ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ሐምሌ 13/1961 ዓ. ም. አፖሎ 11 ወደ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጠፍር ጉዞ በተደረገበት ወቅት ቡራኬ በሰጡበት ወቅት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ሐምሌ 13/1961 ዓ. ም. አፖሎ 11 ወደ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጠፍር ጉዞ በተደረገበት ወቅት ቡራኬ በሰጡበት ወቅት  

የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን የጎበኘበት 50ኛ ዓመት ታስቦ ዋለ።

ልክ የዛሬ ሃምሳ ዓመት፣ ማለትም ሐምሌ 13/1961 ዓ. ም. አፖሎ 11 የተባለው ታሪካዊ የጨረቃ ላይ ጉብኝተ የተካሄደበት 50ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል። በውቅቱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ ስድስተኛ ወደ ጨረቃ ለተጓዙት የመጀመሪያዎቹ የጠፈር ተመራማሪዎች መልካም ጉዞን በመመኘት ቡራኬያቸውን መላካቸው ይታወሳል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኮንን-ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ የዓለማችን ሰዎች፣ ሴቶች ወንዶች እና ሕጻናት ጋር ሆነው ሐምሌ 13/1961 ዓ. ም. የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን ለመርገጥ ያደረገውን የጠፈር ጉዞን መከታተላቸው ይታወሳል። ከ50 ዓመት በኋላ ዛሬ የሰው ልጅ በድጋሚ ወደ ጨረቃ ላይ በመጓዝ፣ የአፖሎ 11 ቡድን ያወረሰውን የላቀ ውጤት በድጋሚ ማስመስገብ እንዳለበት ሳይንትስቶች መስማማታቸው ታውቋል።  

ወደ ጨረቃ ላይ የተደረገውን ጉዞ አስፈላጊነት የተረዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ፣ ለሦስቱ የጠፈር ተመራማሪዎች ቡራኬአቸውን በመላክ የመጀመሪያው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ከዚያም በመቀጠል በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለነበሩት ለርቻርድ ኒክሰን የደስታ መግለጫ የቴሌግራም መልዕክት መላካቸውም ይታወሳል።

 “የሰው ልጅ ጨረቃን መርገጡ የእግዚአብሔር እጅ ድንቅ ሥራ ታላቅነት የተገለጸበት ነው።” በማለት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በወቅቱ ለጠፈርተኞቹ አድናቆታቸውን፣ ሰላምታቸውን እና ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ልከው እንደነበር የቫቲካን የዜና አገልግሎት ባልደረባ ቬሮኒካ ስካሪስብሪክ አስታውሳለች። የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ መውጣት መቻሉ፣ የእግዚአብሔር ታላቅነት እና ሥራዎቹም ገሃድ የሆነበት መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ መናገራቸው ይታወሳል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ጨረቃን ብርሃን እንደሚሰጥ ኩራዝ በማስመሰል በተናገሩት መልዕክታቸው ጨለማችንን የምታበራ፣ ሕያው የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ናት ማለታቸው ይታወሳል።

ጠፈርተኞቹ የተጓዙባት መንኮራኩር ወደ ጨረቃ በተቃረበችበት ወቅት፣ ምን ይከሰት ይሆናል በማለት የዓለም ሕዝብ በቴሌቪዥን ይከታተል እንደነበር እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛም በካስቴል ጋንዶልፎ በተባለ የበጋ ወቅት መኖሪያ ቤታቸው ሆነው የተከታተሉ መሆናቸው  ይታወሳል። ወደ ጨረቃ ላይ ከተጓዙት ጠፈርተኞች መካከል አንዱ የሆነው ነይል አርምስትሮንግ ለመጀመሪያ ጊዜ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ጳውሎስ ስድስተኛ የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ መግለጻቸው ሲታወስ፣ ለጠፈርተኞቹ በላኩት መልዕክታቸው እንደገለጹት ከመላው ካቶሊካዊ ማሕበረሰብ ጋር ሆነው ደስታቸውን በመግለጽ በጸሎት ማስታወሳቸውን የቫቲካን የዜና አገልግሎት ባልደረባ ቬሮኒካ ስካሪስብሪክ አስታውቃለች።

ወደ ጨረቃ ላይ ለተደረገው ጉዞ ልዩ ፍላጎት ያደረባቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ጳውሎስ 6ኛ ጠቅላላ ጉዞን            በቫቲካን በተተከለው ቴሌስኮፕ የተከታተሉት መሆናቸው ይታወሳል። ሰላማዊ ጉዞው ከተጠናቀቀ በኋላ ባሰሙት የመጀመሪያ ንግግራቸውም እንደገለጹት እግዚአብሔር በቸርነቱ ለሰው ልጅ አዲስ የታሪክ ምዕራፍን ክፍቷል ብለው በሚቀጥለው ጉዞ ወደ ጨረቃ ላይ የሚወሰድ ሜዳሊያን ለጠፈርተኞቹ ማበርከታቸው ይታወሳል። በሜዳሊያውም ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰደ “አምላካችን ሆይ: ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ታላቅ ነው” የሚል ጥቅስ የተጻፈበት መሆኑ ታውቋል።      

20 July 2019, 12:37