ትሁት እና ጥበበኛ የነበረው ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚኣብሔር እንዴት መታመን እንዳለብን ያስተምረናል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በታኅሳስ 12/2012 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስረዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት በቅርቡ ከሚከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት በሚገኘው 4ኛው የስብከተ ገና ሰንበት ላይ ከማቴዎስ ወንጌል ማቴ 1፡18-24 ላይ ተወስዶ በተነበበውና የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ በሚገልጸው፣ “ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ የነበረ ሲሆን ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ” በሚለው የእግዚኣብሔር ቃል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ትሁት እና ጥበበኛ የነበረው ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚኣብሔር እንዴት መታመን እንዳለብን ያስተምረናል!” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእለት የተነበበው ቅዱስ ወንጌል

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነው፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ። በዚህ ሐሳብ ሳለ፣ የጌታ መልአክ በሕልም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፤ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ እጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና። ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።”

ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤ “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቃ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ እንዳዘዘው ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት። ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ የተወለደውንም ሕፃን፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳ 12/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድተከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ በአራተኛውና በመጨረሻው የስብከተ ገና ሰንበት (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የስረዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ማለት ነው) ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል (ማቴ 1፡18-24) በሁለተኛ ደረጃ ዮሴፍ ያስቀመጠውን እቅድ ተሞክሮ በመመርመር ክርስቲያኖች ሁሉ በእርሱ ጥበባዊ አመለካከት ተሞለተው ወደ ገና በዓል እንዲያመሩ ያደርጋል። እርሱ ከአጥማቂው ዮሐንስ እና ከማርያም ጋር በእዚህ በስብከተ ገና ሰሞን ስረዓተ አምልኮ ውስጥ እንዲካተት ከተደረጉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው፣ ሦስቱም ትክክለኛ የነበሩ ሰዎች ናቸው። የማይሰብክ ሰው አይናገርም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ይሞክራል። በቅዱስ ወንጌል መንገድ በመጓዝ እና በብጽዕና ይህም “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው ፣ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ናትና” (ማቴ 5፡ 3) የተባለውን በተግባር ይፈጽማል። ዮሴፍ በጣም ድሃ የነበረ ሰው ነበር፣ ምክንያቱም እሱ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ብቻ በሟሟላት ይኖር የነበረ ሰው ነው፣ ይህ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ መታመን እንደ ሚገባቸው ጠንቀቀው የሚያውቁ እና መተማመናቸውን በእርሱ ላይ ብቻ ያደረጉ ሰዎች የሚያሳዩት ድህነት ነው።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል በሰው ልጅ አመለካከት ሲታይ የሚያሳፍር እና የሚጋጭ ሁኔታን ያቀርባል። ዮሴፍ እና ማርያም ታማኝ እጮኛሞች ነበሩ። እነሱ ገና አብረው መኖር አልጀመሩም ነበር፣ ነገር ግን እርሷ በእግዚኣብሔር ድንቅ ሥራ የተጸነስ አንድ ልጅ በመጠባበቅ ላይ ነበረች። ዮሴፍ በዚህ ፊት ለፊቱ በተጋረጠበት አስገራሚ ሁኔታ ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ተጨንቆ ነበር፣ የተፈጠረውን ነገር ስሜታዊ በሆነ መልኩ እና መቀጣጫ በሆነ መልኩ ለክስተቱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሰብዓዊ መብትን ከግምት ባስገባ መልኩ እና ተወዳጅ እጮኛው የነበረችውን ማርያምን ባካተተ መልኩ መፍትሄ ይፈልጋል። ቅዱስ ወንጌል “እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ” (ማቴ 1፡19) በማለት ይናገራል። በእውነቱ ዮሴፍ በሁኔታው የተነሳ ማርያምን ከሱዋት ቢሆን ኖሮ በእርሷ ላይ ከባድ መዘዞች እንደ ሚከተሉ፣ አልፎ ተርፎም እስከ ሞት ድረስ የሚያደርሳት ተጋላጭነት እንደ ሚያጋጥማት በደንብ ይገነዘባል። እርሱ እጮኛ አድርጎ በመረጣት በማርያም ላይ ሙሉ እምነት አለው።

ሆኖም ይህ ሁኔታ በእዚህ እንዳለ አሁን የተፈጠረው በቃላት ሊገለጽ የማይቻል ሁኔታ የነበራቸውን ግንኙነት እንዲጠራጠሩ ያደርጋቸዋል፤ ስለሆነም በሁኔታው የተነሳ ታላቅ ስቃይ ውስጥ የገባ ሲሆን በማርያም ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ በማያስከትል መልኩ ከእርሷ ለመራቅ ወሰነ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ እርሱ ማለትም ዮሴፍ ለራሱ ያቀረበው የመፍትሄ ሐሳብ የእግዚኣብሔር ፈቃድ እንዳልሆነ ጣልቃ በመግባት ይነግረዋል። በተቃራኒው ጌታ ለእርሱ የኅብረት ፣ የፍቅር፣ የደስታ እና አዲስ አንድነት መፍጠር የሚያስችል መንገድ ይከፍታል-“የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ እጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና” (ማቴ 1፡21) በማለት ይነግረዋል።

በዚህ ጊዜ ፣ ዮሴፍ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን አመነ፣ ለመላእክቱ ቃል በመታዘዝ ማርያምን ወሰዳት። በትክክል ይህ በእግዚአብሄር ላይ የነበረው የማይለዋወጥ መታመን በሰው ልጅ አስተሳሰብ አስቸጋሪ እና ለመረዳት አዳጋች የሆነውን ሁኔታ እንዲገነዘብ ፈቃድ ሰጥቶታል። በማርያም ማህፀን ውስጥ ተጸንሶ የሚገኘው ሕጻን ልጅ የእርሱ ልጅ አለመሆኑን በእምነት አማካይነት የተረዳ ሲሆን ነገር ግን ልጁ የእግዚኣብሔር ልጅ መሆኑን አውቆ እርሱ ማለትም ዮሴፍ ምድራዊ አባቱ በመሆን ሙሉ በሙሉ ለሕጻኑ እንክብካቤ እንደ ሚያደርግ ተረዳ። ይህ የዋህ እና ጥበበኛ የሆነ ሰው ያሳየን መልካም አብነት እይታችንን ከፍ እንድናደርግ እና አሻግረን እንድንመለክት ያሳስበናል። ራሳችንን አዲስ ለተከፈተው አድማስ ለክርስቶስ እና ለቃሉ ክፍት በማደረግ ከትናንሽ ይሁን ከትላልቅ ስሌቶች በጣም ሩቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን አስገራሚ አመክንዮ መልሶ የመቀበል ጉዳይ ነው።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ንጹህ የሆነው እጮኛው ዮሴፍ፣ የሚመጣውን ኢየሱስ ለማዳመጥ፣ እንዲሁም በራሳችን እቅዶስች እና በምርጫዎቻችን ውስጥ ሳይቀር እርሱን እንድንቀበል እንዲረዱን ልንማጸናቸው ይገባል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
22 December 2019, 09:08