ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቤተክርስቲያን ለማገልግል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሕብረት መፍጠር ይገባል” አሉ።

የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ሰኔ 02/2011 ዓ.ም መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በሐዋርያቱ ላይ የወረደበት የጴራቂሊጦስ በዓል እንደ ሚከበር ይታወቃል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አገልግሎት የሚሰጡ ምዕመናን ዛሬ ሰኔ 01/2011 ዓ. ረፋዱ ላይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሕብረት መፍጠር ይገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አገልግሎት የሚሰጡ ምዕመናን ዛሬ ሰኔ 01/2011 ዓ. ረፋዱ ላይ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ በተገናኙበት ወቅት ቅዱስነታቸው ያደረጉትን ንግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

አዎን ኢየሱስ ሕያው ነው! የጴንጤቆስጤ በዓል ማክበር ስንጀምር የዛሬ 52 አመት በአዲስ መልክ የጀመራችሁትን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ጉዞ ያስታውሰናል። በእግዚኣብሔር ፈቃድ አማካይነት በቤተክርስቲያን ውስጥ እያደገ የመጣው የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ ቅዱስ ጳውሎስ 6ኛ እንደ ሚሉት “ለቤተክርስቲያን መላካም አጋጣሚን ከፍቶላታል”።

ዛሬ በመላው ቤተክርስቲያን ስም የአለም አቀፍ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አገልግሎት አባላት እና የካቶሊክ የወንድማማችነት ማኅበር ለባለፉት 30 ዓመታት ላከናወናችሁት ተልዕኮ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በጥረታችሁ መንገዱ እንዲበራ አድርጋችኋል፣ በታማኝነታችሁ ደግሞ የአለም አቀፍ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አገልግሎት እውን እንዲሆን አድርጋችኋል። ለእዚህ ተግባራችሁ እጅግ አመሰግናለሁ!

ይህን ልዩ አዲስ አገልግሎት ወደ በተቀናጀ መልኩ እንዲሄድ ያደረጉትን አራት አካላት ላመሰግናቸው እወዳለሁ። የምዕመናን፣ የቤተሰብ እና ሕይወትን የሚመለከተውን ጳጳሳዊ ተቋም እና እንዲሁም እናነትን በተለያየ ሁኔታ የገዙዋችሁን ካርዲናል ፋሬሌን ለማምሰገን እወዳለሁ።

ዛሬ የዚህ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ጀምሩዋል። የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ተአድሶ አባላት ኅበረት በመፍጠር ይህንን ኅበረታቸውን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በመግለጽ ለመላው ቤተክርስቲን በጎ አገልግሎት እያዋሉት መሆኑ አዲስ ምዕራፍ ከፍቱዋል። እያንዳንዳቸው ከአንድ መንፈስ ቅዱስ በመወለዳቸው የተነሳ አንድ ዓይነት እና እኩል በመሆናቸው የተነሳ ትልቅ ይሁን ትንሽ፣ ወጣት ይሁን ሽማግሌ በዓለም አቀፍ ወይም በአከባቢ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሳታፊ በመሆን በግል ከሚያደርጉት አገልግሎቶች በተሻለ መልኩ በጋር የሚደረጉ ተግባሮች አመርቂ ውጤት እንደ ሚያስገኙ በማሳየት ላይ ናቸው።

አዲስ፣ ልዩ እና በኅብረት የሚደረግ አገልግሎት

አዲስ! በመጀመሪያ ደረጃ አዲስ ነገር ስለሚመጣው ለውጥ እርግጠኛ ያለመሆን ስጋት አለ። አዲስ ስለሚከሰት ነገር በተመለከተ ያለው ፍርሃት ሰብዓዊ የሆነ ፍርሃት ነው፣ ነገር ግን የእዚህ ዓይነቱ ፍርሃት አንድ መንፈሳዊ በሆነ ሰው ላይ መከሰት የለበትም። “አይዙዋችሁ እኔ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርገዋለሁ” (ራእይ 21፡5) በማለት ጌታ ተናግሮናል። እግዚአብሄር የሚሰጣቸው አዳዲስ ነገሮች የሚመነጩት ከእርሱ አፍቃሪ ከሆነ ልብ ውስጥ ነው። ምንጊዜም ቢሆን "እኛ በእዚህ መልኩ በመልካም ሁኔታ እየኖርን ነው፣ ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ እየሄደ ነው፣ ለምን ለውጥ አሰፈለገ? ነገሮችን እንደ ነበሩ እንተዋቸው፣ ምን እንደምናደርግ እናውቃለን” እነዚህን የመሳሰሉ ፈተናዎች ሁልጊዜም ያጋጥሙናል። እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከመንፈስ ቅዱስ አይመጣም። ምናልባት ከዓለም መንፈስ እንጂ የእዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ከመንፈስ ቅዱስ አይመነጭም። የእዚህን ዓይነት ስህተት አትፈጽሙ። “ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” የሚለው ሰው ሳይሆን ጌታ ነው።

ልዩ! አገልግሎት ማለት በዓለም ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ተነሳሽነት አገልግሎት በማከናውን ላይ የሚገኙትን ሰዎች ወይም ቡድኖች መርዳት ማለት ነው። አንዱን አገልግሎ ሌላውን መተው ማለት አይደለም።

አገልግሎት። ማስተዳደር ሳይሆን አገልግሎት ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁላችንም እንደምናውቀው ማስተዳደር ማለት ማገልገል ማለት ነው፣ ነገር ግን ማስተዳደር የእናንተ ተግባር አይደለም። የተለያዩ ፍላጎቶችን እንድታሟሉ እና የሚደረጉ ጉዞዎን በተቻለ መጠን የተሻለ ለማድረግ እንድታግዙ ነው የተጠራችሁት።

ኅብረት። በአንድ ልብ ሆነን ወደ እግዚኣብሔር በመመለስ በልዩነታችን መካከል ያለውን ኅብረት በመግለጽ፣ መንፈስ ቅዱስ ለባልፉት 52 አመታት የሰጣችሁን የተትረፈረፈ ስጦታ በመጠቀም ምስክርነት መስጠት ይኖርባችኋል። ሁሉም ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ሆነው መኖር ይችላሉ ዘንድ ነብዩ ኢሳያስ እንደ ሚለው “የድንኳንህን ቦታ አስፋ” (ኢሳ. 54፡ 2) ይላል ማስፋትም ይገባል። አንድ አምላክና እና አንድ አባት ብቻ፣ አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አንድ የሕይወት መንፈስ ብቻ ያለው አንድ ቤተሰብ መመስረት የገባል። አንዱ ከሌላው ይልቅ አስፈላጊ ነኝ ብሎ የማያምንበት፣ እኔ ከሁሉም በእድሜ የባልይ ነኝ ስለዚህ ቦታ የገባኛል የማይልበት፣ በእውቀት ወይም በችሎታ ከሁሉም የተሻልኩኝ ነኝ ብሎ የማያምንበት ሁላችንም የአንዱ የተወዳጁ አባታችን ልጆችን ነን ብለን የምናምንበትን አንድ ቤተሰብ መገንባት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የቅዱስ ጳውሎስ የአካልን ምሳሌ በመጠቀም ሁሉም የአካል ክፍሎች እኩል መሆናቸውን በመግለጽ አንዱ ከአንዱ እንደ ማይነጣጠል ምሳሌ ሰጥቶናል (1ቆሮ 12፡12-26)።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኅበረት ይፈጠር ዘንድ አገልግሎት በመስጠት ላይ የምትገኙ ወጣቶች እዚህ እንዳልችሁ አውቃለሁ። በእዚህ በጣም ተደስቻለሁ። ወጣቶች የአሁኑ እና የሚመጣው ዘመን የቤተክርስቲያን ተስፋዎች ናችሁ። እዚህ የተገኛችሁ ተሳታፊዎች ለወጣቶች እንዲህ ያለ ከፍተኛ የሥራ ድርሻ ያለውን ቦታ በመስጠታችሁ እና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እድል ስለተሰጣቸው አመሰግናለሁ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን ከእናንተ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዓለም አቀፍ የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አገልግሎት አባላት የምንጠብቀው ነገር ምንድነው? ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ እሰጣችኋለሁ፡

Ø  በቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚገኙ ሰዎች ሁሉ ጋር የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት እንድታጋሩ። እናንተ የተቀበላችሁት ጸጋ ነውና ለሌሎች አካፍሉት!

Ø  የክርስቶስ አካላት በኅበረት የሚኖሩባትን ቤተክርስቲያንን፣ አማኝ የሆነውን ማኅበረሰብ በክርስቶስ ኢየሱስ አምካይነት እንድታገለግሉ።

Ø  ድሆችን እና በከፍተኛ የሆነ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች አካላዊ ወይም መንፈሳዊን አገልግሎት ማድረግ።

በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ፣ በክርስቶስ አካል ውስጥ አንድነት መፍጠር እና ድሆችን ማገልገል የሚሉት እነዚህ ሦስት ነገሮች በጥምቀት አማካይነት ሁላችንም ለመላው ዓለም የቅዱስ ወንጌል አገልግሎት እንድንሰጥ የተጠራንበት የምስክርነት ቅርጾች ናቸው። ስብከተ ወንጌልን ማደረግ ማለት ሰዎች እምነታቸውን በመቀየር እኛ ወደ ምናምነው እመንት እዲቀየሩ ማደረግ ማለት ሳይሆን ነገር ግን ፍቅርን መመስከር ማለት ነው። “እንዴት እንደ ሚዋደዱ ተመልከቱ”። ስብከተ ወንጌልን ማደረግ ማለት ፍቅርን መመስከር ማለት ነው፣ እግዚኣብሔር ለእኛ የሰጠንን ፍቅር ከሌሎች ጋር መጋርት ማለት ነው። ስብከተ ወንጌልን በተቀላጠፈ መልኩ ለማካሄድ የሚረዱ ቢሮዎች፣ እና በጥንቃቄ የተዘጋጁ እቅዶችን በማዘጋጀት ተፈጻሚ ለማደረግ እንጥር ይሆናል፣ ነገር ግን ያለ ፍቅር ሁሉም ውጤት አልባ ነው። “እንዴት እንደ ሚዋደዱ ተመልከቱ”።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ታድሶ አባላት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመታገዝ የፍቅር ምስክሮች እንድትሆን እማጸናለሁ! አመሰግናለሁ።

08 June 2019, 16:42