የሰውን ልጅ በተሻለ መልኩ ለማገልገል የሚያስችሉ ለውጦችን ማደረግ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 11/2012 ዓ.ም በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች ጋር ተገናኘተው በተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “የሰውን ልጅ በተሻለ መንገድ ለማገልገል ይቻል ዘንድ አንዳንድ ለውጦችን ማደረግ አስፈላጊ መሆኑን” ቅዱስነታቸው መናገራቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በቅርቡ የሚከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ከመከበሩ በፊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቤተክርስቲያኗ ባህል እና ደንብ መሰረት በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች ጋር ተገናኘተው “የእንኳን አደረሳችሁ” መልእክት እና ሰላምታ እንደ ሚለዋወጡ የሚታወቅ ሲሆን በሰላምታው ልውውጥ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን መዋቅሮች ውስጥ ስለሚከናወኑ ለውጦች ንግግር ማደረጋቸው ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ አጽኖት በመስጠት እንደ ገለጹት ቤተክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በዓለም ውስጥ እየተፈጠሩ የሚገኙትን አዲስ የሆኑ ሥርዓቶችን እና ፍላጎቶችን ለመጋፈጥ ያስችላት ዘንድ፣ እንዲሁም ተለዋዋጭነትን ለመጋፈጥ እና ፍርሃትን ለማሸነፍ፣ የክርስትና እምነት ችላ እየተባለ በመጣባት ዓለማችን ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን በተሻለ መልኩ ለዓለም ለማዳረስ ይችላ ዘንድ ቤተክርስቲያኗ የመዋቅር ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
በተደጋጋሚ የተለያዩ ዓይነት ለውጦችን በማድረግ ላይ ባለው ዓለማችን ውስጥ ቤተክርስቲያን እያደረገች የምትገኘው ለውጥ እንዲያው ለይስሙላ እንደ አንድ “የፋሽን ተከታይ” ከጊዜው ጋር ለመጓዝ በማሰብ ቤተክርስቲያን የምታደርገው ለውጥ እና ማሻሻያ እንዳልሆን በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበለይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያኗ የምታደርገው እና ለውጥ የምታመጣው ከእግዚአብሄር እይታ አንጻር ነው ብለዋል። መጽሐፍ ቅዱስም እንኳ “በመጀመር እና እንደገና በአዲስ መልክ በመጀመር የጉዞ ሂደት የሚታይበት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው የዘመናችን የቅርብ ጊዜ ቅዱስ የሆኑት ካርዲናል ኒውማን ለውጥን በመለከተ ሲናገሩ “ለውጥ” ማለት ውጫዊ ለውጣ ማለት ሳይሆን ውስጣዊ እና “መንፈስዊ ለውጥ” ማምጣት ማለት እንደ ሆነ መናገራቸውን ቅዱስነታቸው በንግግራቸው አስታውሰዋል።
ለውጥ እና መንቀሳቀስ ያለመቻል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የገናን በዓል አስመልክተው የእንኳን አድረሳችሁ ሰላምታ ለመለዋወጥ በቫቲካን በሚገኘው ክሌሜንቶስ አዳራሽ ውስጥ ለተገኙ በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች ያደረጉትን ንግግር በቀጠሉበት ወቅት እኛ አሁን የምንኖረው “በለውጥ ጊዜ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በጊዜ ለውጥ ውስጥ እንደሆነም” ተናግረዋል። ሁሉንም ነገር እንደነበረው በመተው ምንም ዓይነት ለውጥ ማደረግ አያስፈልግም በሚለው ምቾት በመታለል ከመኖር ይልቅ “በዘመናችን ውስጥ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በማንሳት ለራሳችን ጥያቄ ማቅረብ መቻል” ጤናማ የሆነ አስተሳሰብ ነው ብለዋል።
ብዙውን ጊዜ አዳዲስ ለውጦች ሲያጋጥሙ እኛም አዲስ ልብሶችን በመልበስ ውስጣችን ግን እንዳለው ሳይለወጥ ይቀራል። በአንድ ታዋቂ የጣሊያን ልብ ወለድ ውስጥ ያነበብኩት ታሪካዊ አገላለፅ አስታውሳለሁ ፣ 'ሁሉም ነገር እንደሁኔታው እንዲቆይ የምንፈልግ ከሆነ፣ ሁሉም ነገር መለወጥ አለበት’ በማለት ያንገራል።
ከዚያ በኋላ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትኩረታቸውን ወደ በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች አዙረው “ከዚህ በፊት ምንም ነገር እንደሌለ አድርጎ በማሰብ በእዚህ አግባብ መንቀሳቀስ ተገቢ አለምሆኑን” የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በተቃራኒው “በታሪክ ውስብስብ ሂደት ውስጥ የተከናወኑትን መልካም ነገሮች ሁሉ ይበልጡኑ አጠናክሮ ለመቀጠል” መትጋት ይኖርብናል ብለዋል።
መጻይ ጊዜውን ስር መሰረቱን በጠበቀ ሁኔታ እና ፍሬያማ በሆነ መልኩ ለመግንባት ይችላ ዘንድ በቅድሚያ ለእዚህ ጠንካራ መሰረት የሆነውን ያለፈን ጊዜ ታሪካችንን ማድነቅ ግድ ይለናል። ያለፈውን ጊዜ ታሪክ ማስታወስ ማለት ግን ራስችንን በራሳችን ጠብቀን ሳንነቃነቅ ባልንበት መቆም ማለት አይደለም፣ ነገር ግን በቀጣይ እድገት ውስጥ ሊያበረክተው የሚችለውን ሚና እና አስፈልጊ ተግባር ማሳትወስ ማለት ነው። ማህደረ ትውስታ የማይንቀሳቀስ ነገር ሳይሆን ተለዋዋጭ ነው። ማህደረ ትውስታ በተፈጥሮ ባሕሪው መንቀሳቀስን ያመለክታል።
ቅዱስ ወንጌልን በሚገባ ለማብሰር ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች ቀደም ሲል የተደረጉትን በርካታ ለውጦችን በተመለከተ በተናገሩበት ወቅት እንደ ገለጹት የቅድስት መንበር የዲምሎማቲክ ልዑካን ምርጫ በተመለከተ ልውጦች መደረጋቸውን የገለጹ ሲሆን በተጨማሪም በቫቲካን በቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ሥር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የበላይ የአስተዳደር አካላት እና የእርሳቸው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ወይም አማካሪዎች እና በተለያዩ ለየት ያሉ አብያተ ክርስቲያንት፣ እንዲሁም “የምስራቃዊያን አብያተ-ክርስቲያናትን ጨምሮ፣ በሐይማኖት ተቋምት መካከል እየተደረገ ስለሚገኘው ውይይት በተመለከተ ለውጦች መደረጋቸውን” ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በንግግራቸው ወቅት ጨምረው እንድ አገለጹት ቀደም ሲል የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጵጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና አሁንም ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክ አሥራ ስድስተኛ እንደተናገሩት ዓለማችን ለቅዱስ ወንጌል የሚሰጠው ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንደ ሚገኝ መናገራቸውን አስታውሰዋል። ይህንን ሁኔታ ለመጋፈጥ የሚይስችል ታሪካዊ ሊባል በሚችል መልኩ በቫቲካን ውስጥ የተለያዩ አዳዲስ መዋቅሮች እንዲቋቋሙ መንገዱን የከፈተ መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህም መሰረት የቤተክርስቲያኒቷን ዶክትሪን (የእመንት አስተምህሮ) እና ለሕዝቡ የስብከተ ወንጌልን ለማዳረስ ታስቦ የተቋቋመት የቤተክርስቲያን ተቋማት በአብነት እንደ ሚጠቀስ ገልጸው እነዚህ መዋቅራዊ ተቋማት የተቋቋሙት “ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በሁለት ወገኖች መካከል ያለውን ልዩነት በቀላሉ ለመለየት ታስቦ የተቋቋሙ ሲሆን በአንድ በኩል የሚገኘው የክርስቲያን ዓለም የሚያመልክት ሲሆን በሌላ በኩል የሚገኘው ደግሞ ገና ስብከተ ወንጌል ያልተዳረሱባቸውን የዓለማችን ክፍሎች እንደሚያመለክት ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ይህ ሁኔታ አይታይም። የቅዱስ ወንጌልን አዋጅ እስካሁን ድረስ ያልስሙ ሰዎች ምዕራባዊ ባልሆኑ አህጉራት ውስጥ ብቻ አይኖሩም። እነሱ በየተኛውም ስፍራ ይገኛሉ፣ በተለይም በጣም ብዙ ሕዝቦች ታጭቀው በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ስለሚገኙ ለእነርሱ የሚሆን ሐዋርያዊ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ለየት ያለ መዋቅር ያስፈልጋል። በትልልቅ ከተሞች ውስጥ የአስተሳሰባችንን እና የባሕሪያችንን አቅጣጫ ለመቀየር የሚረዳን ሌሎች 'ፍኖተ ካርታዎች' ሌሎች ምሳሌዎች ያስፈልጉናል። ከእዚህ ቀደም እንደ ነበረው የክርስትና ዘመን ውስጥ አይደለንምና! "
ቅዱስ ወንጌልን በሚገባ በዓለም ውስጥ ለማዳረስ ይቻል ዘንድ አንዳንድ የቫቲካን መዋቅሮችን መልሶ ማቋቋም እና ማሻሻል እንደ ሚገባ በማሳሰብ በርካታ ሐሳቦችን ይዞ የሚገኘው ባላቲን ቋንቋ (Evangelii gaudium) በአማርኛው በቅዱስ በወንጌል የሚገኝ ደስታ የተሰኘ ሐዋርያዊ መልእክት ቅዱስነታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእዚሁ ሐዋርያዊ መልእክታቸው ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ አመለካከቶች ፣ ዘይቤዎች ፣ የጊዜ ሰሌዳዎች እና ቋንቋዎችን በመጠቀም በአሁን ጊዜ በሚገኘው ዓለማችን ውስጥ ቅዱስ ወንጌልን ለማብሰር በሚደርገው ጥረት ውስጥ ተስማሚ የሆኑ ዘዴዎች እንደ ሆኑ ቀድም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል።
በእዚህ መሰረት በቫቲካን ሥር የሚተዳደሩ የተለያዩ ዘጠኝ የሕትመት እና የሚዲያ ተቋማት በአንድ ጥላ ሥር እንዲተዳደሩ እንደተደረገ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ዘጠኝ የተለያዩ ተቋማት በአንድ ላይ በተቀናጀ መልኩ በሚሰርሩበት ወቅት በተሻለ ሁኔታ ተግባራቸውን ማከናወን ስለሚያስችላቸው እንደሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።