የባሪ ከተማ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስን ለመቀበል መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ የካቲት 15/2012 ዓ. ም. የደቡብ ኢጣሊያ ከተማ ወደ ሆነችው ባሪ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሀገር ውስጥ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር አመልክቷል። ቅዱስነታቸው ከክፍለ ሀገሩ ምዕመናን ጋር ሆነው መጪው እሁድ ከሚያሳርጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት በተጨማሪ፣ “ሜድትራንያን የሰላም ድንበር” በሚል ርዕሥ ሲካሄድ በቆየው፣ የኢጣሊያ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ስብሰባ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት መሆኑን በጳጳሳቱ ጉባኤ የመገናኛ መምሪያ ተጠሪ የሆኑት አቶ ቪንቼንሶ ኮራዶ አስታውቀዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በባሪ ከተማ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ለመቀበር ሲደረግ የቆየው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የመገናኛ መምሪያ ተጠሪው አስታውቀው በሥፍራው ሲካሄድ የቆየው የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤም፣ በጣሊያን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚደንት በሆኑት በብጹዕ ካርዲናል ጓልቲየሮ ባሰቲ ብርታት በሜዲተራንያን ባሕር አካባቢ የሚገኙ ቤተክርስቲያናት የሰላም ሁኔታ ላይ ለመምከር መሆኑ ታውቋል።

የጉባኤው ቀዳሚ ተልዕኮ

በብጹዓን ጳጳሳቱ ጉባኤ የመገናኛ መምሪያ ተጠሪ የሆኑት አቶ ቪንቼንሶ ኮራዶ እንዳስታወቁት በአካባቢው የሚገኙ ቤተክርስቲያናት በተለያዩ ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙም ቢሆንም ብዙ ተስፋን የሰነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል የጉባኤው ብጹዓን ጳጳሳት ቀዳሚ ተልዕኮም በእነዚህ ሁለት ርዕሠ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት መሆኑን ክቡር አቶ ቪንቼንሶ አስረድተዋል።

በከተማው የሚታይ ስሜት፣

የከተማው ምዕመናን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ወደ ስፍራው የሚደርሱበትን ዕለት በምኞት ቢጠብቅም ከዚህ በተጨማሪ፣ ሦስት ቀናትን በወሰደው የጣሊያን ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ መዝጊያ ላይ ቅዱስነታቸው ተገኝተው፣ ብጹዓን ጳጳሳት የጀመሩትን የሰላም ግንባታ ተግባር በብርታት እንዲገፉበት የሚያግዝ ሐዋርያዊ መልዕክት ለማድድመጥ መሆኑን አቶ ቪንቼንሶ አስታውቀዋል።

በጸሎት ተካፋይ ሕዝብ ቁጥር፣

እሑድ የካቲት 15/2012 ዓ. ም. ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት የሚካፈሉ እና ቅዱስነታቸው በዕለቱ የሚስተላልፉትን መልዕክት ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ምዕመናን ቁጥር በሽህዎች እንደሚቆጠር መሆኑን አቶ ቪንቼንሶ ገልጸው፣ የካህናት እና የዲያቆናት ቁጥር 500, የገዳማዊያን እና ገዳማዊያት ቁጥር 600 እንደሚሆን አስታውቀዋል። ከዚም በተጨማሪ ወደ 500 የሚሆኑ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚሰማሩ እና ወደ 400 የሚጠጉ የመገናኛ አገልግሎት ሠራተኞች የሚገኙ መሆናቸውን አቶ ቪንቼዞ አስታውቀው፣ በዕለቱ ይህን ያህል ሰው መገኘቱ የከተማዋን እንግዳ ተቀባይነት አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።       

19 February 2020, 17:47