ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኔዎፊት ጋር በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኔዎፊት ጋር በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ ቀሬሊዮስ እና መቶዲዮስ የአይማኖት ሕብረት አብነት ናቸው”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቡልጋሪያ እና ሰሜን መቀዶኒያ ከሚያዝያ 27-29/2011 ዓ.ም ድረስ በቅደም ተከተል የሚያደርጉትን 29ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በመጀመር በዛሬው እለት ማለትም በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው የመጀመርያ መዳረሻ ወደ ሆነችው ወደ ቡላጋሪያ ማቅናታቸውን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በእዚያ በቡልጋሪያ ዋና ከተማ በሶፊያ በአገሪቷ ጠቅላይ ሚንስትር አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ወደ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት መወሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚያ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 04፡50 ላይ በእዚያው በብሔራዊ ቤተ መንገሥት ለተገኙ የአገሪቷን ርዕሰ ብሔር ጨምሮ በእዚያው ለተገኙ የምንግሥት ባለስልጣናት እና የተለያዩ አገራት ልዑካን ንግግር ማድረጋቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከእዚያም በመቀጠል የቡልጋሪያ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ከሆኑት ከብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ኔዎፊት እና ከቅዱስ ሲኖዱሱ ጋር በቅዱስ ሲኖዶሱ ሕንጻ ውስጥ መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንኙነቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “ቅዱሳን ቀሬሊዮስ እና መቶዲዮስ የሐይማኖት ሕብረት አብነት ናቸው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የምስራቃዊያኑን ስርዓተ አምልኮ በሚከተሉ የክርቲያን ማኅበርሰቦች ዘንድ ሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም “የቅዱስ ቶስማ እለተ ሰንበት” በመባል እንደ ሚታውቅ በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህ ሰንበት ይህንን መጠሪያ ያገኘበት ምክንያት ደግሞ ሐዋርያው ቶማስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን መነሳት ለማመን ያስችለኝ ዘንድ “እጆቼን በቁስሎቹ ውስጥ አስገብቼ እርሱ መሆኑን ካላረጋገጥኩኝ አላምንም” ብሎ በመናገሩ የተነሳና በእለቱ ማለትም በሚያዝያ 27/2011 ዓ.ም ዳግማዊ ትንሣኤ በመባል በሚታወቀው ሰንበት ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ይህንን የቶማስን ታሪክ የሚገልጽ በመሆኑ የተነሳ ለእለቱ የተሰጠው የመጠሪያ ስም ነው።

“በታሪክ ሂደት ውስጥ በክርስቲያኖች መካከል የተፈጠረው ቁስል የክርስቶስ አካል በሆነችው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሁን የሚያሳምም ቁስል ሆኖ ቀጥሉዋል” በማለት በንግግራቸው ወቅት የገለጹት ቅዱስነታቸው “ዛሬም ቢሆን የዚህ ቁስል ውጤት ተጨባጭ በሆን መልኩ እንደ ሚታይ” ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ሆኖም ግን "በጋራ በመሆን ችግሮቻችንን በመገንዘብ እና ራሳችንን በእርሱ የፍቅር ቁስል ውስጥ በማስገባት በይቅርታ አማክይነት የሚገኘውን ደስታ ለማጣጣም እንችላለን” በማለት በንግግራቸው ወቅት ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

በደም የተሳሰረ ሕብረት አለን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸው በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “በቡልጋሪያ የሚገኙ በርካታ ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ ስም ብለው በተለይም ደግሞ በአለፉት ክፈለ ዘመናት ውስጥ ብዙ ስቃይ እና ስደት ውስጥ ገብተው እንደ ነበረ” የገለጹ ሲሆን “ይህም የፋሲካ በዓል መስካሪዎች የሆኑት ሁሉ ካሳለፉት ሥቃይ ጋር ኅበረት ያለው ነው” ብለዋል።

“በዓለም ላይ ያሉ ሌሎች በርካታ ወንድሞችና እህቶች በእምነታቸው ምክንያት ብቻ የተነሳ ለመሰቃየት ቢገደዱም እነርሱ እራሳችንን ዝግ አድርገን እንድንኖር ሳይሆን ራሳችንን እንድንከፍት ይጠይቁናል” ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ መነገድ ብቻ ነው እነርሱ የዘሩት ዘር ፍሬያማ ሊሆን የሚችለው ብለዋል።

ድሆችን በጋራ እንድናገለግል ተጠርተናል

የቡልጋሪያ ተወካዮች በእየአመቱ ለባለፉት 50 አመታት ያህል ቫቲካንን መጎብኘታቸውን በንግግራቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው “በእግዚኣብሔር እርዳታ እና እርሱ በፈቀደው ጊዜ” ይህ ግንኙነታችን ለውይይት የሚጋብዝ አዎናታዊ አጋጣሚዎችን እንደ ሚከፍት ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን "እኛ በተለይም እርሱ በእነሩስ ውስጥ ለሚገኝባቸው ድሃ እና እጅግ በጣም የተቸገሩትን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በማገልገል አብረን በጋራ እንድንጓዝ እና ጌታን ለመመስከር ተጠርተናል” ብለዋል።

የጋራ ተልዕኮ

የእኛ መሪዎች ቅዱሳን ቀሬሊዮስ እና ሜቶዲዮስ ናቸው በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነርሱ የባይዛንታይን ባሕል ተከታዮች በመሆናቸው የተነሳ "ለስላቭስ ሕዝቦች በቀላሉ ሊገባ በሚችል ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን መተርጎማቸውን” የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ መለኮታዊ የሆነውን የእግዚኣብሔር ቃል የሰው ልጅ በሚጠቀምባቸው ቃላትን ተጠቅመው ትርጉም በሚሰጥ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን አድርገዋል”ያሉት ቅዱስነታቸው እነሱ "የወንጌላዊነት መልካም አብነት በመሆን እና ወንጌላ ለቀጣዩ ትውልድ ለማወጅ እንችል ዘንድ ያነሳሱናል” ብለዋል።

"የየራሳችንን ባሕሎች እና ልዩ የሆኑ መገለጫዎችን በማክበር” እርስ በእርሳችን በመተጋገዝ ለወጣቱ ትውልድ እምነትን የምናስተላልፍበትን መነገድ መቀየ ይኖርብናል ያሉት ቅዱነታቸው አለበለዚያ ግን "በሸማች ማህበረሰብ ውስጥ በመንሸራሸር ላይ በሚገኘው ዜማ ተወስደው” በእኛ ላይ ያላቸው መተማመን ሊቀንስ ይችላል ብለዋል።

ቅዱስ ዮሐንስ ሁለተኛ ከዚህ ቀደም የተናገሩትን ቃል በመጠቀም ቅዱሳን ቀሬሊዮስ እና መቶድዮስ “የተዋሃደ የአውሮፓ አህጉር እንዲፈጠር ጥረት ማድረጋቸውን፣ አብሮ በጋራ መኖር እንደ ሚቻል ማሳየታቸውን፣ ልዩነቶቻችንን በተመለከተ ደግሞ ልዩነቶቻችን አንድነት ለመፍጠር እንቅፋት መሆን እንደ ሚይችሉ ማሳየታቸውን” ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት ገልጸው በዚህ ረገድ ቡልጋሪያን የተለያዩ የእምነት እና ሃይማኖታዊ ትውፊቶች ተቻችለው የሚኖሩባት እና “መንፈሳዊነት የተሳለጠበት” አገር መሆኑን በድጋሚ ከገለጹ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

05 May 2019, 17:57