በሕንድ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ፍለጋ በሕንድ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ሰዎችን ፍለጋ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በተፈጥሮ አደጋ ጎዳት እየደርሰባቸው ለሚገኙ ሰዎች እንጸልይላቸው” አሉ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የፍልሰታ ማሪያም አመታዊ በዓል በዛሬው እለት ማለትም በነሐሴ 09/2011 ዓ.ም  በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉን ቀደስም ሲል መገለጻችን የሚታወስ ሲሆን ይህ የፍለሰት ማሪያም አመታዊ በዓለ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእርሳቸው መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉን መግለጻችን ይታወሳል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃይሌጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በእለቱ ካሰሙት ስብከት በመቀጠል ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በእለተ ሰንበት እኩለ ቀን ላይ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣከ ገብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አገራት በተለይም በኢሲያ አህጉር በተለያዩ ሥፍራዎች በዘነበው ከፍተኛ መጠን ባለው ዝናብ የተነሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከባድ ጉዳት በሰዎች እና በንብረት ላይ መደረሱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

በእዚህ የተፈጥሮ አደጋ ለተጉዱ እና ለተፈናቀሉ ሰዎች ሁሉ ጸሎቴን አቀርባለሁ፣ ለቤተሰቦቻቸውም ጌታ መጽናናትን እና ብርታትን እንዲሰጥ እማጸናለሁ ብለዋል። ዛሬ (ነሐሴ 09/2011 ዓ.ም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ) የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን አመታዊውን የፍልሰታ በዓል ለማክበር በፖላንድ አገር ወደ ሚገኘው የቼስቴኮቫ የእመቤታችን እጅግ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ብዙ መንፈሳዊ ነጋዲያን ወደ እዚያው ማቅናታቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው በእዚህም በዓል ላይ የቅድስት መንበር እና የፖላንድ መንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በአዲስ መልክ የጀመሩበት መቶኛ አመት እንደ ሚታሰብ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“እዚህ ለተገኛችሁ መንፈሳዊ ነጋዲያን፣ ምዕመናን እና የአገር ጎብኚዎች በሙሉ ሰላምታዬ ይደረሳችሁ” ያሉት ቅዱስነታቸው እንደ ተለመደው እና ዘወትር በመልእክታቸው ማብቂያ ላይ እንደ ሚያደርጉት ሐዋራይዊ ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ የእለቱ ዝግጅት መጠናቀቁን ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

15 August 2019, 08:42