ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ በባንኮክ ለቅዱስ ሉዊስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ንግግር ሲያደርጉ፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ በባንኮክ ለቅዱስ ሉዊስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ንግግር ሲያደርጉ፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ ኢየሱስ በድካማችን እና በሕመማችን በኩል ለእኛ ቅርብ መሆኑን ገለጹ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከህዳር 9 – 16/2012 ዓ. ም. ድረስ በሁለት የእስያ አገሮች ውስጥ የሚያደርጉትን 32ኛውን ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት በታይላንድ በማድረግ ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በተቀመጠላቸው የሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር መሠረት ለአገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ ለውጭ አገር ዲፕሎማቶች፣ ለፖለቲካ መሪዎች፣ ለሕዝባዊ ማሕበራት ተወካዮች እና ለሐይማኖት መሪዎች በአገሪቱ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተገኝተው የመጀመሪያ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ቀጥለውም በታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ የሚገኘውን የቅዱስ ሉዊስ ሆስፒታልን መጎብኘታቸው ታውቋል። በሆስፒታሉ ለሚሰሩት የጤና ባለሙያዎች እና በሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ሆስፒታሎች እንዲሁም እርዳታ መስጫ ማዕከላት ለሚሰሩት በሙሉ ንግግር አድርገዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ በስፍራው ለተገኙት ባሰሙት ንግግር  በድካማችን እና በሕመማችን በኩል ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ቅርብ መሆኑን አስረድተዋል።

በባንኮክ ከተማ ውስጥ ከተገነባ ዘንድሮ 120ኛ ዓመቱን ያስቆጠረውን የቅዱስ ሉዊስ ሆስፒታል የጎበኙት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቁጥር ወደ 700 መቶ ለሚሆኑት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ባሰሙት ንግግር ሆስፒታሉ በእውነትም እርዳታን ለሚሻው የታይላንድ ደሃ ማሕበረሰብ የሚያበረክተውን የሕክምና አገልግሎት በገሃድ መመስከር መቻሌ ቅድስና ነው ብለዋል።

ፍቅር ባለበት እግዚአብሔር አለ የሚለውን የሆስፒታሉን መሪ ቃል ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በሆስፒታሉ በኩል የምናበረክተው የቸርነት አገልግሎት እኛ ክርስቲያኖች ለዚህ አገልግሎት የተጠራን ሐዋርያት መሆናችንን ብቻ ሳይሆን የተሰጠንን ተልዕኮ በተግባር በመፈጸም የሐዋርያነታችንን በታማኝነት መፈጸማችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በሆስፒታሉ ውስጥ አገልግሎት በመስጠት በህክምና ሥራ የተሰማሩት በሙሉ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋቸውን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ ብለው በዚህ ተልዕኮዋቸው በተለይም አቅመ ደካሞችን በማከም እና በመፈወስ፣ በእነርሱም በኩል እግዚአብሔርን ያዩታል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩት የሕክምና ባለሞያዎቹ የምሕረትን ታላቅ ሥራ በመስራት ላይ መሆናቸውን አስረድተው በማበርከት ላይ የሚገኙት የፈውስ ስራ ለህክምና አገልግሎት ከሚሰጠው ትርጉም በላይ ነው ብለዋል።

ወደ ሆስፒታሉ የሚመጣውን የሰው ሕይወት በፍቅር ተቀብሎ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እያንዳንዱ ከሰብዓዊ ክብር አንዱ ነው ብለዋል። ቅዱስነታቸው በንግግራቸው እንደገለጹት የሕክምናን ሞያ በተግባር ማከናወን ከባድ መሆኑን አስታውሰው፣ በማከልም የጤና አገልግሎት ለሕሙማን ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የማሕበርሰብ አባል በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሊያገኘው የሚፈልገው እንክብካቤ የሚቀርብበት ተልዕኮ መሆኑን አስረድተዋል።

የሕክምና አገልግሎትን ለማግኘት በምንሄድበት ጊዜ ህመማችንን ብቻ የምናስታውስ ቢሆንም በድካማችን፣ በሕመማችን እና በስቃያችን በኩል ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የምንቀርብ መሆናችንን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
21 November 2019, 16:37