በናይጄርያ የትምህርት ቤት ተማሪዎች በናይጄርያ የትምህርት ቤት ተማሪዎች  

ስልጣንን ለማግኘት ያስችል ዘንድ ሆን ተብለው የተፈጠሩ ተረቶች አጭር የሕይወት ዘመን ብቻ ነው ያላቸው!

54ኛው ዓለማቀፍ ማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴ ቀን በመከበር ላይ የገኛል። ለእዚህ 54ኛው ዓለማቀፍ የማኅራዊ የመገናኛ ዘዴ የሚሆን መልእክት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 15/2012 ዓ.ም ያፋ ማደርጋቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው ለእዚህ 54ኛው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ ዓለም አቀፍ ቀን ያስተላለፉት መልእክት  “ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ትናገሩ ዘንድ” (ዘጸአት 10፡2) በሚል አርእስት እና “ሕይወት ታሪክ ይሆናል” በሚል መሪ ቃል የተላለፈ መልእክት ነው። የእዚህን መልእክት የመጀሪያ ክፍል እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

 

“ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ተናገሩ ዘንድ” (ዘጸአት 10፡2)

ሕይወት ታሪክ ይሆናል

የዚህን ዓመት መልእክት በታሪክ አተረጓጎም ጭብጥ ላይ ማደረግ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም የእኛን ሕልውና ላለማጣት በመልካም ታሪኮች ውስጥ የራሳችንን እውነተኛ የሆነ አስተዋጾ ማድረግ አለብን የሚል እምነት ስላለኝ ነው። የሚገነቡ እንጂ የሚያፈሩስ ታሪኮች፦ ሥር መሰረታችንን መልሰን እንድንገኝ የሚረዱን ታሪኮች እና ወደ ፊት ለመራመድ የሚያስፈልገንን ጥንካሬ የሚሰጡን ታሪኮች ያስፈልጉናል። በዙሪያችን በሚሰሙት ድምጾች እና መልእክቶች ዝርዝር ውስጥ ስለራሳችን እና በዙሪያችን ስላለው ውበት የሚናገር የሰው ታሪክ እንፈልጋለን። ዓለማችንን እና ክስተቶችንም ሳይቀር በእርጋታ እይታ ሊመለከት የሚችል ትረካ ያስፈልገናል። እኛ ሕያዋን እና እርስ በእርሳችን የተቆራኘን አንድ አካል መሆናችንን ሊነግረን የሚችል ትረካ ያስፈልገናል። እንደ አንድ ሸማ ፈትል እርስ በርሳችን እንደ ምንገናኝ የሚያሳይ ትረካ ያስፈልገናል።

1.     የሽመና ታሪኮች

የሰው ልጆች ታሪክ ተራኪዎች ናቸው። ከልጅነታችን ጀምሮ ምግብ ካጣን እንደ ሚርብን ሁሉ እኛም ታሪክን እንራባለን። ተረት/ተረት፣ ልብ-ወለድ ፣ ፊልሞች ፣ ዘፈኖች ፣ ዜና ፣ ምንም እንኳን ሁልጊዜ ልብ ባንልም እንኳ እነዚህን የመሰሉ ታሪኮች በሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። ራሳችን በተጫወትናቸው ገጸ-ባህሪያት እና ባከናወናቸው ታሪኮች ላይ በመመርኮዝ ብዙውን ጊዜ ትክክል ወይም ስህተት የሆነው ታሪክ የቱ እንደ ሆነ እንወስናለን፣ ታሪኮች በእኛ ላይ አሻራ ያሳድራሉ፣ የእኛን እምነት እና ባህሪ ይቀርጻሉ። እኛ ማንነታችንን እንድንረዳ እና ማንነታችንን ለሌሎች መግለጽ እንችል ዘንድ ይረዱናል።

ተጋላጭነታችንን ለመሸፈን ልብስ የምንፈልገው እኛ ብቻ አይደለንም (ዘፍ 3: 21)፣ እኛም ህይወታችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ታሪኮችን “መልበስ” የሚኖርብን እኛ ብቻ ነን። እኛ የምንለብሰው ልብስ ብቻ ሳይሆን ታሪኮችን ጭምር ነው- በእርግጥም “ሽመና” (የሚለው ቃል በላቲን ቋንቋ ሲገለጽ) የሚያመልክተው ጨርቃጨርቅን መዘወር የሚለውን ትርጉም ብቻ ሳይሆን ጽሑፍንም ይመለከታል። በሁሉም ዕድሜ የሚገኙ ታሪኮች አንድ የጋራ የሆነ “ማእቀፍ” አላቸው፣ በራሳቸው የታሪክ ትረካ ሂደት ውስጥ በተከታታይ ሕልማቸውን እውን ለማደረግ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመጋፈጥ የሚዋጉ “ጀግኖች” ይገኙባቸዋል፣ ጥንካሬን በሚሰጣቸው የፍቅር ታሪክ በመታገዝ ፈተናዎችን በመቋቋም በእየለቱ በጀግንነት የሚጉዙ ጀጎኖች ታሪክ ይገኝበታል።

ራሳችንን በእነዚህ ዓይነት ታሪክ ውስጥ በማስገባት በሕይወታችን የሚጋጥሙንን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ እነዚህን የጀግንነት ታሪክ ሰርተው ያለፉትን ሰዎች ለማስታወስ ምክንያት እናገኛለን።

የሰው ልጆች ታሪክ ጸሐፊዎች ናቸው፣ ምክንያቱም እኛ ራሳችንን እያወቅን እና በሕይወታችን በምናሳልፋቸው ጥሩ ጊዜዎች እየበለጸግን ቋሚ በሆነ የእድገት ሂደት ውስጥ ገብተናልና።  ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ፣ የእኛ ታሪክ አደጋ ላይ ወድቋል፣ ክፉ የሆኑ እባቦች በታሪክ ሂደት ውስጥ የገኛሉ።

2. ሁሉም ታሪኮች መልካም የሚባሉ ታሪኮች አይደሉም!

“ከእርሱ ውስደህ ከበላህ . . . እንደ እግዚአብሔር ትሆናለህ (ዘፍ 3: 4)- የእባቡ ፈተና ሊቀለበስ የማይችል አስቸጋሪ የሆነ ታሪክ ያስተዋውቀናል። “ወስዳችሁ ከበላችሁ፣ እንደ እርሱ ትሆናላችሁ፣ ውጤታማ ትሆናላችሁ . . .” ። ይህ ዛሬ ይህንን መሰል ታሪክ በመፍጠር በዝባዢ የሆነ ዓላማዎቻቸውን ለመስረጽ በሹክሹክታ የሚናገሩ ሰዎች ድምጽ ነው። ደስተኛ ለመሆን ከፈለግን ያለማቋረጥ ማግኘት፣ መውረስ እና መብላት/መጠጣት እንዳለብን ሊያሳምኑን የሚፈልጉ አፍራሽ የሆኑ ስንት ታሪኮች አሉ! እኛ ለወሬ እና ለሐሜት ምን ያህል ስግብግብ እንደሆንን ፣ ወይም ምን ያህል ዓመፅ እና ውሸት እንደምንጠቀም እንኳን ላናስተውል እንችላለን። ብዙውን ጊዜ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ወይም መድረኮች የምናደርጋቸው/የምንናገራቸው ንግግሮች /ውይይቶች ማህበራዊ ግንኙነቶችን እና ባህላዊውን እሴቶችን የሚያጠናክሩ ገንቢ ታሪኮችን፣ የኅብረተሰቡን አንድነት የሚያጠናክሩ ታሪኮችን ሳይሆን አጥፊ እና አፍራሽ የሆኑ አንድነታችንን የሚያጠፉ እና አሉታዊ የሆኑ ቀስቃሽ ታሪኮችን እናገኛለን። ያልተረጋገጡ ቁርጥራጭ የሆኑ መረጃዎችን በማሰባሰብ ገንቢ እና አሳማኝ ያልሆኑ መረጃዎችን በመላክ ፣ ስውር እና የጥላቻ መልዕክቶችን በመላክ የሰውን ታሪክ መልካም በሆነ መልኩ ከመቀመር ይልቅ የሌሎች ሰዎችን መብት በሚጋፋ መልኩ እናቀርባቸዋለን።

ነገር ግን ለብዝበዛ እና ስልጣንን ለማግኘት ያስችል ዘንድ ሆን ተብለው የተፈጠሩ ተረቶች አጭር የሕይወት ዘመን ቢኖራቸውም በተቃራኒው ደግሞ ጥሩ የሚባሉ ታሪኮች ግን የቦታ እና የጊዜ ገደቦችን አልፈው መልእክታቸውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ከብዙ መቶ አመታት በኋላ ሳይቀር እንደ አዲስ ወቅታዊ ሆነው ሕይወትን ማረስረስ ይችላሉ።

ውሸት ይበልጡኑ እየተራቀቀ አስገዳጅ ወደ ሆነ ደረጃ ሲደርስ ውብ፣ እውነተኛ እና መልካም ታሪኮችን ለመቀበል እና ለመፍጠር እንድንችል ጥበብ ያስፈልገናል። ሐሰት እና መጥፎ የሆኑ ታሪኮችን ላለመቀበል ደፋር መሆን ይኖርብናል። ዛሬ በሚደረጉ ብዙ ክርክሮች መካከል እውነት የሆኑትን ነገሮች እንዳንጥል የሚረዱንን ታሪኮች መልሰን ለማግኘት ትዕግሥትና ማስተዋል ያስፈልገናል። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ የእኛን ትክክለኛ ማንነት መግለጽ የሚችሉ እውነተኛ ታሪኮችን ፈልገን ማግኘት ይኖርብናል።

3. የታሪኮች ታሪክ

ቅዱስ መጽሐፍ የታሪኮች ሁሉ የበላይ የሆነ ታሪክ ነው። ብዙ ክስተቶችን ፣ ሕዝቦችን እና ግለሰቦችን ከፊታችን ያኖራቸዋል! ከመጀመሪያው ጊዜ አንስቶ እርሱ እግዚኣብሔር ፈጣሪ እና ተራኪ መሆኑን ያሳየናል። በእርግጥ እግዚአብሔር ቃሉን ይናገራል፣ ነገሮችም ወደ ሕልውና ያገኛሉ ( ዘፍ 1)። እንደ አንድ ተራኪ እግዚአብሔር ነገሮች ሕይወት እንዲያገኙ የሚጠራው ጥሪ የመጨረሻ ግቡን የመታው ወንድና ሴትን በመፍጠር ከእርሱ ጋር ታሪክ የሚፈጥሩ ነፃ ውይይቶችን በማድረግ አጋሮቹ በማደረግ ነው። በመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ በአንድ ክፍል ውስጥ ፍጡር ለፈጣሪ እንዲህ ይላል “አንተ ውስጣዊ ሰውነቴን ፈጥረሃልና፤ በእናቴም ማሕፀን ውስጥ አበጃጅተህ ሠራኸኝ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና መሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፤ ነፍሴም ይህን በውል ተረድታለች። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ከአንተ አልተደበቁም፤ በምድር ጥልቀት ውስጥ በጥበብ በተሠራሁ ጊዜ ዓይኖቼ ያኔ ያልተበጀውን አካሌን አዩ!” (መዝ 139፡13-15) በማለት ይናገራል። ሙሉ ሆነን አይደለም የተወልድነው፣ በእየጊዜው “መሸመን” አልብን፣ “በአንድነት መጠቃለል” አለብን። እኛ ለሕይወታችን የሚሆን ድንቅ ምስጢር መቀባታችንን መቀበል ይኖርብናል።

በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል ታላቅ የፍቅር ታሪክ ነው። ኢየሱስ በመሃል ላይ ቆሟል ፣ የእሱ ታሪክ የእግዚአብሔር ፍቅር ለእኛም ሆነ ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ፍጻሜውን ያመጣል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየትኛውም ትውልድ ውስጥ የሚኖሩ ወንዶች እና ሴቶች ትርጉሙን በተሻለ መልኩ ለማስተላለፍ የተመረጥን የዚህ ታሪክ ተራኪዎች በመሆን ሁሉም ያስታውሰው ዘንድ ይህንን ታሪክ እንዲያበስሩ ተጠርተዋል።

የዚህ ዓመት መልእክት መሪ ቃል የተወሰደው እግዚአብሔር በሕዝቦቹ ታሪክ ውስጥ ጣልቃ ከገባበት የዘፀአት መጽሐፍ ነው። በባርነት የነበሩት የእስራኤል ልጆች ወደ እርሱ ሲጮኹ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፣ እናም ያስታውሳቸዋል፣ “እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) የጩኸታቸውን ሲቃ ሰማ፤ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አሰበ። እግዚአብሔርም (ኤሎሂም) እስራኤላውያንን ተመለከተ፤ ስለ እነርሱም ገደደው” (ዘጸ 2፡24-25)። የእግዚአብሔር ማደረ ትውስታ በተከታታይ በሚያሳያቸው ምልክቶች እና ድንቅ ነገሮች አማካይነት ከጭቆና ነፃነትን ያመጣል። ከዚያም ጌታ የእነዚህን ምልክቶች ሁሉ ትርጉም ለሙሴ ገልጦለታል፣ “ይኸውም ግብፃውያንን እንዴት አድርጌ እንደ ቀጣኋቸውና በመካከላቸውም ምልእክተኞቼን እንዴት እንደላኩኝ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትናገሩና እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) መሆኔንም እንድታውቁ ነው” (ዘጸ 10፡2) ይላል። የዘፀአት ልምምድ እንደሚያስተምረን የእግዚአብሔር እውቀት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንደሚተላለፍ በዋናነት እርሱ በሕዝቡ ህይወት ውስጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ ራሱን እንዴት ያቀርብ እንደ ነበረ የሚገልጸውን ታሪክ በመናገር ነው። የሕይወት አምላክ የሆነው እርሱ በሕይወታችን በሚገለጽ ታሪክ አማካይነት ያናገራል።

ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር የተናገረው ውስብስብ የሆኑ ጽንሰ-ሀሳቦችን በመጠቀም ሳይሆን ነገር ግን በዕለት ተዕለት ሕይወት የተወሰዱ አጫጭር ታሪኮች በመጠቀም ነው። በዚህ ጊዜ ሕይወት ታሪክ ይሆናል ፣ ከዚያም ለአድማጩ የሕይወት ታሪክ ይሆናል፣ ታሪኩን ለሚሰሙት ሰዎች ሕይወት አንድ አካል ነው፣ እናም ይቀይራቸዋል።

ቅዱሳን የሆኑ ወንጌላት እንዲሁ ታሪኮች እንጂ በአጋጣሚ የተገኙ ነገሮች አይደሉም። ስለ ኢየሱስ የሚናገሩ ቢሆንም እነርሱ “የሚያንጹ” ናቸው፣ እነሱ ኢየሱስን ለእኛ ያሳዩናል። በተጨማሪም ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሕይወት በመኖር አንባቢው ተመሳሳይ የሆነ እምነት እንዲካፈል ቅዱስ ወንጌል ይጠይቃል። የዮሐንስ ወንጌል እንደሚነግረን ቃል ራሱ ታሪክ እነደ ሆነ ይነግረናል “የእግዚኣብሔር አንዲያ ልጅ፣ እግዚኣብሔር ራሱ አጠገቡ ሆኖ አንዲያ ልጁ እንዲታወቅ ያደርገዋል”። እግዚአብሔር በግለሰብ ደረጃ የሰው ልጆችን ስጋ በመልበስ በእኛ ታሪክ ውስጥ ተካፋይ ሆኑዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
24 January 2020, 15:41