ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ድሆችም የሰው ልጆች በመሆናቸው የተነሳ የክርስቶስ መልክ መገለጫዎች ናቸው”

ከግንቦት 15-20/2011 ዓ.ም ደረስ “አንድ ቤተሰብ፣ እንድ የጋራ መኖሪያ” በሚል መሪ ቃል ካሪታስ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅ 21ኛውን አጠቃላይ ጉባሄ በሮም ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ ካሪታስ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅ 21ኛው አጠቃላይ ጉባሄ ተሳታፊዎች ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልእክት ሶስት ቁልፍ ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ መሰረቱን ያደርገ መልእክት እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሰረት ስለ በጎ አድራጎት ተግባር፣ ሁለንተናዊ ልማት እና ኅብረት በሚሉት ጭብጦች ዙሪያ ላይ መሰረቱን ያደርገ መልእክት እንደ ነበረ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከባለፈው ከግንቦት 15/2011 ዓ.ም ጀመሮ “አንድ ቤተሰብ፣ እንድ የጋራ መኖሪያ” በሚል መሪ ቃል ካሪታስ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅ 21ኛውን አጠቃላይ ጉባሄ በሮም ከተማ እያካሄደ እንደ ሚገኝ ቀደም ሲል መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዚህ ጉባሄ ላይ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ 300 ተሳታፊዎች ጉባሄውን በመታደም ላይ እንደ ሚገኙ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ጉባሄ የሚካሄደው በአራት አመት አንዴ የድርጅቱን የሥራ ሂደት እና ፖሊሲዎችን ለመገምገም እና በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ድርጅቱን ወደ ፊት እንዲራመድ የሚያስችሉትን ስልታዊ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት ታስቦ የሚደረግ ጉባሄ ነው።

በጎ አድራጎት

ካሪታስ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅ ተወካዮች ዛሬ ግንቦት 19/2011 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት እንደ ገለጹት የበጎ አድራጎት ተግባር “ሕሊናች እንዳይወቅሰን በማሰብ የምናከናውነው ተግባር” ብቻ እንዳልሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተቃራኒው የበጎ አድራጎት ተገባር ሁሉ ምንጭ የሆነው እግዚኣብሔር ራሱ መሆኑን በመገንዘብ በዚሁ መንፈስ ልናከናውነው የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል። ቤተክርስትያን የምታደርገውን የበጎ አድራጎት ተግባር እንደ አገልግሎት ከቆጠርነው ቤተክርስቲያን ሰብዓዊ አገልግሎት መስጫ ወደ መሆን እንደምትቀየር የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህ አንጻር ደግሞ ቤተክርስቲያን የእርዳታ ማከፋፈያ ተቋም ሆና ትቀራልች ብለዋል።

ሁለንተናዊ እድገት

ለዚህም ነው ታዲያ ተጠቅሞ መጣልን ባሕሉ ባደረገው የአሁኑ አለማችን ውስጥ ይህንን ተጠቅሞ መጣል የሚለውን ባሕል ለማስወገድ ይቻል ዘንድ ማነኛውም የበጎ አድራጎት ተግባር ሁለንተናዊ እድገትን በሚያመጣ መልኩ መከናወን ይገባውል የምንለው በዚሁ ምክንያት እንደ ሆነ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ በአሁኑ ወቅት እየተንሰራፋ የመጣውን የግድዬለሽነት መንፈስ ለመዋጋት የሚቻለው በዚሁ መንገድ ብቻ ነው ብለዋል። “ድሆችም የሰው ልጆች በመሆናቸው የተነሳ የክርስቶስ መልክ መገለጫዎች ናቸው” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ድሆች ከሚደርስባቸው እጅግ በጣም የከፋ መከራ ውስጥ አንዱ የመንፈሳዊ አገልግሎት እጦት በመሆኑ” የተነሳ እግዚኣብሔር ያስፈልጋቸዋል በዚህም የተነሳ ከእርዳታው ጎን ለጎን እግዚኣብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ሆነ፣ እንደ ሚባርካቸው በቃሉም እንደ ሚያጽናናቸው” ማስተማር ተገቢ ነው ብለዋል።

ኅብረት

በመጨረሻም "በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያነቃቃው፣ የሚደግፈው እና የሚያጅበው በሁለቱም ማለትም በክርስቶስ እና በቤተክርስትያን መካከል ያለው ኅበረት እንደ ሆን የገለጹት ቅዱስነታቸው ማነኛውም የበጎ አድራጎት ተግባር ይህንን በክርስቶስ እና በቤተክርስትያን መካከል ያለውን ኅብረት መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደ ሚገባው፣ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ይህንን ኅበረት የሚገልጽ አገልግሎት ሊሆን የገባዋል ብለዋል።

ማነኛውም የበጎ አድራጎት ተግባር መልካም የሆነ ግንኙነት መፍጠር በሚያስችል መልኩ መካሄድ እንደ ሚገባው የገለጹት ቅዱስነታቸው “ከድሆች ጋር የግል ግንኙነት ሳትመሰርቱ የበጎ አድራጎት ተግባር ማከናወን አይቻልም፣ መነኛውም የበጎ አድራጎት ተግባር ልብን፣ ነፍስን እና በአጠቃላ ሁለንተናችንን ባማከለ መልኩ” ሊደረግ የገባዋል ብለዋል። "በግብዝነት መንፈስ ወይም አሳሳች በሆነ ሁኔታ የበጎ አድራጎት" ተግባራት መፈጸም እንደ ማይኖርባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው የበጎ አድራጎት ተግባር እኛ እግዚኣብሔርን እንድንመስል ሊያነሳሳን የሚገባ ስነ-ምግባር ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

ከግንቦት 15-20/2011 ዓ.ም ደረስ “አንድ ቤተሰብ፣ እንድ የጋራ መኖሪያ” በሚል መሪ ቃል ካሪታስ በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የእርዳታ መስጫ ድርጅ 21ኛውን አጠቃላይ ጉባሄ በሮም ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ይህ 21ኛው ዓለማቀፍ ጉባሄ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 15/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በይፋ መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ቤተክርስቲያን እንደ አንድ ታዋቂ ተቋም ለራሷ ሞገስ ለማግኘት በማሰብ “እንከን የለሽ አሠራር” ከመከተል ይልቅ ቤተክርስትያን የተጠራችሁ ቅዱስ ወንጌልን ለማብሰር መሆኑን በመገንዘብ ለሁሉም የሰው ልጆች በተለይም ለድሃው ማኅበርሰብ ቅርብ መሆን እንደ ሚገባት ገልጸው ማነኛውም የሥራ እቅድ የሰው ልጆችን ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖችን ታሪክ መመልከት ተገቢ እንደ ሆነ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው አሁን ያላችሁ ቤተክርስቲያን ከእዚያ ዘመን ጀምሮ ተጉዛ እዚህ እኛ ያለንበት ዘመን መድረሱዋን ገልጸው ቤተክርስትያን አሁን የደርሰችበት ቦታ ለመድረስ የቻለችሁ ሦስተ መሰራታዊ የሆኑ ነገሮችን አጥብቃ በመያዟ እንደ ሆነ ገልጸው እነዚህ ሦስት መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮች ደግሞ “በትህታና ማዳመጥ፣ አብሮ የመኖር ውበት እና አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን የመተው ብርታት” የሚሉትን መሰረታዊ የሆኑ ተግባሮችን በመጠቀም እዚህ እኛ ዘመን መድረሷን ጨምረው ገልጸዋል። ቤተክርስቲያን “በጣም ውጤታማ  መሆን አለብኝ ከሚለው ፈተና በመውጣት” ምንም እንኳን ቤተክርስትያንን ብዙ ስቃይ ውስጥ የሚከታት ቢሆንም ቅሉ “በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሟትን መገራገጮች/መሰናክሎች ያለምንም ፍርሃት” በማለፍ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርባታል ብለዋል። ቅዱስነታቸው ይህንን በተመለከተ ሲናገሩ. . .

ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ልክ የራሱን ድርጅት በደስታ የሚቀበል እና ለስሙ ጥብቅና የሚቆም ፍጹም የሆነ ሞዴል ያለው ዓይነት ድርጅት እንድትሆን አይፈልግም። መዋቅራዊ አሰራራቸውን ብቻ እንከን የለሽ በሆነ መልኩ ለማስኬድ የሚጥሩ፣ በእቅዶቻቸው ውስጥ ሁሉንም ነገር ግልጽ እና በተሳካ መንገድ ለማስኬድ ብቻ የሚጥሩ አብያተክርስትያናት ሚስኪን ሊባሉ የሚገባቸው አብያተ ክርስትያን ናቸው። እንዲህ ዓይነቱ ነገር ደግሞ እኔን ብዙ ያስጨንቀኛል። ኢየሱስ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አልነበረም የኖረው፣ ሁልጊዜም በጉዞ ላይ ነበር፣ በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙትን ውጣ ውረዶችን በፍጹም ሳይፈራ ነበር ወደ ፊት የተጓዘው። የሕይወታችን እቅድ ሊሆን የሚገባው ደግሞ ቅዱስ ወንጌል ነው፣ ምክንያቱም በውስጡ ሁሉንም ነግሮች እናገኛለንና። ጥያቄዎች ሁሉ ምልስ ሊያገኙ የሚችሉት በእኛ ፈጣን ምላሽ እንዳልሆነ እና እምነት የመንገድ ማሳያ ካርታ እንዳልሆነ በማስተማር በአንጻሩ ደግሞ እምነት ሕይወት መሆኑን፣ እምነት በጋራ የምንጓዝበት የሕወት መንገድ መሆኑን፣ ሁልጊዜ በጋራ በመተማመን የምንጓዝበት የሕይወት መንገድ መሆኑን ያስተምረናል።

አብሮ ለመጓዝ ከተፈለገ ደግሞ በተለይም በተገቢው ሁኔታ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለመግለጽ የማይረዱ ነገሮችን በሙሉ ከጀርባችን ላይ አውረድን መጣል አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮችን አውልቀን የመጣል ውበት” እውነተኛ የሆነ እምነት እንዲኖረን ያደርጋል፣ እውነተኛ እምነት ደግሞ ከነገሮች ጋር ካለን የጠበቀ ግንኙነት እንድንላቀቅ ይረዳናል ብለዋል።

“እንደ ቤተክርስትያን እኛ የተጠራነው ልክ አንድ ድርጅት የሚሰራውን ዓይነት ሥራ ለመሥራት ሳይሆን ነገር ግን ዋናው ተግባራችን ቅዱስ ወንጌልን ማሰራጨት ነው” በማለት በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ራሳችንን ለማንጻት በምናደርገው ጥረት፣ ራሳችንን ለማደስ በምናደርገው ሙከራ ውስጥ ከዚህ ቀደም የነበሩ ነገሮች ሁሉ የተሳስቱ ነገሮች ናቸውና ሁሉንም ነገር በአዲስ መልክ መቀየር ይገባል የሚለውን አመለካከት  ግን ማስወገድ እንደ ሚገባ ጠቅሰው ነገሮችን ላይ ላዩን ማስዋብ ብቻ እግዚኣብሔርን የማያስደስት ነገር እንዳልሆነ ገልጸው እግዚኣብሔርን የሚያስደስተው ነገር ውጫዊ ገጽታችን ሳይሆን ውስጣዊ ወይም ልባችንን መቀየር እንደሆነ ጠቅሰው ይህንን ውስጣዊ የሆነ የልብ ለውጥ ማምጣት የምንችለው ደግሞ የማይጠቅሙንን ነገሮች ከሕይወታችን ስናስወግድ ብቻ ነው፣ ካራሳችን ውስጥ መውጣት ደግሞ መሰረታዊ የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ የማምጫ መንገድ ነው ብለዋል።

ከራሳችን ውስጥ በመውጣት የማያስፈልጉንን ነገሮች አውልቀን መጣል የግላችንን ሳይሆን የሌሎችን ሰዎች ፍላጎት እንድንገነዘብ ያደርገናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ ደግሞ የዋሆች እንድንሆን  ይረዳናል ብለው ይህ ደግሞ የማዳመጥ ክህሎታችን እንዲዳብር የሚያደርግ ሲሆን ይህም በሁሉም ነገር ላይ የጋራ ስምምነት እንዲኖረን ከመፈለግ ወደ ኋላ እንዳንል ያደርገናል፣ ራሳችንን ማዕከል አድርገን ከመቁጠር ይልቅ ትሁታን እንዲንሆን ያደርገናል ምክንያቱም በማነኛውም የበጎ ሥራ ተግባር ውስጥ መንገዱን የሚከፍትልን መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ የተነሳ ይህ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ መንገዶችን ወደ አድማስ በመክፈት አናሳ የሚባሉ የማሕበርሰብ ክፍሎችን ለቅሶ እንድንሰማ ያደርገናል ብለዋል። ይህንን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስነታቸው የሚከተለውን ብለዋል. . .

የሁሉንም ሰው ድምጽ በተለይም ደግሞ አቅመ ደካማ እና የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ድምጽ ማዳመጥ ሁልጊዜ አስፈላጊ ነው። በዓለም ውስጥ ብዙ የመናገሪያ መንገዶች ያሉት ሰው የበለጠ ይናገራል፣ በእኛ መካከል ግን እንዲህ መሆን አይኖርበትም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በአቅመ ደካማው ወይም ደግሞ የመጨረሻ ደረጃ ላይ በሚገኙ ሰዎች አማካይነት ራሱን መግለጽ ስለሚወድ ነው። እያንዳንዳችን ከላይ ሆነን ወደ ታች እናዳንመለከት ይጠይቀናል። አንድን ሰው ከላይ ወደታች መመልከት የሚፈቀደው ያንን ሰው ለመርዳት እና ካለበት ሁኔታ ለማንሳት ስንፈልግ ብቻ ነው- ይህም ብቸኛው አጋጣሚ ነው- አለበለዚያ ግን  ከላይ ሆነን ሌሎችን ወደ ታች መመልከት ተገቢ አይደለም።

የቤተክርስትያን ዋነኛው ተግባር ሰዎችን ማነጽ እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም የቤተክርስትያን ዋነኛው ግብ ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ማቅረብ እንደ ሆነ ገልጸው ይህንን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለውን ብለዋል. . .

ቤተ ክርስቲያን በኮምፒተር ፊት ሳይሆን፣ ተጨባጭ በሆኑ በሰዎች ፊት መቆም የገባናል የሚል ጠንካራ አቋም አላት። ሀሳቦችን ማብራራት ሁኔታዎችን ደግሞ መገንዘብ ይገባል የሚል አቋም አላት። እቅዶቻችንን ከማስቀደም ይልቅ ሰዎችን ማስቀደም ይገባል፣ በትህትና በተሞላ እይታ እኛ በምንሰራው ታላላቅ ተግባራት ሳይሆን ነገር ግን በትናንሽ ተግባሮቻችን ድሆችን ለመገናኘት በምናደርገው ጥረት ውስጥ የሚገኘውን እግዚኣብሔርን እንዴት መፈለግ እንዳለበት የምታውቅ ቤተክርስትያን ልትሆን ይገባል።

“ነገር ግን መርሳት የማይገባን አንድ መዋቅሩ አለ፣ ይህም አብረን በመሆናችን የሚገኝ ውበት ነው፣ በልዩነቶች መካከል የሚፈጠር የጎላ አንድነት፣ የኢየሱስ የሚፈልገው ዓይነት ቤተክርስቲያን መሆን እና ያንን ስሜት መጎናጸፍ ማለት የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች መመልከት ማለት ነው፣ በበጎ አድርጎት ተግባር የተሞላ ሕብረት ነበራቸውና “ ብለዋል።

ድሆች ሕያው የሆኑ የእግዚኣብሔር ማደሪያ ድንኳኖች ናቸው በማለት ስበከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በኢየሱስ "ፍቅር ውስጥ መኖር" ማለት ራሳችንን እንደ እግዚኣብሔር ሙሉ በሙሉ ማቅረብ እና ራሳችንን ሙሉ በሙሉ መስጠት ነጻ እና ነጻ አውጪ የሆነች ቤተክርስትያን መሆን ማለት ነው ብለዋል።

27 May 2019, 18:15