ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በአማዞን ደን ላይ እየተቃጣ ያለው ውድመት መቃወም ያስፈልጋል” አሉ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በአማዞን ደን ላይ እየተቃጣ ያለው ውድመት መቃወም ያስፈልጋል” አሉ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በአማዞን ደን ላይ እየተቃጣ ያለው ውድመት መቃወም ያስፈልጋል” አሉ

በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” በአማርኛው ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በግንቦት 24/2015 ዓ.ም አንድ ሐዋርያዊ መልእክት ይፋ ማደረጋቸው ይታወቃል። በዚህ በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርእስት ሐዋርያዊ መልእክታቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ የዛሬ 4 አመት ገደማ ያፋ ያደርጉት ሐዋርያዊ መልእክት ሲሆን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ በዓለማችን ላይ የሚታየው የአየር ንብረት ለውጥ መንስሄ ምድራችንን ያለ አግባቡ በመበዝበዛችን፣ ከባቢ አየርን ሊበክሉ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችን፣ ጋዞችን ወደ አከባቢ በመልቀቃችን በመሳሰሉ ጉዳዮች የተከሰተ እና የጋራ የመኖርያ ቤታችንን አደጋ ላይ የጣለ ክስተት በመሆኑ ክስተቱን ለመግታት ባለድርሻ አካላት የራስቸውን ሚና መጫወት ይገባቸዋል የሚል ጭብጥ ያለው ሐዋርያዊ መልእክት እንደ ሆነ ይታወሳል።

ይህንን የቅዱስነታቸውን ሐዋርያዊ መልእክት ዋና ዓላማ በመደገፍ የተለያዩ የሲቪክ ማሕበራት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ ተመሥርተው በእዚህ ዓላማ ዙሪያ ላይ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን የእዚህ ማኅበር አባላት ደግሞ በእዚህ በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” ውዳሴ ለአንተ ይሁን በተሰኘው ሐዋርያዊ መልእክት ውስጥ የተጠቀሱትን ፍሬ ሐሳቦችን ተቀብለው በተግባር ላይ እያዋሉ የሚገኙ ብዙ ግለሰቦች እና ማኅበራት እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ግለሰቦች እና ማኅበራት በግል እና በቡድን በመሆን የአከባቢ ጥበቃ በማደረግ ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

እ.አ.አ ከመጪው ጥቅምት 6-27/2019 ዓ.ም ድረስ “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ በቫቲካን እንደ ሚካሄድ ቀደም ሲል ባስተላለፍናቸው ዘገባዎቻችን መግለጻችን ይታወሳል። ለእዚህ “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር” በሚል መሪ ቃል ሊካሄድ በታቀደው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚሆኑ ቅደመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ““የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን ከጥፋት እንዴት መከላከል እንደ ምንችል” ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚችሉ ዝግጅቶች በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ውስጥ በምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አማካይነት እየተካሄደ እንደ ሚገኝ ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የቫቲካን ዜና በሬዲዮ፣ በድህረ ገጽ፣ እና እንዲሁም በተለያዩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የአማርኛ እና የትግረኛን ቋንቋዎች ጨምሮ በ 34 የተለያዩ የአለማችን ቋንቋዎች በሚያስተላልፋቸው ዝግጅቶቹ አማካይነት የአከባቢ ጥበቃን በተመለከተ የግንዛቤ መስጫ ዝግጅቶችን በማስተላለፍ ላይ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን እ.አ.አ ከመጪው ጥቅምት 6-27/2019 ዓ.ም ድረስ “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ የአማዞን ደን ከሚያዋስናቸው አገራ መካከል አንዱ በሆነችው በብራዚል በማዞን ደን አከባቢ ለሚገኙ ሰዎች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት የሚያደርጉትን ሲኖዶስ  በቀጥታ መከታተል ያስችላቸው ዘንድ በአጭር ሞገድ የሬዲዮ ስርጭት አገልግሎት እንደ ሚሰጥ ተገልጹዋል።

በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በቀዳሚነት ተጎጂ የሚሆኑት ደግሞ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ክስተት ሁነኛ አስተዋጾ ያላደረጉ በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በተለይም ደግሞ የአማዞን ሕዝቦች ለብዙ አመታት ያህል ተገለው የኖሩ፣ እንዲሁም በከፍተኛ የድኽነት አረንቋ ስር የሚገኙ፣ በአከባቢያቸው የሚገኘው እና ለብዙ ሺ አመታት ለእነዚህ ለአማዞን ሕዝቦች እና ለዘር ማንዘራቸው በመጠለያነት፣ የምግብ ምንጭ በመሆን በአጠቃላይ የሕይወታቸው ሕልውና የሆነው የአማዞን ጥቅጥቅ ደን በሕገወጥ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ እየተጨፈጨፈ ለተወሰኑ ሰዎች ከፍተኛ የገንዝብ ማግኛ ምንጭ ቢሆንም እነዚህ የአማዞን ሕዝቦች ግን በከፍተኛ የድኽነት አርቋ ሥር ሰለሚገኙ፣ የመኖር ሕልዋናቸው አደጋ ላይ በመውደቁም ጭምር፣ እንዲሁም የአማዞን ደን “የዓለማችን ሳንባ” በመባል የሚታወቅ በመሆኑ የእዚህ ደን አደጋ ላይ መውደቅ የአማዞን ሕዝቦች የመኖር ሕልውናቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ብቻ ሳይሆን የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የመኖር ያለመኖር ህልውናቸው እና ዋስትናቸው በመሆኑ ጭምር “የጋራ መኖሪያ ቤታችንን እንከባከብ” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የዓለማችን ሳንባ” በመባል የሚታወቀውን የአማዞን ደን እና እንዲሁም በዓለም ደረጃ በተመሳሳይ መልኩ የሚደረጉ የድን ጭፍጨፋዎችን እና በምድራችን ላይ የሚቃጣውን ማነኛውም አደጋ መከላከል ይቻል ዘንድ ለዓለም ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

በቅርቡ በከፍተኛ ደረጃ በአደጋ ላይ የሚገኙትን የአማዞን ሕዝቦች እና መልካ ምድራቸው ከተጋረጠበት ከፍተኛ አደጋ ለመታደግ በማሰብ አማዞንን የተመለከተ አንድ ሲኖዶስ እንደ ሚዘጋጅ የተገለጸ ሲሆን ለእዚህ ሲኖዶስ አገልግሎት የሚውል ቅድመ ጥናቶች በመደረግ ላይ እንደ ሚገኙ ለቫቲካን ሬዲዮ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከቤተክርስቲያን ጋር በመሆን በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሕዝቦችን ጩኸት እናዳምጥ በሚል መርህ ዙሪያ የቅድመ ዝግጅት ውይይት በቫቲካን በመካሄድ ላይ ይገኛል። የአማዞን ሕዝቦች በአከባቢያቸው ላይ በከፍተኛ ደረጃ እየደረሰ የሚገኘውን የደን ጭፍጨፋ ለማስቆም በርካታ ጥረቶችን ማደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን አከባቢያቸውን እና ደናቸውን እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ ለመታደግ ባለመቻላቸው የአማዞን ሕዝቦች የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እገዛ የጠየቁ ሲሆን ቤተክርስቲያን ኢየሱስ ወደ ዓለም በመጣበት ወቅት የሰው ልጆች ሁሉ በተለይም ድሆች ምልአት ያለው ሕይወት እንዲኖሩ ለማደረግ ወደ እዚህ ምድር እንደ መጣ ሁሉ ቤተክርስቲያን ይህንን የኢየሱስ ስክርስቶስን ተልእኮ የማስቀጠል ኃላፊነት ስለተጣለባት በእዚህ ረገድ  የአማዞን ሕዝቦች የሕይወት የኑሮ ዋስትና የሆነው የአማዞን ደን ላይ እየደረሰ የሚገኘው ከፍተኛ ውድመት ይቆም ዘንድ ቤተክርስቲያን የበኩሉዋን አስተዋጾ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በእዚህም መሰረት በእዚህ ጉዳይ ዙሪያ በቅርቡ “አማዞን፣ የቤተክርስቲያን አዳዲስ እርምጃዎች ለተቀናጀ ስነ-ምዕዳር”  በሚል መሪ ቃል ለሚደርገው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዐን ጳጳሳት ሲኖዶስ ግብዐት ይሆን ዘንድ ቅድመ ዝግጅት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በቅርቡ የአማዞን ሕዝቦችን እና የአማዞን ድን በተመለከተ ለሚደረገው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹዐን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚያገለግል የቅድመ ዝግጅት ሰነድ በሰኔ 10/2011 ዓ.ም በቫቲካን ይፋ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ የቅድመ ዝግጅት ሰነድ ርዕሰ ሊቃን ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ከጥር 10-13/2010 ዓ.ም. በፔሩ አድርገውት በነበረው 22ኛው ሐዋሪያዊ ግብኝት ከአማዞን ሕዝቦች ጋር በተገናኙበት ወቅት . . .

“የአማዞን መሬት ለያዘው ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት እና ሕዝብ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ከአመታት ወዲህ የአማዞን ሕዝብ ሸክም ከባድ እየሆነ መምጣቱ የሚታይ ነው። ወደዚህ ሥፍራ እንድመጣ ከገፋፉኝ ምክንያቶች አንዱም ይህ ስለሆነ ሸክማችሁን ለመጋራት፣ ችግራችሁን በማዳመጥ፣ በአካባቢያችሁ፣ በሕይወታችሁና በባሕላችሁ ላይ የሚመጣውን ጥቃት ከመላዋ ቤተክስቲያን ጋር ሆነን ለመመከት ያለኝን ልባዊ ፍላጎቴን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ። በአማዞን ሕዝብ ታሪክ ውስጥ፣ ሕዝቡ የዛሬን ያህል የከፋ ጊዜ ገጥሞት አያውቅም። የአማዞን ግዛት በተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ይስተዋላል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው በስፍራው ተገኝተው የሁኔታውን አሰክፊነት በዓይናቸው በማየታቸው የተነሳ ይህ የቅድመ ዝግጅት ሰነድ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር እና እንዲሁም የአማዞን ደን የሚያዋስናቸው አገራት ሕዝቦች ጋር በተደጋጋሚ ጉዳዩን በተመለከተ ውይይት ከተደረገ በኋላ ይፋ የሆነ የቅድመ ዝግጅት ሰነድ እንደ ሆነ በመግለጫው ተጠቅሱዋል።

“የዓለማችን ሳንባ” በመባል የሚታወቀው የአማዞን ደን 7.8 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ክልል ሲሆን ብራዚል፣ ቦሊቪያ፣ ፔሩ፣ ኤኳዶር፣ ኮሎንቢያ፣ ቬንዙዌላ፣ ጉያና እና ሱሪናም የሚዋሰኑበት ስፊ ግዛት አቅፎ የያዘ ነው። ይህ የአማዞን ደን በአሁኑ ወቅት በምድራችን ላይ ከሚገኙ ደኖች መካከል 40% የሚሆነው የደን ሽፋን በአማዞን የተያዘ ነው።

የአማዞን ሕዝቦች ድምጽ

የእዚህ የቅድመ ዝግጅት ሰንድ የመጀምሪያ ክፍል “የአማዞን ሕዝቦች ድምጽ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ሲሆን በአማዞን ደን ውስጥ እና በመዳረሻዎቹ ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች የስቃይ ድምጽ አካቶ የያዘ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአማዞን ሕዝብ ከደኑ ከሚወጣው ውኃው እና እንዲሁም ከፍጥረታትና የእንስሳት ዝርያዎች፣ ከሚፈሱት ትላልቅ ወንዞች ጋር ሕዝቡ ያለውን የጠበቀ የሕይወት፣ የባህል እና መንፈሳዊ ውህደት እና ትስስር፣ እንዲሁም እነዚህ ነገሮች በሕዝቡ ሕይወት ላይ ያላቸው አዎንታዊ ተፅዕኖዎች፣ በአማዞን ደን ዙሪያ የሚኖሩ በሽዎች የሚቆጠሩ ቀድምት ሕዝቦች ዘር ከደኑ ጋር ያላቸው የጠበቀ ትስስር፣ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አድሮች፣ በአማዞን ዙሪያ በሚገኙ ወንዞች ላይ ኑሮዋቸውን የመሰረቱ ሕዝቦች አጠቃላይ የስቃይ ድምጽ የሚያስተጋባ የሰነዱ የመጀርያ ክፍል ነው።

በአደጋ ላይ ያለ ሕይወት

በአማዞን ደን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቃጣ የሚገኘው ጭፍጨፋ እና ውድመት 40% የሚሆነውን የምድራችን ጥቅጥቅ ደን የሚገኝበትን ይህንን አከባቢ በከፍተኛ ደረጃ ወደ ውድመት እየቀየረው እንደ ሚገኝ የሚያወሳው ሰንዱ በእዚህም የተነሳ በአማዞን ድን ላይ ሕይወታቸው የተመሰረት በርካታ ሕዝቦች የኑሮዋቸው ዋስትና አደጋ ላይ መውደቁን በሰፊው በሰነዱ ውስጥ ተካቶ ይገኛል። በአማዞን ደን ውስጥ የሚገኙትን ቀደም ሕዝቦች ከቦታቸው ለማፈናቀል በተቀናጀ መልኩ ወንጀሎች እንደ ሚፈጸሙ የሚያወሳው ሰንዱ በእዚህም የተነሳ የሰዎች መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሱ እንደ ሚገኙ በተለይም ደግሞ የዓለማችን ሐብት የሆኑት እስከ ዛሬ ድረስ ከሰዎች ጋር ተቀላቅለው የማያውቁ በደኑ ውስጥ የሚኖሩ ቀድምት ሕዝቦች ሕይወት አደጋ ላይ እየወደቀ እንደ ሚገኝ በሰፊው የሚዘረዝር ሰነድ ነው።

የምድራችን እና የድሆች ጩኸት

የቅድመ ሰነዱ ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ደግሞ በምድራችን ላይ በተቃጣው ከፍተኛ አደጋ የተነሳ ምድራችን እና ሕዝቦቿ በመጮኽ ላይ ይገኛሉ የሚል እንድምታን ያዘለ ሰነድ ሲሆን ይህንን ችግር ከተቻለ ለማስወገድ ካልሆነ ለመቀነስ ይችላ ዘንድ የሚረዱ አንዳንድ አስተያየቶችን አቅፎ የያዘ የሰነዱ ክፍል ነው። በእዚህም መሰረት የምድራችንን እና የሕዝቦቿን በተለይም የድሆን ጩኸት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ የተቀናጀ የስነ-ምዕዳር አሰራሮችን መከተል እንደ ሚገባ የሚያትት የሰነዱ ክፍል የሚገኝበት ነው።

የአማዞን መሬት የያዘውን በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ ወርቅ እና ዛፎችም ላይ ብዙዎች እጃቸውን አስገብተዋል። የቦታውን ሕዝቦች ሕይወት ያላገናዘበ የመንግሥት የተፈጥሮ ጥበቃ ፖሊሲዎች በነዋሪው ላይ ችግር እያስከተለ ይገኛል” በእዚህም የተነሳ መንግሥት ለእዚህ አንገብጋቢ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባዋል የሚል አንቀጾች የተካተቱበት የሰነዱ ክፍል ነው።

  

የኢትዮጲያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑት ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ “አረንጓዴ አሻራ” ለአገራችን ለኢትዮጲያ ጥለን እንለፍ በሚል ሐሳብ ለመላው የኢትዮጲያ ሕዝብ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም 200 ሚልዮን የዛፍ ችግኞች በመላው የአገሪቷ ክፍል መተከላቸው እና በእዚህም ኢትዮጲያ ይህንን ያህል የዛፍ ችግኝ በአንድ ቀን በመትከሉዋ የአለም ሪከርድ መስበሯ ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህንን የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር የዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ ተከትሎ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ ቀን በማስመልከት በሐምሌ 22/2011 ዓ.ም ሆላንድ ፓርክ በመባል በሚታወቀው ስፍራ ተገኝተው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ትሳታፊ ሆነዋል።

በዕለቱም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና ሰራተኞች ችግኞችን
ተክለዋል። በእዚህ የችግጅ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ የነበሩት ክቡር አባ ጴጥሮስ በርጋ “እግዚአብሔር የሰጠንን የጋራ ቤታችን የሆነችው ምድራችንን የመንከባከብ ሀላፊነት እያንዳንዳችን እንድንወጣ” ጥሪ አቅርበዋል።
“Earth Overshoot Day” (የምድርን የተፈጥሮ ሐብት ከመጠን በላይ በመጠቀማችን የሚደርሰውን ጉዳት) በተመለከተ ታስቦ የሚውለው ቀን በሐምሌ 22/2011 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። “Earth Overshoot Day” (የምድርን የተፈጥሮ ሐብት ከመጠን በላይ መጠቀም የሚያደርሰው ጉዳት) የሚታሰብበት ቀን መሬትን ከመጠን በላይ መጠቀም በተመለከተ የሰው ልጅ ሥነ ምህዳራዊ ሀብቶች እና አገልግሎቶችን ምድራችን በአንድ አመት ውስጥ መልሳ ማምረት ከምትችለው መጠን በላይ የምድራችንን ሐብት መጠቀም የሚያስከትለውን ከፍተኛ አደጋ አስመልክቶ ታስቦ የሚውል ቀን ሲሆን በእዚህ ቀን ምድራችን በአንድ አመት ውስጥ ልትሰጠን ከምትችለው የተፈጥሮ ሐብት እጅግ በላቀ መልኩ በምድራችን ላይ ጫና በማደረግ ምድራችንን ለከፍተኛ አደጋ እና የአየር ንብረት ለውጥ እንደ ሚዳርጋት የሚያሳስብ ቀን ነው።

“Earth Overshoot Day” (የምድርን የተፈጥሮ ሐብት ከመጠን በላይ በመጠቀማችን የተነሳ የሚከሰተውን ጉዳት) በተመለከተ ታስቦ የሚውለው ቀን በሐምሌ 22/2011 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሮ ባለፈበት ወቅት ምድራችንን ከመጠን በላይ በመጠቀማችን የተነሳ የምድር ተፈጥሮአዊ ስነ-ምዕዳር በመዛባቱ የተነሳ አለማችን ለከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ መዳረጓ እለት በእለት የምናስተውለው እውነታ ሲሆን በተለይም ደግሞ በማደግ ላይ የሚገኙ አገራት በሚባሉት እንደ ኢትዮጲያ ባሉት አገራት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተንሰራፋ በመጣው የደን ጭፍጨፋ ታክሎበት የአገሪቷን ተፈጥሮአዊ የሆነ መልካ ምድራዊ ትሩፋቶችን እያሳጣት እና ለከፍተኛ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ እየዳረጋት፣ ሕዝቦቿንም ለረሃብ እና ለሰቆቃ እየዳረገ መምጣቱ ተከትሎ የገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር በሆኑት በዶክተር አብይ አህመድ አነሳሽነት በአንድ ቀን ብቻ 200 ሚልዮን ችግኞች በሐምሌ 22/2011 ዓ.ም መተከላቸው ይታወሳል።

በእዚህ አጋጣሚ ይህ መልካም የሆነ ጅምር ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ሬዲዮ ቫቲካን የአማርኛው የስርጭት አገልግሎት የበኩሉን ጥሪ በማቅረብ ይህ መልካም ጅምር ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ተነሳሽነትን የሚፈጥሩ ሐሳቦችን በሬዲዮ እና በብዙሃን መገናኛ መስመሮቹን በመጠቀም ሐሳቦች እዲሸራሸሩ የበኩሉን ሙያዊ ድጋፍ እንደ ሚያደርግ ለመግለጽ እንወዳለን።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የማኅበራዊ አስተምሮዎቿ አማካይነት የአለም የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ የሚገኘውን አደጋ በተመለከተ እና በተለይም ከኢንዱስትሪ አብዮት ማበብ እና መስፋፋትን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ በከባቢ አየር ላይ በሚለቀቁ ጋዞች የተነሳ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በአለም ላይ እየተከሰተ የሚገኘው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ በቀዳሚነት ለዚህ ችግር እዚህ ግባ የሚባል አስተዋጾ ያላበረከቱትን የአለማችን በማደግ ላይ የሚገኙ አገራትን ከፍተኛ የሆነ ዋጋ እያስከፈለ በመሆኑ የተነሳ፣ የእነዚህን የድሃ አገራት ሕዝቦች ለስደት እና ለመከራ እየዳረገ የሚገኝ አደገኛ ክስተት በመሆኑ የተነሳ ባለ ድርሻ አካላት የበኩላቸውን እርምጃ እንዲወስዱ እና ታጋሽ የኃይል ምንጮችን እንዲጠቀሙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በማሳሰብ ላይ ትገኛለች።

ለእዚህም እርምጃ በዋቢነት የሚጠቀሰው ደግሞ የዛሬ አራት አመት ገደማ በላቲን ቋንቋ “Laudato Si” በአማርኛው በግርድፉ ሲተረጎም ውዳሴ ለአንተ ይሁን በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይፋ ያደርጉት ሐዋርያዊ መልእክት በአብነት የሚጠቀስ ሲሆን “የጋራ የመኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” የሚል ጭብት የያዘ ሐዋርያዊ መልእክት ይፋ ማደረጋቸው ይታወሳል። ይህ ሐዋርያዊ መልእክት ስድስት ምዕራፎችን በውስጥ አቅፎ የያዘ ሐዋርያዊ መልእክት ሲሆን የእዚህ ሐዋርያዊ መልእክት መሪ ሐሳብ የመነጨው ደግሞ እ.አ.አ. በ11ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው እና ለተፈጥሮ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፍቅር ከነበረው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲሲ ጥሎት ካለፈው አሻራ ሲሆን እርሱም ምድራችንን በተመለከተ ሲናገር “የጋራ ቤታችን፣ ሕይወታችንን የምናጋራት እህታችንና እጆቹዋን ዘርግታ የምታቅፈን ውድ እናታችን” በማለት ምድራችንን ውበት ይገልጽ የነበረ ሲሆን በተጨማሪም “ጌታዬ ሆይ በምትንከባከበን እና በምታስተዳድረን በቀለማት ባሸበረቁ አበቦች እና ዕጽዋት በተሞላችውና ልዩ ልዩ ፍሬዎችን በምታፈራልን እህታችን እና እናታችን ምድር አማካይነት ተወደስ” በማለት የተፈጥሮን ሥጦታዎን በመመልከት ብቻ የእዚህ ስጦታ ፈጣሪ የሆነውን አምላክን ማወደስ እንደ ሚቻል ይገልጽ ነበር። ምድራችንን መንከባከብ ማለት የአምላክ ስጦታን መንከባከብ ማለት እንደ ሆነ አበክሮ ይገልጻል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
24 August 2019, 11:47