ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸውን ሲያቀርቡ፣ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸውን ሲያቀርቡ፣ 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአፍሪቃን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው መመለሳቸው ተገለጸ።

ማክሰኞ ጠዋት ጳጉሜ 5/2011 ዓ. ም. ከማዳጋስካር ዋና ከተማ አንታናናሪቮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጉዟቸውን ወደ ሮም ያቀኑት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት ከጥቂት ደቂቃዎች  ወደ ሮም ቻምፒኖ አውሮፕላን ማረፊያ መድረሳቸውን የቫቲካን ዜና አገልግሎት ባልደረባ አሌሳንድሮ ዲ ቡሶሎ የላከልን ዘገባ አመልክቷል። ሰባት ቀናትን በወሰደው የአፍርቃ አህጉር ቆይታቸው ቅዱስነታቸው በሞዛምቢክ በማዳጋስካር እና በሞሪሼስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደረጉ መሆናቸውን ታውቋል። 

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ይህ 31ኛው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ ቅዱስነታቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡበት ከመጋቢት 4/2005 ዓ. ም. ወዲህ በአፍሪካ አህጉር ያደረጉት ሦስተኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲሆን ከዚህ በፊት እ. አ. አ በ2015 ዓ. ም ወደ ኬኒያ፣ ኡጋንዳ እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው፣ ቀጥለውም በሚያዚያ ወር 2009 ዓ. ም. በግብጽ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከነሐሴ 29 - ጳጉሜ 5 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በሦስቱ የአፍሪቃ አገሮች ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ወደ ሮም በተመለሱ ጊዜ፣ በሮም ከተማ ወደ ሚገኘው ወደ ታላቁ ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በመሄድ የምስጋና ጸሎታቸውን አድርሰዋል።

ቅዱስነታቸው ከዚህ በፊትም ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ከመጀመራቸው አስቀድመው እና ካጠናቀቁው በኋላም ወደ ሮም ከተማ በሚመለሱበት ወቅት በሮም ከተማ በሚገኘው እና ሳናታ ማርያ ማጆሬ በመባል በሚታወቅ  የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ በመሄድ የተማጽኖ እና የምስጋና ጸሎት እንደሚያቀርቡ ይታወቃል።

በሮም ከተማ የሚገኝ ታላቁ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ባዚሊካ፣ ባላቲን ቋንቋ “Salus Populi Romani” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም “የሮም ከተማ ሕዝቦች አዳኝ እና ጠባቂ” በመባል የሚታወቅ ሲሆን በሮም ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ክብር የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ቤተክርስቲያን ውስጥ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሕጻኑን ኢየሱስን በእጆቹዋ ላይ አቅፋ መያዙዋን የሚያሳየው ምስል የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ትናንት ማክሰኞ ጳጉሜ 5/2011 ዓ. ም. ለ31ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ስኬታማነት እና ምኞታቸው መፈጸም ለረዳቻቸው ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስጋናቸውን 

11 September 2019, 17:07