ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዓለም ውስጥ የሚገኘው ብዝሃነት ሕበረትን እንጂ ግጭት እንዳይፈጥር መሥራት ያስፈልጋል አሉ።

ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመባል የሚታወቁት ሁለት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎች 80 አመት የምስረታ በዓላቸውን ምክንያት በማደረግ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ በኅዳር 04/2012 ዓ.ም 80ኛውን ዓመት የምስረታ በዓላቸውን አስመልክተው ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ግለጹት በዓለም ውስጥ የሚገኘው ብዝሃነት ሕበረትን እንጂ ግጭት እንዳይፈጥር መሥራት ያስፈልጋል ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በልዩነቶች እና ብዝሃነት ምክንያት ግጭቶች በሚፈጠሩበት ዓለም ውስጥ ባለው ማዕበል ሳትወሰዱ  አእምሮዋችሁን፣ ልቦናችሁን እና እጆቻችሁን ተጠቅማችሁ የበኩላችሁን አዎንታዊ አስተዋጾ ማበርከት ይኖርባችኋል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በወቅቱ ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመባል የሚታወቁት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ሥር የሚተዳደሩት ዩኒቨርሲቲዎች 80 አመት የምስረታ በዓላቸውን ምክንያት በማደረግ በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ በተሰበሰቡበት ወቅት ከሁለቱ ዮኒቬርስቲዎች የተውጣጡ ከ6ሺህ በላይ ተማሪዎች በስፍራው የተገኙ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር “ቁርጠኛ መሆን፣ ጥበብን ማዳበር፣ በተቀናጀ መልኩ መሥራት” የተሰኙት ጭብጦች አእምሮዋችንን፣ ልቦናችንን እና እጆቻችን በመጠቀም ገቢራዊ ማድረግ እንደ ሚገባ የሚያሳቡ መልእክቶችን የተላለፉበት ንግግር እንደ ነበረ” ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

አንድነትን እና መተማመንን ማጎልበት

በወቅቱ በስፍራው ለተገኙት ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመባል የሚታወቁት ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን፣ በአስተዳደር ሥራ ውስጥ ለተሰማሩ ሰዎች እና ተማሪዎች ትኩረቱን ባደርገው ንግግር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ ገለጹት “አንድነትን እና መተማመንን ማጎልበት” እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን “ዩኒቬርሲቲ” እንደ አንድ ማኅበርሰብ የሚቆጠር ነው፣ ነገር ግን በተጨማሪም በዓለም ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በመወያየት እውነተኛ እና ትርጉም በሚሰጥ ጥልቅ እውቀት በመታገዝ በማኅበርሰቡ ውስጥ መግባባት እንዲፈጠር እና ተመጣጣኝ የሆነ እውቀት ያለው ማኅበርሰብ እንዲፈጠር ከፍተኛ የሆነ ሥራ ማከናወን እንደ ሚጠበቅባቸው ቅዱስነታቸው ጭምረው ገልጸዋል።

በዚህ አሁን ባለንበት ወቅት ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በተመለከተ ተለይተው በሚታዩት ግዴታዎች ፊት ለፊት የተጣለብንን ኃላፊነት የማደስ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ግንኙነት መፍጠር እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲ ተቋማት አራት ዓይነት ዋና ዋና ኃላፊነት እንደ ተጣለባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ መሆን

ሉምሳ እና የፍልሰታዋ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመባል የሚታወቁት ዩኒቨርሲቲዎች 80ኛውን አመት የምሥረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በቫቲካን በተገኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው ያደረጉትን ንግግር በመቀጠል የካቶሊክ ዩኒቨርስቲ መሆን ማለት የትኛውንም ልዩነቶች እና በዝሃነቶችን ከምትወክለው “የካቶሊክ” ቤተክርስቲያን የራሷን ምሳሌ መጠቀም ማለት ስለሆነ በመጽሐፍ ላይ የተመሰረቱ እውቀቶችን ማስተላለፍ ብቻ ሳይሆን ከእዚያም ባሻገር በመሄድ በማሕበርሰቡ ውስጥ የሚገኙ እሴቶችን፣ መልካም ስብዕና ያላቸው ግለሰቦችን እና እንዲሁም ማሕበራዊ ፍትህን የመሳሰሉ የማሕበርሰቡን ጠንካራ ዓምዶች ከግምት ባስገባ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱ ሊከናወን ይገባል ብለዋል።

ቀጣይነት ያለው ኃላፊነት እና ተልእኮ

ቀጣይነት ያለው ኃላፊነት እና ተልእኮ የተሰኙት በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጡ ግዴታዎች ሲሆኑ ከጠቅላላው የማኅበርሰቡ ራዕይ እና ከአጠቃላይ የማኅበራዊ እድገት እና አንድነት በሚፈጥር መልኩ የማኅበርሰቡን ሥር መሰረት ከግምት በማስገባት ኅላፊነትን መወጣት እንደ ሚገባ ገልጸው የማኅበርሰቡን ባሕላዊ መሰረት በጠበቀ መልኩ እና መንፈሳዊ ተልእኮን ጭምር በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም በዓለም ፊት ሚስዮናዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደ ሚገባ ጭምረው ገልጸዋል።

ማህበረሰብ እና በዩኒቬርስቲዎች መካከል ግንኙነት የመፍጠር ኃላፊነት

ማኅበራዊ ኃላፊነቶችን በተመለከተ እንደገናም፣ ማህበራዊ ሃላፊነት-ማለትም በማኅበርሰቡ ውስጥ የተቀናጀ ልማት ማምጣት የሚችሉ ኃይሎችን አስተባብሮ በብርታት ማስኬድን የሚጠይቅ እንደ ሆነ የገልጹት ቅዱስነታቸው በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የካቶሊክ ዩኒቬርሲቲዎች ይህንን መሰረታዊ ዓላማ ለማሳካት ይችላ ዘንድ ማንንም ባላገለለ መልኩ በሮቻቸውን ለሁሉም ክፍት ማደረግ እንደ ሚጠበቅባቸው ቅዱስነታቸው ጭምረው ገለጸዋል።

ፍራቻን ማስወገድ እና በትንሹ አለመርካት

ሁሉም ተማሪዎች፣ መምህራን እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መሪዎች ፣ ልብ እና አእምሮአቸውን  እንዲከፍቱ ያበረታቱት ቅዱስነታቸው በተለያዩ ምክንያቶች አለመግባባቶች በሚከሰቱበት ወቅት የዜግነት ኃላፊነታችሁን ከግንዛቤ ባስገብ መልኩ ልዩነቶች እና ብዝሃነት በከፍተኛ ሁኔታ በሚጸባረቅበት ዓለማችን ጤናማ እና አዎንታዊ የሆነ አስተዋጾ ማበረከት እንደ ሚጠበቅባችሁ በፍጹም መዘንጋት አይገባችሁም ብለዋል። ከአድሎ ከፍርሃት ነጻ በሆነ መልኩ ተጨባጭ እና ጠቃሚ የሆኑ መፍትሄዎችን እናንት ወጣቶች ማምጣት ይኖርባችኋል ያሉት ቅዱስነታቸው መምህራን ለመሆን መጣር ይኖርባችኋል፣ ለአሰተማሪዎቻችሁ ጥያቄ ማቅረብ በፍጹም እንዳትፈሩ፣ ይህም ተማሪዎች ራሳቸውን በተሻለ መልኩ ለመግለጽ እንደ ሚረዳ የገለጹት ቅዱስነታቸው ወጣት ተማሪዎች በሚያገኙዋቸው ነገሮች በትንሹ በመርካት ተዘናግተው መኖር ሳይሆን የበለጠ ለመሥራት መነሳሳት እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ከገለጹ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

/content/dam/vaticannews/pam/audio/agenzie/netia/2019/11/15/15/noti-1x-151119-135336518.mp3
14 November 2019, 16:33