ካህናት “እያከናወናችሁት ስለምትገኙት አገልግሎት አመሰግናለሁ! ካህናት “እያከናወናችሁት ስለምትገኙት አገልግሎት አመሰግናለሁ!  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ካህናት “እያከናወናችሁት ስለምትገኙት አገልግሎት አመሰግናለሁ! አሉ

ከ160 ዓመታት በፊት ልክ ዛሬም በእኛ ዘመን እንደ ሚከናወነው ማለት ነው፣ በፈረንሳይ አገር በልዮን አውራጃ አከባቢ በምትገኘው አሪስ በመባል በምትታወቀው በአንዲት መንደር ውስጥ ትገኝ በነበረችው ቤተክርስቲያን ቆመስ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያኔይ ለሁሉም ካህናት የሚሆን መልካም እና የፍቅር ምሳሌ ጥሎ ማለፉ የሚዘከርበት እለት በትላንትናው እለት ማለትም በሐምሌ 28/2019 ዓ.ም ታስቦ መዋሉ ይታወሳል።

የእዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪያኔይ በሕይወት በነበረበት ወቅት “በምድር ላይ ሳለን ካህን ምን ማለት እንደሆነ በደንብ ጠንቅቀን ከተረዳን እንሞታለን፣ የምንሞተው ደግሞ በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር ነው” በማለት አዘውትሮ በመናገር በወቅቱ በኋላፊነት የተቀበላቸውን ምዕመናን በተገቢው መልኩ ሐዋርያዊ፣ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ በማድረግ በተቀናጀ መልኩ ለእግዚኣብሔር ሕዝብ ጥበቃ በማደረግ እና ከለላ በመሆን ማለፉ ይታወሳል፣ በእዚህም የተነሳ የካህናት ሁሉ መልካም አብነት ተደርጎ በመቆጠር በእየ አመቱ በስሙ አመታዊ የመታሰቢያ በዓል እንደ ሚዘጋጅ ይታወቃል፣ በእዚህም እለት ከህናት የቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪዬኔይ አብነትን በመከተል የተሰጣቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት ይወጡ ዘንድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የማበረታቻ መልእክቶች በመላው ዓለም ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት እንደ ሚተላለፍ ይታወቃል።

ቅዱስነታቸው በሐምሌ 28/2011 ዓ.ም ይፋ ባደረጉት መልእክታቸው ካህናት “እየፈጸማችሁት ለምትገኙት አገልግሎት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በመላው ዓለም ለሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያ ምዕመናን ያስተላለፉት መልእክት ምንም እንኳን የክህነት አገልግሎት በጣም አድካሚ እና አንዳንዴም ተስፋ ሊያስቆርጥ የሚችል አገልግሎት ቢሆንም፣ በየቀኑ መስዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ እና ከእግዚአብሔር ህዝብ ጋር አብረው ለሚጓዙ ካህናት ሁሉ ያላቸውን ድጋፍ ፣ ቅርበት እና እንዲሁም ማበረታቻ ገልጸዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ ማሪያ ቪዬኔይ በሕይወት ዘመኑ አከናውኖት ባለፈው መልካም ተግባር የተነሳ በሁሉም ዘመን ለሚኖሩ ካህናት መልካም አብነት እና ምሳሌ ያሳየ በመሆኑም ጭምር በመላው ዓለም የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ጠባቂ ተደርጎ የሚቆጠር ታላቅ ቅዱስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእለቱ ይህ ታላቅ ቅዱስ የሞተበት 160ኛው አመት ተዘክሮ ባለፈበት ወቅት ይፋ ባደረጉት መልእክታቸው “እዩኝ እዩኝ ሳይሉ እንዲያው በዝምታ መልካም ተግባራቸውን በማከናወን ላይ የሚገኙ ብዙ ካህናት እንደ ሚገኙ” ገልጸው ሕይወታቸውን ማሕበረሰቡን ለማገልገል ማዋላቸው ደግሞ ልያስመሰግናቸው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ጨምረው እንደ ገለጹት “እያንዳንዳችሁ በተለያዩ ሁኔታዎች እና ቦታዎች ለምትገኙ፣ በተለያዩ መስዋዕትነትን በሚያስከፍሉ ቦታዎች የሚተገኙ፣ በመከራ ወይም በድካም ውስጥ ለምትገኙ፣ ተስፋ በመቁረጥ ወይም ደግሞ በበሽታ ውስጥ ለምትገኙ ካህናት በሙሉ ተልዕኮዋችሁ የእግዚኣብሔር እና የእግዚኣብሔር ሕዝብ  ተልዕኮ እንደ ሆነ አድርጋችሁ አስቡት፣ ምንም እንኳን አስቸጋሪ በሚባል ሁኔታ ውስጥ የምትኖሩ ቢሆንም እንኳን የክህነት ምስጢር አገልግሎታችሁን መልካም ገጽታ ጽፋችሁ እለፉ” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ሐዘን

ቅዱስነታቸው ለመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ባስተላለፉት መልእክት ውስጥ ሐዘን፣ ምስጋና፣ ብርታት እና ውዳሴ በሚሉት አራት ጭብጦች ዙሪያ ላይ ያጠነጠነ እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “የሕዝቤን መከራ አይቻለሁ” (ዘጸዐት 3፡7) በሚል አርእስት የተቀመጠው ቀዳሚው ጭብጥ ሲሆን በእዚህ ጭብጥ ሥር በተለያዩ አጋጣሚዎች በቤተክርስቲያን አገልጋዮች አማካይነት በተፈጸሙ ያልተገቡ ተግባራት በሕዝቡ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን የሚገልጽ ሲሆን ምንም እንኳን አንዳንድ ካህናት ያልተገቡ ከተጠሩበት ጥሪ እና አገልግሎት ውጪ የሆኑ ተግባራትን በመፈጸም ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ ረገድ እንዲህ ዓይነት ተግባራትን የሚፈጽሙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ እና ቅጣት እየተጣለባቸው እንደ ሆነ ገልጸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ የተሰጣቸውን የክህናት አገልግሎት በታማኝነት እየካናወኑ የሚድገኙ ብዙ ካህናት እንደ ሚገኙ ማሰብ በራሱ ደግሞ ደስታን እንደ ሚፈጥርባቸው ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ምስጋና

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 28/2011 ዓ.ም ለመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ባስተላለፉት መልእክት በሁለተኛነት የተጠቀሰው ቃል “ምስጋና” የሚለው ቃል እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን “በጸሎቴ እያስታወስኋችሁ ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረብን አላቋረጥሁም” (ኤፌ 1፡16) በሚለው ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን በጻፈው መልእክቱ ዙሪያ ላይ የሚያጠነጥን ጭብጥ ሲሆን “መነፍሳዊ ጥሪ የእኛ የግል ምርጫ ከመሆኑ ባሻገር፣ እግዚኣብሔር ላቀረበልን ጥሪ በምስጋና መንፈስ የተሰጠ ምላሽ ነው” ብለዋል። በእዚህም የተነሳ ካህኑ መላውን ሕይወቱን ለእግዚኣብሔር ገልግሎት የዋለ እና ራሱን ብቁ አድርጎ በማቅረብ የተሰጠውን መንፈሳዊ አገልግሎት በተቻለው አቅም መፈጸም እንደ ሚገባው” የገለጹ ሲሆን አስቸጋሪ በሚሆን ሁኔታዎች ውስጥ በምትገቡበት ወቅት፣ ድካም በሚሰማችሁ ወቅት፣ በጠቃላይ ከፍተኛ የሆነ ፈተና በሚያጋጥማችሁ ወቅቶች ሁሉ ማዕደረ ታውስታችሁን በሚገባ በመመርመር ወደ ቀድሞ መስመራችሁ እንድትመለሱ ይረዳችሁ ዘንድ ለእርሱ እና ለእርሱ ሕዝብ የተገባ አገልግሎት እንድትሰጡ የጠራችሁን እግዚኣብሔርን ቃል በመስማት እና ድጋፉን በመሻት ወደ ቀድሞ ሁኔታችሁ በምስጋና መንፈስ መመለስ ይኖርባችኋል” ብለዋል።

ብርታት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 28/2011 ዓ.ም ለመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ባስተላለፉት መልእክት በሦስተኛ ደረጃ የተጠቀሰው ቃል “ብርታት” የሚለው ቃል እንደ ሆነ የተገልጸ ሲሆን “ልባችሁ ብርታት እንዲኖረው እሻለሁ” (ቆላስይስ 2፡2) በሚለው ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ በተጠቀሰው ጭብጥ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “የተጠራንበት እና የተሰጠን ተልዕኮ ከስቃይ ፣ ከሐዘን አልፎ ተርፎም ካለመግባባት መንፈስ ነፃ የሆነ ጥሪ አይደለም፣ ከዚህ ይልቅ ችግሮችን ፊት ለፊት እንድንጋፈጥ እና ጌታ እነዚህን ተግዳሮቶች እንዲለውጥ እና የበለጠ ለእርሱ የተገባን እንድሆን እንዲሁም ብርታቱን እንዲሰጠን የምንጠይቀበት ምስጢር ነው” ብለዋል።

የተሰጠንን ጥሪ በብቃት በመወጣት በብርታት ወደ ፊት መጓዝ እንችል ዘንድ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ያስፈልጉናል፣ “አንደኛው ከኢየሱስ ጋር ያለንን ግንኙነት አጠንክረን መቀጠል ነው” በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ከወንድሞቻችን ጋር መልካም የሚባል ቅርበት በመፍጠር በመንፈሳዊ ሕይወታችን ያግዙን ዘንድ፣ እንዲያጽናኑን እና እንዲያግዙን ከወንድሞቻችን ጋር ያለንን ቅርበት አጠንክረን መቀጠል ይገባናል ብለዋል። በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከእግዝጊኣብሔር ሕዝብ ጋር ያለንን ቅርበት በተቻለ መጠን ማጠናከር እንደ ሚገባን የገለጹት ቅዱስነታቸው “በፍጹም ከሕቦቻችሁ፣ ከማህበራችሁ እና ከወንድሞቻችሁ ራሳችሁን አታርቁ” ብለዋል።

ውዳሴ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 28/2011 ዓ.ም ለመላው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካህናት ባስተላለፉት መልእክት የተጠቀሙ አራተኛው እና የመጨረሻ ቃል “ውዳሴ” የሚለው ቃል ሲሆን “ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች” (ሉቃ 1፡46) በሚለው ከሉቃስ ወንጌል ላይ ከተወሰደው የማሪያም የውዳሴ መዝሙር ላይ ጭብጡ ያደረገ ሲሆን ማርያም መጪውን ጊዜ በተስፋ ተሞልታ ትጠባበቀው እንደ ነበረ ሁሉ እኛም ይህንን መንፈስ ከእርሷ ዘንድ ተምረን ሁሉንም ነገር በአዲስ መልክ ሊለውጠው በሚችለው በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን አጥብቀን በመቀጠል እግዚኣብሔር በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥምሙንን ተግዳሮቶች በሙሉ ወደ መልካም አጋጣሚ እንደ ሚቀይር በማመን ለእርሱ የውዳሴ መዝሙር በማቅረብ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል።

04 August 2019, 16:33