ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በናፖሊ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በናፖሊ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በሕዝቦች መካከል ሰላም ይሰፍን ዘንድ ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል” አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሰኔ 14/2011 ዓ.ም የናፖሊን ከተማ መጎብኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚያው በናፖሊ በላቲን ቋንቋ “Veritatis Gaudium” (በእውነት የሚገኝ ደስታ) በሚል አርእስት እርሳቸው እ.አ.አ በጥር 29/2018 ዓ.ም ያፋ ባደረጉት ሐዋሪያዊ ሕግ-ጋት ላይ በናፖሊ የሚገኘው የነገረ-መለኮት ትምህርት መስጫ ጳጳሳዊ ዩኒቬርሲቲ ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ቅዱስነታቸው መሳተፋቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በናፖሊ በሚያደርጉት የአንድ ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ላይ ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል በገለጽነው መሰረት በእዚያው በሚካሄደው ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው በላቲን ቋንቋ “Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) በሚል አርእስት ከተጻፈው ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት በኋላ በሜድትራኒያን ባሕር አከባቢ በሚኖሩ አገራት የነገረ-መለኮት ትምህርት አውድ ሲታይ” በሚል አርእስት ላይ ተመርኩዘው ንግግር ማደረጋቸው ተገልጹዋል።

በወቅቱ ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት አጽኖት ሰጥተው እንደ ተናገሩት “በሜድትራኒያን አከባቢ በሚገኙ አገራት ሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ውይይት ማደረግ እና ተቀብሎ ማሰተናገድ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ይህ በናፖሊ ቅዱስነታቸው የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአሁኑ ወቅት በተለይም በአውሮፓ አህጉር በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ የሚገኘው የስደተኞ ፍልሰት ላይ፣ በባህሎች መካከል ስላለው ልዩነት እና በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶችን በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጡ የተላያዩ ምሁራን ተጋብዝው ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህ ውይይት ላይ ቅዱስነታቸው ተሳትፈው ንግግር ማደርጋቸው ተገልጹዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከእዚህ ቀደም ከጥር 23/2011 እስከ ጥር 26/2011 ዓ.ም 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት “ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል የተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡዳቢ ማደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ጋር ስብሰባ ማደርጋቸው የሚታወስ ነው።

ይህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለመጀመሪያ ጊዜ የእስልምና እምነት መነሻ በሆነው በአረብ ባህረ-ሰላጤ ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት እርሳቸው በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታይ ሕዝቦች መካከል ያለውን የጋራ የሆነ የእምነት እውቀት እና በተጨማሪም በሁለቱ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የነበሩ ግንኙነቶች እና ውይይቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ፣ ልዩነቶችን ለማጥራት ቁርጠኛ በመሆን፣ እነዚህ ጉዳዮች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ የመሸጋገሪያ ድልድይ የሚገነባ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ነበረ መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች እርስ በእርሳቸው እንዲተማመኑ በማድረግ ወንድማማቾች መሆናቸውን እንዲገነዘቡ የሚረዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አብዛኛው ሕዝባቸው የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ አገራት ውስጥ የሚያደርጓቸው ጉብኝቶች እና ልዩ ልዩ ስብሰባዎች በመላው ዓለም በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ ሕዝቦች እና ለመላው ዓለም ሳይቀር የሰባዊ ፍጡር ሊኖረው ስለሚገባው ፍቅር ትምህርት የሰጠ አጋጣሚ ነበር።

እ.አ.አ በሚያዚያ ወር 2017 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግብፅ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማደርጋቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ የአልዓዛር ታላቁ መስጊድ እና ዮኒቬርሲቲ ታላቁ ኢማም ከሆኑት አህመድ ሙሀመድ ኣል ታይብ ጋር በተገናኙበት ወቅት የሚከተለውን ንግግር አድረገው ነበር “የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንደመሆናችን መጠን ማነኛውንም ዓይነት ቅድስናን የሚያጎድፉ ብጥብጦችን እና ግጭቶችን፣ የኋጢኣት ሁሉ መንስሄ የሆነውን የራስ ወዳድነት መንፈስን በማውገዝ እውነተኛ የሆኑ የውይይት መድረኮችን መክፈት ይኖርብናል። በሰው ልጆች ክብር እና ሰብአዊ መብት ላይ የተፈጸሙ ጥሰቶችን ለማውገዝ፣ በሐይማኖት ተቋማት ውስጥ ጥላቻዎችን በመፍጠር፣ እነዚህን ጥላቻዎች በሐይማኖትና በእግዚኣብሔር  ስም እውነተኛ እንደሆኑ አስመስሎ ለማቅረብ የሚደርጉትን ጥረቶች በሙሉ ለማጋለጥ እና እነዚህን ጉዳዮች የእውነተኛው አምላክ ፍላጎቶች ሳይሆኑ ነገር ግን የጣዖት አምላክ ፍላጎቶች መሆናቸውን በማሳወቅ፣ የእውነተኛው እግዚኣብሔር ስም ቅዱስ፣ እርሱ የሰላም አምላክ፣ እግዚኣብሔር ሰላም መሆኑን በድፍረት መመስከር ይኖርብናል። ስለዚህ የተቀደሰ ነገር የሚባለው ሰላም ብቻ ነው፣ ስለሆነም በእግዚአብሔር ስም ምንም ዓይነት ግፍ፣ ብጥብጥ፣ ግጭት ሊፈጸም አይችልም፣ ምክንያቱም በእግዚኣብሔር ስም የሚፈጸሙ ግፎች ቅዱሱን የእግዚኣብሔር ስም ያረክሱታልና” በማለት መናገራቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በጥር 29/2018 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ “Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ ተቋማት ውስጥ ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን በተለይም ደግሞ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥር በሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች እና መሰል ተቋማት ውስጥ ሥራ ላይ እየዋለ የሚገኝ ሕግ እንደ ሆነ ይታወቃል። ሕግ-ጋቱ የእግዚአብሔርን ታላቅነት እና እውነትን በተመለከተ ሰፊ የሆነ መልእክት የያዘ ሲሆን በተጨማሪም በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ተቋማት ውስጥ በተለይም ደግሞ በትምህርት መስጫ ተቋማት ውስጥ ለስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሊደረግ ሰለሚገባው እንክብካቤ፣ በሐይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት በማድረግ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲፈጠር ማድረግ ይገባል የሚሉ ሐሳቦች የተንጸባረቁበት ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዛሬ ሰኔ 14/2011 ዓ.ም በናፖሊ የሚገኘው የነገረ-መለኮት ትምህርት መስጫ ጳጳሳዊ ዩኒቬርሲቲ ባዘጋጀው ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተው ያደረጉትን ንግግር የመጀመሪያውን ክፍል በዛሬው እለት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን ተከታተሉን።

የተከበራችሁ ካርዲናሎች

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ጳጳሳት እና ካህናት

የተወደዳችሁ መምህራን እና ተማሪዎች

ዛሬ “Veritatis Gaudium  (በእውነት የሚገኝ ደስታ) የተሰኘው ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት ከተጻፈ በኋላ በሜድትራኒያን ባህር አከባቢ በሚገኙ አገራት አውድ መሰረት ያለው ነገረ መለኮት” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘቴ ተደስቻለሁ። ለእዚህ ስብሰባ በግል መልእክታቸው ለእዚህ ስብሰባ አስተንትኖ የሚሆን መልዕክት ለላኩልኝ ለፓሪያርክ በርቶሎሜውስ ከልብ የመነጨ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።

የሜዲትራንያን ባሕር ሁልጊዜ የመተላለፊያ፣ የመለዋወጫ፣ እና አንዳንዴ ደግሞ የግጭት ስፍራ በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ዛሬ ይህ ቦታ በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳል። እነዚህ ጥያቄዎች ከእዚህ ቀደም በአቡዳቢ በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ ባነሳናቸው ጥያቄዎች መተርጎም እንችላለን-ይህም የአንድ ቤተሰብ አባል የሆነውን የሰው ልጅ አንዱ ሌላውን እንዴት መንከባከብ ይችላል? የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደረገናል። በእውነተኛ ወንድማማችነት መንፈስ ጋር በተገናኘ መልኩ ተቻችሎ እና ሰላማዊ አንድነት ጠብቆ እንዴት መኖር ይቻላል? ከእኛ የተለየ ባሕል፣ ሐይማኖት እና የሕይወት ልምድ ያላቸውን ሰዎች በማኅበርሰስባችን ውስጥ ሊገቡ አይገባም የሚለውን አስተሳሰብ እንዴት ማስወገድ እንችላለን? ሐይማኖት የሚለያዩንን ግንቦች የምንገነባበት ነገር ሳይሆን የወንድማማችነት መንፈስን የምናጠናክርበት መሳሪያ ማደረግ የምንችለው እንዴት ነው? እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች በበርካታ ደረጃዎች መተርጎም ይጠይቃል፣ እናም በትህትና ማዳመጥን፣ ጥናት ማደረግን፣ የነፃነትን፣ የሰላም፣ የወንድማማችነትና የፍትህ ስርዓት እና የወንድማማችነት መንፈስ ማዳበርን ይጠይቃል።

ተቀብሎ የማሳተናገድ እና የውይይት ነገረ-መለኮት

በዚህ ስብሰባ ወቅት በመጀመሪያ በሜዲትራኒያን አካባቢ የነበሩትን ግጭቶች እና ችግሮች መርምራችሁ እና ከዚያም ምርጥ የሆኑ መፍትሄዎች ላይ ተወያይታችኋል። በዚህ ረገድ የምትኖሩበትን እና የምትሰሩበትን አውድ በተገቢው ሁኔታ ለመፍታት የሚችል የነገረ-መለኮት አስተምህሮ የተኛው ነው? ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል። እኔን እንደ ሚመስለኝ በተለይ በዚህ ዐውደ ዙሪያ ላይ ተቀባይነት ያለው የነገረ መለኮት አስተምህሮ የትኛው ነው ተብሎ ቢጠየቅ፣ ተቀብሎ የማስተናገድ የነገረ-መለኮት አስተምህሮ ነው፣ ይህም እውነተኛ የሆነ ውይይት ማደረግን፣ ከማኅበረሰቡ እና ከሲቪል ተቋማት ጋር፣ በዩኒቨርሲቲና በምርምር ማዕከላት፣ ከሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር፣ ከሁሉም ሰዎች ጋር፣ እንዲሁም በጎ ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር፣ በመወያየት ሁሉን አካታች የሆነ በሰላም የተሞላ የወንድማማችነት መንፈስ ያለው ማኅበረሰብ በመገንባት ለፍጥረታት ሁሉ ጥበቃ መድረግ የሚለው ነው።

Veritatis Gaudium (በእውነት የሚገኝ ደስታ) በተሰኘው ሐዋርያዊ ሕግ-ጋት በመግቢያው ላይ እንደ ተጠቀሰው በማነኛውም ጥናት ውስጥ ውይይት ማደረግ አስፈላጊ እንደ ሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም ቤተክርስቲያን በጉዞዋ ውስጥ ሁሌም ቢሆን በላቀ ሁኔታ በስብከተ ወንጌል አገልግሎቷ ውስጥ የውይይት መንፈስ ማዕከል ሊሆን ይገባል በማለት በስፋት ተገልጹዋል። ከተለያዩ ባህሎች እና የእመንት ተቋማት ጋር የሚደረገው ውይይት  ቤተክርስቲያን ስለ ኢየሱስ መልካም ዜና እና ቅዱስ ወንጌል ፍቅርን ተጨባጭ በሆነ መልኩ በመግለጽ ኢየሱስ የሕግ አስተምህሮዎችን፣ የነብያትን ራእዮች እና የአባቱን ፈቃድ ጠቅለል አድርጎ እንደ ሰበከ እና እንደ ግለጸ ሁሉ ቤተክርስቲያን በእዚሁ መልኩ መጓዝ ይኖርባታል። ውይይት ሁሌም ውሳኔን በማስተዋል ጥበብ በተሞላ መልኩ ለማደረግ እና ለእያንዳንዱ ሰው የፍቅር ቃላት የማስተዋወቂያ ዓይነተኛው ዘዴ ነው። ይህንን ቃል በመስማት ብቻ እና በሚያስተላልፈው የኢየሱስ የፍቅር ስሜት ውስጥ ለመግባት የሚቻለው። በዚህ ሁኔታ ውይይት ማደረግ ማለት ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር አብ የሰጠንን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የሰጠንን ፍቅር መቀበል ማለት ነው።

“በማስተዋል ጥበብ የሚደረግ መንፈሳዊ የሆነ ውሳኔ ሰዎችን፣ ሕልውናን፣ ሥነ ልቦናዊን፣ ማህበራዊና ሥነ-ምግባራዊ ሳይንስ የሚያበረክተውን አስተዋጾ ባገለለ መልኩ ሊደረግ እንደ ማይገባ በድጋሚ ለመናገር እፈልጋለሁ። በተጨማሪም የቤተክርስቲያን ጥበባዊ መመዘኛዎች እንዲሁ በቂ አይደሉም። በማስተማል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማደረግ የጸጋ ስጦታ መሆኑን ማስታወስ ይኖርብናል። በማስተማል ጥበብ የሚደረግ ውሳኔ በአጠቃላይ ሲታይ ወደማይሞተው የሕይወት ምንጭ ይመራል፣ ያም ማለት “እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን” (ዩሐ 17፡3) እንዲያውቁት ያደርጋል ማለት ነው።

የሥነ-መለኮት ትምህርት ቤቶች በተለመደው የማስተዋል ዘዴ እና ውይይት ለፈጠር በሚያስችል መልኩ በመሥራት መላካም የሆነ መንፈሳዊ እና አእምሮአዊ ሁኔታዎች ለመፍጠር በሚያስችል ዘዴዎች መታደስ ይኖርባቸዋል። ችግሮችን መፍታት እና የጋራ መፍትሄዎችን ማምጣት በሚያስችል መልኩ ውይይት ይደረግ ዘንድ መንገዶችን ማመቻቸት ይኖርባቸዋል። ሕያው የሆነውን የኢየሱስን ፋሲካን ማሳየት በሚችል መልኩ በሚደረግ ውይይቶች መመዘኛዎችን ማካተት የሚችል፣ ከእውነታው ጋር በሚዛመድ መልኩ በፍጥረት እና በታሪክ ውስጥ የሚገኙ ሁኔታዎችን በመመልከት፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ ውይይት ይደረግ ዘንድ የበኩላቸውን ጥረት ማደረግ ይኖርባቸዋል። ይህም ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጉዞ፣ ወደ መስቀሉ እንዲሁም ወደ ትንሣኤ እና ወደ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚወስደው ምሥጢራዊ ትርጓሜ ነው። ይህን አመክኒዮ ማስታወስ የፋስካ ምስጢር በማመላከት የእግዚአብሔርን የፍቅር ምሥጢር በማብራራት ታሪካዊ እና የፍጥረታት እውነታ እንዴት እንደ መጣ ለመጠየቅ ወሳኝ ነው። በእየሱስ ታሪክ ውስጥ - በእያንዳንዱ ጊዜ እና ሁኔታ ውስጥ፣ በታላቅ ፍቅር የተሞላው እና ከሁሉም ክፉ ነገሮች በላይ የሆነው የእግዚኣብሔር ፍቅር መግለጫ ነው።

ሁለቱም እንቅስቃሴዎች አስፈላጊ እና ውሳኝ ናቸው፣ የሰውን አጠቃላይ ፍጥረት ከግምት ባስገባ መልኩ፣ በማዳመጥ እና በማስተዋል ከታች ወደ ላይ መወያየት ይችላላ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከላይ ወደ ታች “ላይ” ማለት ከእዛ ኢየሱስ ከነበረበት መስቀል ላይ - የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክቶችን በታሪክ ውስጥ ለመለየት እና በትንቢታዊ መልኩ የእግዚአብሄርን መንግስት ምልክቶች ለመለየት፣ ነፍስና የሰው ታሪክን የሚያበላሹ ነገሮችን ለመለየት የሚያስችል ውይይት። ይህ እሳቤ-በቋሚነት ተነሳሽነትን የሚፈጥር - እያንዳንዱን ሰብዓዊ ፍጡር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ እና የክርስትና እና የፋሲካ ብርሃን እውነታዎችን በማንፀባረቅ እና ከሙታን በተነሳው የክርስቶስ መንፈስ ኃይል ተሞልተን እዚህ እና አሁን የሚታዩትን ሁኔታዎችን ለመፍታት የሚያስችለን ዘዴ ነው።

ማነኛውም ውይይት መቀጠል የሚገባው የመገናኛ ዘዴዎችን ለመፍጠር፣ አካባቢያዊ ቅርርቦሽን ለመፍጠር፣ ሕዝቦችን እና ግለሰቦችን ማቀረረብ በሚችል መልኩ መደረግ ይኖርበታል። ወደዚያ በመግባት - የሕዝብን ነፍስ "መንፈሳዊ በሆነ ብርሃን በመሙላት" በዓለም ውስጥ የመወያየት መንፈስ እንዲዳብር በማደረግ የእግዚኣብሔርን መንግሥት የሚያውጀውን ቅዱስ ወንጌል በመስበክ የጎለመሰ የወንድማማችነት መንፈስ እንዲጠናከር በማደረግ የተጠናከረ እና ሁሉን ያካተተ ማኅበረሰብ መፍጠር ይችላል። ውይይት እና ቅዱስ ወንጌል ማወጅ ስልታዊ በሆነ መልኩ በአዚዚው በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ሕይወት ውስጥ ተከስተው ያለፉ ነገሮች ሲሆኑ እርሱ ይህንን እውን ሊያደርግ የቻለው በቅዱስ ወንጌል ምርህ ላይ ተንተርሶ ነበር፣ በእዚህም ተግባሩ በሜድትራኒያን ባሕር አከባቢ በሚኖሩ አገራት ውስጥ መቀራረብ እንዲፈጠር አደረገ። ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ይህን ገቢራዊ ያደርገው ደግሞ በቀላሉ እንደ አንድ ክርስቲያን በመኖር ነበር አንደኛው መንገድ እርስ በእርስ አለመግባባትን ወይም ጥልን የሚፈጥሩ ነገሮችን በማስወገድ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል  ለእግዚአብሔር ፍቅርና ለሰው ልጆች ሁሉ ታዛገዥ በመሆን ነበር"። ከዚያም በመቀጠል ከሙታን ወደ ተነሣው ጌታ እና እርሱ ወደ ሚሰጠው የሰላም መንፈስ በመከተል የክርስቲያን እምነት በኢየሱስ አማካይነት የተገለጸው የእግዚኣብሔር ፍቅር ለሁሉም የሰው ልጆች የተሰጠ ፍቅር መሆኑን አብስሩዋል።

ይህ የመንፈስ ድነት የሚያመለክተው አሰገዳጅ በሆነ መልኩ አለመስበክን እና ሰዎች እምነታቸውን እንዲቀይሩ ባለማስገደድ፣ በተጨማሪም በጣም አሰገዳጅ በሆነ መልኩ በግድ ቅዱስ ወንጌል እንዲቀበሉ ማደረግም አያካትትም። ሰዎችን፣ ባሕላቸውን፣ ታሪካቸውን፣ የተለያዩ ሐይማኖታዊ ልምዶቻቸውን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ  ከውስጥ በመነጨ መልኩ ወደ ውይይት መንገድ የሚመራ አንድ ዜዴ ሲሆን በቅዱስ ወንጌል ላይ መሰረቱን ባደረገ መልኩ ይህንን ምስክረነት ሕይወቱን በመስዋዕትነት እስከ ማቅረብ ድረስ በመዝለቅ ከእዚህ ቀደም የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ወንድሞቻችን በክርስቶስ ጸጋ ተሞልተው፣ በትህትና እና በየዋህነት መንፈስ ለእርሱ ታማኝ ሆነው በከነፈራቸው ላይ የኢየሱስ ስም እየጠሩ እና በልባቸው ደግሞ በምሕረት ተሞልተው ከእዚህ ዓለም እንዳለፉት ቅዱሳን ነበር እርሱም ተግባሩን የፈጸመው። በእዚህ ረገድ ማርቲን ሉተር ኪንግ ይህንን በተመለከተ የሰላም መሳሪያዎች ብሎ የተናግረውን ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ።

21 June 2019, 16:08