ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ጋር በቫቲካን ተገናኙ። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ጋር በቫቲካን ተገናኙ። 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአማዞን ደን አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ጋር በቫቲካን ተገናኙ።

ከመስከረም 25-ጥቅምት 16/2012 ዓ.ም “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዐን ጳጳሳት ቅዱስ ሲኖዶስ በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኝ ቀድም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ። በጥቅምት 06/2012 ዓ.ም በአማዞን ደን እና በአዋሳኝ አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች ከተውጣጡ 40 ሰዎች ጋር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በግንኙነት ወቅት ቅዱስነታቸው የእነዚህን ቀደምት ሕዝብ ባሕል በጠበቀ መልኩ ቅዱስ ወንጌልን ለማስፋፋት ቤተክርስቲያን የበኩሉዋን አስተዋጾ እንደ ምታደረግ ቅዱስነታቸው አረጋግጠውላቸዋል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እነዚህ በአማዞን ደን እና በአዋሳኝ አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች የተውጣጡ 40 ሰዎች ገሚሶቹ በአሁኑ ወቅት “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዐን ጳጳሳት ሲኖዶስ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ከእዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሳ ለመሳ በሆነ መልኩ በመከናወን ላይ በሚገኘው የአማዞን ሕዝቦችን ባሕል ባማከለ መልኩ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳተፊ የሆኑ ሰዎች የሚገኙበት ሲሆን ይህንን ቡድን በመምራት ላይ የሚገኙት ደግሞ በብራዚል የሮኩዌ ፓሎሺ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ካርዲናል ክላውዲዮ ሁሜስ መሆናቸውም ተገልጹዋል።

ግንኙነቱን በተመለከተ የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጫ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማቴዎች ቡሩኒ ስለሁኔታው በሰጡ መግለጫ እንደ ገለጹት እነዚህ በአማዞን ደን እና በአዋሳኝ አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦች የተውጣጡ 40 ሰዎች ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በነባራቸው ቆይታ በአማዞን ደን እና በአዋሳኝ አከባቢ ከሚኖሩ ቀደምት ተወላጅ ሕዝቦችን በመወከል አንድ ወንድ እና አንድት ሴት ንግግር ማደረጋቸውን የገለጹ ሲሆን የአማዞን ደንን በተመለከተ “ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲካሄድ የበኩላቸውን ከፍተኛ አስተዋጾ ላደረጉት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ምስጋናቸውን በማቅረብ ለህዝባቸው ሰላምና ደስታ የሰፈነበት፣ መሬታቸውን የመንከባከብ እና ከደኑ የሚፈልቁትን የውሃ ምንጮች በመንከባከብ፣ ቀጣዩ ትውልድ ደስተኛ የሆነ ሕይወት መኖር እንዲችል እና ፍላጎቶቻቸውን በተግባር ማዋል ይችሉ ዘንድ እገዛ እንዲደረግላቸው” መጠየቃቸውም ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በበኩላቸው ባደረጉት አጭር ንግግር እንደ ገለጹት ቅዱስ ወንጌል ልክ እንደ አንድ ዘር ፍሬያማ መሆን የሚችለው በሚያርፍበት መሬት ጥራት እና ልክ መሆኑን ገልጸው የክርስትና እምነት ከአይሁድ እምነት እንደ ተወለደ እና ከእዚያም ቀስ በቀስ በግሪክ እና በላቲን ዓለማት፣ በመቀጠልም ወደ መላው ዓለም እንደ ተስፋፋ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩም “ሕዝቦች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መልካም ዜና ባሕላቸውን እና እሴታቸውን ከግምት ባስገባ መልኩ” ወንጌላዊ አገልግሎትን ማከናወን እንደ ሚገባ መናገራቸው ተገልጹዋል።

 

18 October 2019, 15:28