ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፥ “ከመንፈስ ቅዱስ የሚላከውን ለውጥ ለመቀበል ታማኝ መሆን ያስፈልጋል”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለፓን-አማዞን ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ልዩ ጉባኤ በቅዱስ ጴጥሮስ ቤዝሊካ መስዋእተ ቅዳሴ አድርገዋል፡፡ ቅዱስነታቸው ለጳጳሳቱ በሙሉ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዎስ በላከው መልእክት ላይ ልብ እንዲሉ በጥብቅ አሳስበዋል ፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መቅድም ገረመው - ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ለቤተክርስቲያኒትዋ ሐዋርያዊ ስራ አዳዲስ መንገዶችን ለመቀየስ እና ሥነ-ምህዳራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት” የሲኖድ ጉባኤ እንደሚካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገሩት እ. አ. አ. ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ. ም. በመሩት የመላእከ እግዚአብሔር ጸሎት ላይ ነበር፡፡

በትላንትናው እለት እሑድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የ “ሲኖዶስ” ጉባኤ መክፈቻ ላይ በቤተክርስትያን ታሪክ ውስጥ የሐዋርያው ጳውሎስን ታላቅ መልእክተኛንትን በመግልጽና ይህንንም ጉባኤ ፍሬአማ ይሆን ዘንድ እንደሚያግዛቸው ከተናገሩ በኋላም ፣ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼሰኮስ ሐዋርያው ጳውሎስ  ለጢሞቴዎስ የላከውን መልእክት ሲጠቅሱ፣ “እጆቼን በመጫን በናንተ ያለውን የእግዚአብሔር ስጦታ እንደገና እንደሚቀሰቀስ አሳስባችኋለሁ” በማለት የላከውን ነበር አጣቅሰው የተናገሩት፡፡

በመቀጠልም ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለዚህ ሲኖዶስ የተሰበሰቡትን ጳጳሳት  በሙሉ ያ የሐዋርያው ጳውሎስ እጅ በነሱ ላይ መሆኑን አምነው እግዚአብሔርን በመተማመን እጆቻቸውን ከፍ በማድረግ ወንድሞቻቸውን እና እህቶቻቸውን መርዳት እንደሚችሉ አሳስበዋል። አያይዘውም “እኛ ስጦታ እንሆን ዘንድ ስጦታን ተቀብለናል” ስጦታዎች አይገዙም ፣ ለሽያጭም አይቀርቡም ነገር ግን የተቀበልነው ደግሞም በነጻ የምንሰጠው ነገር ነው ራሳችንን የተቀበልናቸው ስጦታዎቻችን ማእከል ላይ ካደረግን እረኞች ሳንሆን ወግ አጥባቂዎቸ እንሆናልን በማለት አስገንዝበዋል።

“ለተቀበልነው ስጦታ ምስጋና ይግባውና ሕይወታችን አገልግሎት ላይ ነው መዋል ያለበት ካሉ በኋላም እኛ የምናገለግለው ለግል ጥቅማችን ወይም ለትርፍ ብለን አይደለም ፣ ነገር ግን በነፃነት ስለተቀበልን እና በምላሹ በነፃ መስጠት ስላለብን ነው በማለት ጳጳሳቱን የእግዚአብሔርን ስጦታ በመሰጠት መስጠት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ለጥሪያችን ታማኝ ከሆንን” ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ እንዴት እንደገና መታየት እንዳለበት ሲናገሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ ሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት በመመለስ፣ ይህ ስጦታ እንደ እሳት መቀጣጠ አለበት ነገር ግን እሳቱ ብቻውን አይቀጣጠልም በማለት ክርስቶስ የአለም ብርሃን ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ይህ የስጦታ እሳት መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ገልጸው  ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዳለው “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ፣ የማስተዋል መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም” ብለው ያብራሩ ሲሆን ቅዱስነታቸው እንዳሉት ሐዋርያው ጳውሎስ ፍራቻን በመቃወም ብልህነትን አሳይቷል ብለዋል ፡፡ ከዚያ በኋላም ትምህርተ ክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ የጥበብን ትርጉም እንደሚከተለው አብራርተዋል ፣ “በማንኛውም ሁኔታ እውነተኛነታችንን ለመለየት እና ትክክለኛውን ለማሳካት ትክክለኛውን መንገድ ለመምረጥ ተግባራዊ ምክንያትን የሚያንፀባርቅ በጎነት” ነው በማለት አብራርተዋል፡፡

በመቀጠልም “ጥበብ ወይም ማስተዋል የእረኝነት መሳርያ ነው። በማስተዋል ለማገልገል በመንፈስ ቅዱስ ለመታደስም ያበረታል።ስጦታዎቻችንን በመንፈስ ቅዱስ እሳት መቀስቅስ መቻላችን ከስንፍና ይጠብቀናል ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ የማስተዋል ችሎታን እንዲሰጠንና ጉባኤአችንን ባርኮ የዚህች ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያዊ ስራ እንዲቀጣጠል በማለት ጸልየዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስም “ህዝቦች እና ባህሎቻቸው ያለፍቅር እና ያለ አክብሮት ሲኖሩ” ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ሳይሆን የዓለም እሳት ነው ”በማለት ያስገነዘቡ ሲሆን፡፡ አክለውም “ከአዳዲስ የቅኝ ግዛት ዓይነቶች ከስግብግብነት እግዚአብሔር ይጠብቀን” ብለዋል ፡፡

አያይዘውም በቅርቡ አማዞንን ያወደመውን የሰደድ እሳት በመጥቀስ ይህ እሳት “የወንጌሉ እሳት አይደለም” ብለዋል ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እሳት ለትርፍና ለስግብግብንት ሳይሆን አብሮ በመኖር የሚተገበር ነው ካሉ በኋላ “የሚያጠፋው እሳት” “ሰዎች የራሳቸውን ሀሳብ ብቻ ለማስተዋወቅ ሲፈልጉ እና… ሁሉንም ሰው እና ሁሉንም ነገር አንድ ወጥ ለማድረግ ሲጥሩ ነውም” ብለዋል ፡፡

ከዚሁ ጋር በማያያዝ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የጠየቀውን “ስለወንጌል ምስክርነት” በመድገም ሲያጠናቅቁ፡ ወንጌልን ለመስበክ በመስዋእትነት መኖር ፣ እስከ መጨረሻው መመሥከር ፣ እስከ ሞት ድረስ ማፍቀር ነው በማለት አሳስበዋል። በተጨማሪም ራሳቸው በመስጠት “የሰማዕትነት መስቀልን” የተካፈሉ የተወሰኑ ካርዲናሎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

ስለሆነም ወንጌልን እናገለግላለን፡በትህትናና በፍቅር በመጽናት “ሕይወትን ለመኖር ብቸኛው እውነተኛ መንገድ በፍቅር ሕይወትን ማጣት ነው” በማለት አሳስበዋል።በመጨረሻ ንግግራቸው በአማዞንያ ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን “ከባድ የሕይወት መስቀሎችን በመሸከም እና በወንጌል ብርሃን ነጻ በመውጣት ላይ ይገኛሉ ካሉ በኋላም ቤተክርስቲያንም በፍቅር ስለፍቅር ስራ ትተጋለችም ብለዋል። አክለውም “በአማዞን ያሉ ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ህይወታቸውን ሰጥተዋል” በማጣቀስም “የእኛ ተወዳጁ ካርዲናላችን ሁሜስ በአማዞን በሚገኙ ትናንሽ ከተሞች ውስጥ ባሉ የመቃብር ቦታዎች በመደበኛነት ይሄዱ እንደነበር ተናግረው እነዚህ ህይወታቸውን የሰጡ ሰዎችም ቅድስና ይገባቸዋል ይሉ እንደነበርም ተናግረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም በመጨረሻ ሕይወታቸውን ለሰጡት፣ አሁን ሕይወታቸውን እየሰጡ ካሉት ጋር ሆነን ወደ ፊት አብረን እንጓዝ በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል።

07 October 2019, 18:13