ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በጉዞ ላይ ሆነው ለጋዜጠኞች መልስ በሰጡበት ወቅት፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በጉዞ ላይ ሆነው ለጋዜጠኞች መልስ በሰጡበት ወቅት፣  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የባሃማ ደሴቶች ሕዝቦችን በጸሎታችን እንድናስታውሳቸው አሳሰቡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ወደ ሞዛምቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ ባደረጉት የአውሮፕላን ጉዞ ወቅት፣ የባሕር ላይ አውሎ ነፋስ ባደረሰው አደጋ ከፍተኛ ጥፋት ለደሰባቸው፣ በካሬቢያን ደሴቶች መካከል ለባሃማ ሕዝቦች ጸሎት እንድናደርግ አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው ወደ አፍሪቃ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው አብሮአቸው ለተጓዙት ጋዜጠኞች ሰላምታቸውን ከማቅረባቸው አስቀድመው፣ ዶሪያን በተባለ የባሕር ላይ አውሎ ነፋስ ምክንያት በርካታ የሰው ሕይወት ለጠፋበት፣ ክፉኛ የመቁሰል አደጋ ለደረሰበት፣ ቤት ንብረት ለወደመበት ለባሃማ ደሴቶች ነዋሪዋች የሕብረት ጸሎታቸውን አቅርበውላቸዋል። ቅዱስነታቸው በባሃማ ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ጥፋት ያስከተለው አደጋ ዜና የደረሳቸው በአውሮፕላን ጉዞ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዶሪያን የተባለ የባሕር ላይ አውሎ ነፋስ በባሃማ ያደረሰው ጥፋት፣
ዶሪያን የተባለ የባሕር ላይ አውሎ ነፋስ በባሃማ ያደረሰው ጥፋት፣

የዶሪያን አውሎ ነፋስ ያስከተለው ጥፋት፣

ባሁኑ ጊዜ ወደ መካከለኛው አሜሪካ የደረሰው፣ ዶሪያን የተሰኘ የባሕር ላይ አውሎ ነፋስ፣ በየካቲት እና በሚያዚያ ወር በሞዛምቢክ ላይም ከፍተኛ አደጋን አስከትሎ ያለፈ፣ ኢዳይ እና ኬነት አውሎ ነፋስ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ አፍሪቃ አህጉር በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በቅርቡ ሥራቸውን የጀመሩት የቫቲካን ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ ማቴዎ ብሩኒ መገኘታቸው ታውቋል።

ቅዱስነታቸው ለጋዜጠኞች ያቀረቡት ሰላምታ፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አብሮአቸው በመጓዝ ላይ ለሚገኙት ጋዜጠኞች ባቀረቡት ሰላምታ፣ ዘንድሮ ሰማንያ ዓመቱን ያከበረውን የስፔን ዜና ማሰራጫ ማዕከልን አስታውስዋል። በማከልም የዜና ማዕከሉ በዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ እንዲሳተፍ መጋበዙንም ገልጸዋል። ከተለያዩ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ በተደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝቶች ውስጥ ለ152 ጊዜ የተሳተፈች የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ አላዝራኪ በዚህ ጉዞ ላይ ያልተሳተፈች መሆኗን ተናግረው፣ ተጉህ ጋዜጠኛ እና በቅርቡም በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደል እና ብዝበዛ የሚገልጽ ድንቅ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃቷንም አስታውሰው ይህ መጽሐፍ በዘመናችን ሴቶች ላይ የሚደርስ ስቃይ ምን ያህል ከባድ መሆኑን ያስረዳል ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
04 September 2019, 16:49