ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሰው ልጅ እግሩን በጨረቃ ላይ በማሳረፍ እልሙን እውን አድርጉዋል” አሉ።

ርዕሰ ሊቅነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ሐምሌ 14/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልአክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ስማንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ባለፈው ሐምሌ 13/2011 ዓ.ም የዛሬ ሃምሳ ዓመት ገደማ ማለት ነው  አፖሎ 11 የተባለው መንኮራኩር ታሪካዊ የሆነ ጉዞ ካደረገ በኋላ የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በጨረቃ ላይ እግሩን ያሳረፈበት 50ኛ ዓመት ዕለት ታስቦ መዋሉን በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በእዚህ ተግባር የሰው ልጅ በጨረቃ ላይ እግሩን ለማሳረፍ የነበረውን አስደናቂ የሆነ ምኞት እውን ማደረጉን ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። ይህንን የሰውን ልጅ ታሪካዊ የሆነ ስኬት አሁንም አጠናክረን በመቀጠል ከእዚህ ስኬት ሁሉ በላይ የሆነውን የድሆችን እና የአቅመ ደካሞችን ሰብዓዊ መብት በማክበር በሰዎች መካከል ፍትህ እንዲሰፍን በማደረግ የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን ከጥፋት መታደግ ይኖርብናል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በእዚያ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በወቅቱ የተሰበሰቡትን ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው  እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘንጉ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ስምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

21 July 2019, 13:29