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና” (ማቴ 5፡9) በሚለው ኢየሱስ በተራራ ላይ ባደረገው ስብከት ውስጥ በሚገኘው ሰባተኛው ክፍል ላይ ነው።  ይህ አስተምህሮ በቅርብ ጊዜ ካከበርነው የፋሲካ በዓል በኋላ የተከሰተ በመሆኑ ደስ ያለኝ ሲሆን ምክንያቱም ቀደም ሲል ሐዋርያው ጳውሎስ ከጻፈው መልእክት ተወስዶ ሲነበብ እንደ ሰማነው (ኤፌሶን 2፡14) የክርስቶስ ሰላም የእርሱ ሞት እና የትንሳኤ ፍሬ በመሆኑ የተነሳ ነው። አንድ ሰው የእዚህ በተራራ ላይ የተደርገው ስብከት አንድ አካል የሆነውን “ሰላም” የሚለውን ቃል ትርጉም ይበልጥ መረዳት አለበት፣ ምክንያቱም ይህ በተሳሳተ መንገድ ልንረዳው ወይም አንዳንድ ጊዜ ሊተነተን ይችላል።

እኛ በሁለት የሰላም ሀሳቦች መካከል እራሳችንን ማስገባት አለብን - አንደኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሲሆን እዚያም የተትረፈረፈ ብልጽግናን፣ ማበብን፣ ደህንነትን የሚገልፅ ሲሆን በዕብራይስጥ ቋንቋ ሻሎም በመባል ይታወቃል። አንድ ሰው በዕብራይስጥ ቋንቋ ሌላውን ሻሎም በማለት ሰላምታ ሲያቅርብለት ውብ የሆነ፣ የተሟላ ፣ የበለጸገ ሕይወት ይመኛል ማለት ነው፣ በተጨማሪም ደግሞ በእውነት እና በፍትህ ላይ የተመሰረት፣ የሰላም ልዑል በሆነው በመሲህ አማካይነት የሚመጣውን ዓይነት ሰላም ያመለክታል (ኢሳያስ 9: 6፤ ሚክያስ 5፣4-5)።

ከዚያ “ሰላም” የሚለው ቃል ከውስጣዊ መረጋጋት ዓይነት ጋር በተገናኘ መልኩ እንድንረዳ የሚረዳን ሌላ ትርጉም አለ፣ የተረጋጋው ነኝ፣ ሰላም አለኝ የሚሉትን ቃላት የሚገልጽ ነው። ይህ ዘመናዊ ፣ ሥነ-ልቦናዊ እና የበለጠ ከስብዕና ጋር የተቆራኘ ጉዳይ ነው። ሰላም በተለምዶ ፀጥታ ፣ ስምምነት ፣ ውስጣዊ ሚዛን እንደሆነ ይታመናል ፡፡ ይህ ሁለተኛው “ሰላም” የሚለው ቃል ትርጉም ያልተሟላ እና ፍጹም የሆነ ሊሆን አይችልም ፣ ምክንያቱም በሕይወት ውስጥ እረፍት ማድረግ ለእድገት አስፈላጊ የሆነ ነገር ሊሆን ይችላል። እሱን ለማግኘት ወደ እርሱ እንሄድ ዘንድ ሊረዳን ብዙውን ጊዜ በውስጣችን የመቅበጥበት ስሜት የሚዘራው ጌታ ራሱ ነው። በዚህ ረገድ ይህ አስፈላጊ የእድገት ወቅት ነው ፣ ውስጣዊ መረጋጋት የሚገኘው ከትክክለኛ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ከተረጋጋ ህሊና ጋር የተዛመደ መሆኑን ያሳያል። ብዙ ጊዜ ጌታ “የተቃራኒዎሽ ምልክት” (ለብዙዎች መነሣትና መውደቅ ምክንያት እንዲሆን ሉቃስ 2፡34-35) መሆን አለበት፣ እውነተኛ ያልሆነ እምነታችንን በመነቅነቅ ወደ ድህንነት ሊያመጣን ይችላል ፡፡ በዚያ ቅጽበት ሰላም ያለ አይመስልም ፣ እሱ ራሱ ወደ ሚሰጠን ምድር ለመግባት እንድንችል በዚህ መንገድ ላይ ያስቀመጠን ጌታ ራሱ ነው።

በዚህን ጊዜ ጌታ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደምሰጣችሁ ሰላም ዓይነት አይደለም” (ዮሐንስ 2፡ 27) በምልበት ወቅት የሰው ልጅ ጌታ የምሰጠው ሰላም ከዓለም ሰላም የተለየ መሆኑን ለመረዳት መዘንጋት የለብንም። ኢየሱስ የምሰጠን ሰላም ለየት ያለ ሰላም ነው፣ ዓለም ከምሰጠን ሰላም የተለየ ነው።

እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ-ዓለም ሰላምን የምሰጠው እንዴት ነው? ስለ ጦርነት እና ግጭቶች ካሰብን ፣ ጦርነቶች በተለምዶ በሁለት መንገዶች ይጠናቀቃሉ፣ አንደኛው ወገን ስያሸንፍ ወይም የሰላም ስምምነቶችን በመፈጸም ሊሆን ይችላል የምጠናቀቀው።  እኛ ይህ ሁለተኛው መንገድ እንዲተገበር ለማድረግ የምንችለው ተስፋ በማድረግ እና በመጸለይ ብቻ ነው፣ ሆኖም  በታሪክ ሂደት ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች መካከል በታሪክ ሂደት ውስጥ በተከታታይ ማለቂያ የሌለው የሰላም ስምምነቶች ዓይነት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። በእኛ ጊዜ እንኳን “በሁኔታዎች” ውስጥ በብዙ ሁኔታዎች እና በተለያዩ መንገዶች ጦርነቶች ይካሄዳል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በኢኮኖሚያዊ ወይም የግል ጥቅም ፍላጎቶች ለማስጠበቅ ብቻ በማሰብ በተፈጠረው አለማቀፋዊ ትስስር (ግሎባላይዜሽን) ሁኔታ የአንዳንዶቹ “ሰላም” የምረጋገጠው ሌሎቹ “ጦርነት” ላይ ሲሆኑ ነው ከምለው አስተሳሰብ ጋር እንደምዛመድ ቢያንስ መጠርጠር አለብን። የእዚህ ዓይነቱ ሰላም የክርስቶስ ሰላም አይደለም!

ይልቁንም ጌታ ኢየሱስ እንዴት ነው ሰላሙን “ልሰጠን” የምችለው? ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቶስ ሰላም “ሁለቱን አንድ ያደረገ፣ የሚለያየውንም የጥል ግድግዳ ያፈረሰ ሰላማችን እርሱ ራሱ ነውና” (ኤፌ 2፡14) በማለት ሁለቱን አንድ እንደ ሚያደርግ የገለጸ ሲሆን የጠላትነትን መንፈስ በመደምሰስ እርቅ እንደ ሚፈጥር ይገልጻል። ይህንን የሰላም ሥራ ለማከናወን የምረዳን መንገድ ደግሞ የእርሱ አካል ነው። በእርግጥ እሱ ሁሉን ነገር ያስታረቀው እና ሰላም ያመጣው ደሙን በመስቀል ላይ በማፍሰስ ነው ሰላም የፈጠረው (ቆላሲያስ1፡ 20) ፡፡

እናም እዚህ ጋር እኔ አንድ ጥያቄ አለኝ፣ እናንተም ራሳችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ፣ “ታዲያ ሰላም የምያወርዱ እነማን ናቸው?” ። በተራራው ላይ በተደርገው ስብከት ውስጥ በሰባተኛው ክፍል ላይ በግልጽ እንደ ምያስቀምጠው ቀለል ያለ አገላለጽ ይጠቀማል፣ ስለአለም አፈጣጠር በሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ክፍል ላይ ከተጠቀሰው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን  ተነሳሽነት እና ታታሪነትን ያሳያል። ፍቅር በተፈጥሮ አዳዲስ የሆኑ ነገሮችን እንድንፈጥር ያነሳሳናል፣  እናም ማነኛውንም ዋጋ በመክፈል እርቅ እንዲፈጠር ያደረጋል።  የሰላም ጥበብን የተማሩ እና በተግባር ላይ ያዋሉት የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ፣ የራሳቸው ሕይወት ስጦታ አድርገው ካላቀረቡ በስተቀር እርቅ ሊፈጠር እንደ ማይችል ያውቃሉ። እናም ሰላም ሁል ጊዜ መፈለግ አለበት። ሁል ጊዜ ይህንን አንዳትረሱ! እንደዚህ መሆን አለበት ፡፡ ይህ የራስን ችሎታ በራስ የመፍጠር ሥራ አይደለም፣ እሱ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን አድርጎ የሰጠን ሰላማችን የሆነው ከክርስቶስ የተቀበልነው የጸጋ መገለጫ ነው።

እውነተኛ ሰላም እና እውነተኛ ውስጣዊ ሚዛን የሚመነጨው ከመስቀሉ የሚመጣ እና አዲስ ስብዕና ከምያስገኘው ከክርስቶስ ሰላም ሲሆን ይህም ቁጥር ስፍር በሌላቸው ቅዱሳን ሕይወት ውስጥ የተንጸባረቀ በፍቅር የተሞላ አዳዲስ መንገዶችን እንድንከተል እኛን ያነሳሳናል። ቅዱሳን እና ቅዱሳት የሰላም ገንቢዎች ናቸው። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው ወንድሞቻቸውን አዳኝ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ ደም የምያቀርቡ እና እውነተኛ ደስታ እንዲያገኙ ይረዳቸኋል። በዚህ መንገድ የምሄዱ ሁሉ ብጽዕን ናቸው ፡፡

የክርስቶስ ሰላም ይድረሳችሁ!

15 April 2020, 16:28