“የሁሉም ቅዱሳን” ዓመታዊ በዓል “የሁሉም ቅዱሳን” ዓመታዊ በዓል  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ወደ ብጽዕና የምወስደንን መንገድ መከተል ይኖርብናል”

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 22/2011 ዓ.ም ማለት ነው “የሁሉም ቅዱሳን” ዓመታዊ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉ ይታወቃል። ይህ በዓል በቫቲካን በተከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይህንን “የሁሉም ቅዱስ” በዓለ ለመታደም ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በዕለቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ተወስደው በተነበቡ ምንባባት ላይ ተመስርተው ባሰሙት አስተንትኖ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ወደ ብጽዕና የሚወስደንን መንገድ መከተል ይኖርብናል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም በጥቅምት 22/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በዕለቱ የተከበረውን “የሁሉም ቅዱሳን” ዓመታዊ ክብረ በዓል አስመልክተው ያሰሙትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አባራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ ከዮሐንስ ራእይ ተወስዶ በተነበበልን የዛሬው የመጀመርያ ምንባብ ሰለሰማይ በመናገር “ለመቁጠ የምያዳግቱ ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ” (7፡9) በእነርሱም ፊት አቆመኝ በማለት ይናገራል። እነዚህ ሰዎች ቅዱሳን ናቸው። ታዲያ እነርሱ "እዚያ ላይ ሆነው" ምን ያደርጋሉ? በጋራ ሆነው በመዘመር እግዚኣብሔርን ያሞግሳሉ። ውዳሴያቸውን ማዳመጥ መልካም ነበር. . .ነገር ግን ወዳሴያቸው ምን እንደ ነበር መገመት እንችላለን፡ ይህ ውዳሴ መቼ እንደ ሚደረግ ታውቃላችሁ ወይ? ይህ ወዳሴ የሚደረገው በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች” (ኢሳያስ 6፡3) በማለት መጽሐፍ ቅዱሳችን በሰማይ ሆነው የሚዘምሩ ሰዎችን ይገልጻል። ስለዚህ "ቅዱስ" የሚለውን መዝሙር የሚዘምሩት ቅዱሳን ብቻ ሳይሆኑ ነገር ግን እኛም ቅዱሳን የሚዘምሩትን ውዳሴ አብረን ከእነርሱ ጋር በመሆን እንዘምራለን፣ በዚህም ሁኔታ ይህን ውዳሴ በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት በምንዘምርበት ወቅት ከሁሉም ጊዜ በላይ ከቅዱሳን ጋር ያለንን ሕብረት እንገልጻለን ማለት ነው።

እኛ ሁላችን ከቅዱሳን ጋር ኅበረት ፈጥረናል፣ ይህም ማለት የሰረዓተ አምልኮ የቀን አቆጣጠር ደንብ ላይ የተጠቀሱትን ቅዱሳን ብቻ ማለታችን ሳይሆን ነገር ግን የቅድስናን በር ለማለፍ የተዘጋጁ ሰዎች የምናውቃቸውን በብጽዕና መንገድ ላይ የተጓዙ ሰዎችን ማለታችን ጭምር ነው። በዚህም መሰረት ዛሬ የቤተሰብ በዓል እናከብራልን ማለት ነው። ቅዱሳን ለእኛ በጣም ቅርብ ናቸው እንዲያውም ቅዱሳን የእኛ እውነተኛ ወንድሞች እና እህቶች ናቸው። በጣም ይረዱናል፣ መልካም ነገሮችን ይመኙልናል፣ የእኛ እውነተኛ እና ትክክለኛ መልካም የሆነ ነገር ምን እንደ ሆነ ያውቃሉ፣ ያግዙናል ይንከባከቡናልም። እነርሱ በጣም ደስተኞች ናቸው እኛም ከእነርሱ ጋር በገነት ደስተኛ ሆነን እንድንኖር የፈልጋሉ።

የዛሬው ቅዱስ ወንጌል እንደ ሚለው እና በጣም ውብ በሆነ መልኩ እንደ ተቀመጠው “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፣ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው” (ማቴ 5.3-8) በማለት እንደ ተጠቀሰው ለዚህም ነው ቅዱሳን በደስታ መንገድ እንድንጓዝ የሚጋብዙን በዚሁ ምክንያት ነው። ዓለማችን ሐብታሞች የተባረኩ ናቸው” ብሎ በምያወራበት ሰዓት ቅዱስ ወንጌል ደግሞ በተቃራኒው ድኾች ብጹዕን ናቸው” ይለናል። ቅዱስ ወንጌል የዋሆች  እና ድኾች ብጹዕን ናቸው” ሲል ዓለም ደግሞ ኃያላን ብጹዕን ናቸው” ይለናል። ቅዱስ ወንጌል ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው” ሲል ዓለም ደግሞ ተንኮለኞች እና መሰሪዎች ብጹዕን ናቸው” ይለናል። ይሄ የደስታ መንገድ፣ ይህ ወደ ብጽዕና የሚያደርሰው መንገድ፣ ይህ ወደ ቅድስና የምያደርሰው መንገድ በዓለም እይታ ስንመለከተው ወደ ሽንፈት የሚያመራ መንገድ ይመስላል። የመጀመርያው ምንባብ ላይ እንደ ተገለጸው ቅዱሳን በእጃቸው የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ነበር” ይለናል ይህም የድል አድራጊነት ምልክት ነው። ከዓለም ጋር በነበራቸው ውግያ ያሸነፉት እነርሱ ናቸው። የእርሱ ተግባር ሁሉ ቅዱስ የሆነውን አምላክ እንድንመርጥ ያሳስበናል።

ከምድር ነን? ወይስ ከሰማይ? ከየተኛው ወገን እንደ ሆንን ራሳችንን እንጠይቅ። ለእግዚኣብሔር ነው ወይስ ለራሳችን ብቻ ነው የምንኖረው? ለዘለዓለም ደስታ ነው ወይስ ጊዝያዊ ለሆነ በየሰዓቱ ለምናገኘው ደስታ ነው የምንሰራው? ያለምንም ውጣ ውረድ ክርስቲያን መሆን ነው የምንፈልገው ወይስ ምንድነው? በአጠቃላይ የምንፈልገው ምንድነው? ቅድስና ነው ወይስ ምን? ይህ ጉዳይ ሰለ ቅዱሳን በማሰብ መኸል መንገድ ላይ እንዳንጓዝ በማሳሰብ በብርታት ቅዱሳንን መከተል እንደ ሚገባን ያሳስበናል፣ ምክንያቱም እግዚኣብሔርን መምረጥ ማለት በትህትና፣ በምሕረት፣ በንጽሕና መንገድ መጓዝ ማለት ነው፣ ከምድር ይልቅ ሰማይን መመልከት ይኖርብናል።

ዛሬ እነዚህ በሰማይ የሚገኙ የእኛ ወንድሞች እና እህቶች የሆኑ ቅዱሳን የሚጠይቁን ነገር ቢኖር ሌላ አዲስ ቅዱስ ወንጌል እንድናነብ ሳይሆን ያወ የተነበበልንን የምናወቀውን ቅዱስ ወንጌል በሥራ በተግባር ላይ እንድናውለው እና በብጽዕና መንገድ መጓዝ እንድንችል ነው። በጣም ድንቅ የሆኑ ተዐምራዊ የሆኑ ነገሮችን እንድንፈጽም ሳይሆን የሚያሳስቡን እለታዊ በሆነው ኑሮዋችን ጥቃቅን የሚባሉትን መልካም ነገሮች በመፈጸም እንድንተጋ ነው የሚይጠይቁን፣ ይህንንም በቤታችን እና በቤተሰብ ውስጥ እንኳን ሳይቀር በተግባር በማዋል ልንተገብረው እንችላለን። ጌታ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ” (ማቴ 5፡12) በማለት ይህንን ደስታ እንድንቋደስ ይጋብዘናል። የእግዚኣብሔር እናት የሆነችው እና የቅዱሳን ሁሉ እናት የሆነቺው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቅድስና መንገድ ላይ በአግባቡ መጓዝ እንችል ዘንድ እንድትረዳን እርሷ የሰማይ ደጃፍ በመሆኗ የተነሳ ወደ እዚያ በር እንድናመራ እንድትረዳን ልንማጸናት ይገባል።

01 November 2019, 16:44