ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የሮማኒያ  የኦርቶዶክስ ቤተ/ቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተ/ቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እኛን የሚያገናኝ የእምነት ትስስር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው” አሉ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ እያካሄዱ መሆኑ ይታወቃል። ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከግንቦት 23-25/2011 ዓ.ም ድረስ 30ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮማኒያ ማድረጋቸውን በቀጠሉበት ወቅት በቅድሚያ በአገሪቷ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ በእዚያው ለተገኙ የአገሪቷ ባለስልጣናት፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት እና የተለያዩ አገራትን ልዑካን በተገኙበት የአገሪቷ ርዕሰ ብሔር ካደረጉት የእንኳን መጣችሁ መልእክት በመቀጠል ቅዱስነታቸው ንግግር ማድረጋቸውን ቀደም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 10፡15 ላይ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ መኖሪያ ሕንጻ በማቅናት በሮማኒያ  የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ በሆኑት ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸው እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚያው ለተገኙ በሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና በአገሪቷ የምትገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ንግግር ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ቅዱስነታቸው ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት “እኛን የሚያገናኝ  የእምነት ትስስር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ተከበሩ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና የተከበራችሁ የቅዱስ ሲኖዶሱ ብጹዕን ጳጳሳት

“ክርስቶስ ከሙታን ተነስቱዋል! የጌታ ትንሳኤ ለአብያተ ክርስቲያናት የተላለፈው እና የቤተክርስቲያን የሐዋርያዊ ስብከት ማዕከል ነው። በትንሳኤ በዓል ወቅት ሐዋርያቱ ከሙታን የተነሳውን ጌታ በመመልከታቸው እጅግ በጣም ተደስተው ነበር” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ አሁን በምንገኝበት የትንሳኤ በዓል ወቅት ይህ የትንሳኤ ደስታ በእያንዳንዳችን ፊት ላይ ይታያል ብለዋል።

የዛሬ 25 አመት ገደማ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ በዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ቆመው ባደረጉት ንግግር “ወደ እዚህ የመጣውት በእናንተ ቤተክርስቲያን ውስጥ  በሚገኘው የኢየሱስን የፊት ገጽታ በሚያሳየው ምስል ላይ ለማሰላሰል ነው” በማለት ተናግረው እንደ ነበረ በማስታወስ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኔም ቢሆን እዚህ የተገኘውት እንደ አንድ ነጋዲ በመሆን ይህንን የኢየሱስን የፊት ገጽታ በወንድሞቼ በእናተ ላይ ለመመልከት በማሰብ ነው፣ የእናንተን ፊት ስመለከት ይህንን የኢየሱስን ፊት እመለከታለሁ፣ ላደረጋችሁልኝ ደማቅ አቀባበል እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ብለዋል።

“እኛን የሚያገናኝ  የእምነት ትስስር ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ የነበረ ሲሆን በተለይም በቱፊት እንደ ሚነገረው በአገራችሁ የክርስትናን እምነት ያስተዋወቁ ጴጥሮስና እንድርያስ ለየት ባለ መልኩ ትስስራችንን ያጠናክሩታል። እነዚህ የደም ትስስር ያላቸው ወንድማማቾች ይህንን ምስክርነት እውን ያደርጉት ደማቸውን ለጌታ በማፍሰስ ጭምር ነው” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ ሰማዕታት እኛም በደም የተሳሰርን ወንድማማቾች መሆናችንን እንድንገነዘብ በማድረግ ከክፍለ ዘመናት በፊት የተጀመርውን የእመንት ጉዞ አጠንክረን በጋራ እንቀጥል ዘንድ ከእኛ ጋር ሆነው ይረዱናል ብለዋል።

“በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ስፍራዎች እንደ ምናስተውለው የእናንተም አብያተ ክርስቲያናት የፋሲካን በዓል ማለትም ስቅለተ አርብ ቀን ኢየሱስ ስቃይ እና መከራ የተቀበለበትን፣ እለተ ቅዳሜ ደግሞ በመቃብር ውስጥ በዝምታ የቆየበትን እና እሁድ እለት ደግሞ እንደ ገና የተወለድንበትን የትንሳኤ በዓል በከፍተኛ ድምቀት እየተከበረ” መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት ይህንን እምነታቸውን በመመስከራቸው የተነሳ በጣም ብዙ ወንድሞች እና እህቶች ለስቃይ እየተዳረጉ፣ ሰማዕት እየሆኑ እንደ ሚገኙም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ዛሬም ቢሆን በተለያየ መልክ እምነታቸውን በመግለጻቸው ብቻ ለከፍተኛ ስቃይ የተዳረጉ ብዙ ሰዎች እንደ ሚገኙ በንግግራቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ሕይወታቸውን በመስጠት እና ደማቸውን በማፍሰስ ለእኛ ያሳየቱ አብነት እኛም በጋራ በእዚህ ዓይነት ስቃይ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች አለኝታነታችንን መግለጽ እንደ ሚገባ ገልጸው በክርስቶስ ሐዘን እና መከራ፣ እንዲሁም በክርስቶስ ትንሳኤ ውስጥ በአንድነት በመግባት “ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከእርሱ ጋር ተቀብረናል” (ሮም 6፡4) ብለዋል።

“የተከበሩ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል እና የተከበራችሁ ብጹዕን ጳጳሳት ወንድሞቼ የዛሬ 25 አመት ገደማ ከእኔ በፊት የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና በእናንተ ቤተክርስቲያን መካከል በአዲስ መልክ የተጀመረው ግንኙነት የዚህ የፋሲካ በዓል ስጦታ ነው” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሮማኒያ በሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መካከል የዛሬ 25 አመት በአዲስ መልክ የተጀመረው ግንኙነት አዲስ ምዕራፍ የከፈተ እንደ ነበረ ገልጸው ይህ ግንኙነት በእዚያው በሮማኒያ ብቻ ተገድቦ የቀረ ሳይሆን ነገር ግን በአጠቃላይ በዓለም ደረጃ በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ለሚደረገው ውይይት መልካም አጋጣሚ መክፈቱን ገልጸዋል። በአንድ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አብዛኛው ሕዝብ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ በሆነባት በሮማኒያ ያደረጉት ያ ጉብኝት በዓለም ደረጃ ተመሳሳይ የሆኑ ግንኙነቶች እንዲመሰረቱ በር መክፈቱን የገለጹት ቅዱስነታቸው አሁን ያለንበት ወቅት በጋራ በወንድማማችነት መንፈስ ወደ ፊት የምንጓዝበት ወቅት ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

“ቅደም ሲል የነበሩንን ማደረ ትውስታዎችን በድጋሚ በማስታወስ በጋራ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርብናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቀደም ሲል የነበሩን መልካም ያልሆኑ ማደረ ትውስታዎችችን በግንኙነታችን ላይ እንቅፋት እና መሰናክል የሚፈጥሩብን በመሆናቸው የተነሳ መልካም የሚባሉትን ማደረ ትውስታዎቻችንን ማለትም በመጀመሪያ ምዕተ አመት ቅዱስ ወንጌል በድፍረት እና በነብይነት መንፈስ የመሰከሩትን ሥር መሰረታችንን ብቻ በማስታወስ  በእዚህም መሰረት ሕዝቦቻችንን በዚህ መንፈስ ውስጥ ሆነው ይጓዙ ዘንድ በማበረታታት ቀደም ሲል በመጀመሪያው ምዕተ አምት ውስጥ የነበሩት አባቶቻችን የከፈሉትን መስዋዕትነት እና ገድል በማስታወስ፣ እንዲሁም በእየለቱ በሕይወታቸው የቅድስናን ሕይወት ለመኖር እየተጉ ያሉ ሰዎችን አብነት በመከተል “ዝማሬዬን በሌሊት አስታወስሁ፤ ሥራህን ሁሉ አሰላስላለሁ፤ ድንቅ ሥራህን ሁሉ አውጠነጥናለሁ። አምላክ ሆይ፤ መንገድህ ቅዱስ ነው፤ እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?” (መዝ 77፡6. 12-13) የሚለውን በማስታወስ ወደ ፊት በጋራ መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል።

“ጌታን በማዳመጥ አንድ ላይ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርብናል” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሳኤ ቀን ወደ ኤማሁስ በመጓዝ ላይ ከነበሩ የእርሱ ደቀመዛሙርት ጋር ያደርገውን ጉዞ በማስታወስ፣ እነዚህ የኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት በመንገድ ላይ በሚጓዙበት ወቅት ኢየሱስ ያጋጠመውን መከራ እና የእነርሱን ስጋት፣ ጥያቄ እና ጥርጣሬ በማስታወስ ሞቅ ያለ ክርክር በማደረግ ወደ የቤታቸው ይመለሱ እንደ ነበረ እና ይህንን ጥያቄያቸውን፣ ክርክራቸውን፣ ስጋታቸውን ጭንቀታቸውን ሁሉ ኢየሱስ ከእነሩስ ጋር በመሆን በሚገባ በትዕግስት ካዳመጠ በኋላ በውይይታቸው ውስጥ ኢየሱስ ጣልቃ መግባቱን ገልጸው ያልተረዱትን ነገሮች በማብራራት ጥርጣሬያቸውን እንዲያስወግዱ እና ሁኔታውን በሚገባ እንዲገነዘቡ፣ ከእዚያም በሁኔታዎች ላይ በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ እንዲያደርጉ እንደ ረዳቸው ሁሉ እኛም ይህንን አብነት በመከተል ጌታ እንዲያግዘን በመጠየቅ በጋራ ወደ ፊት መጓዝ ይኖርብናል ብለዋል።

እኛም ብንሆን በተለይም ደግም አሁን ባለንበት ዓለማችን ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመታየት ላይ ባለው የማኅበራዊ እና ባሕላዊ ለውጥ በሚገባ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ የኤማሁስ መንገደኞችን አብነት በመከተል ጌታን ማዳመጥ የገባናል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የቴክኖሎጂ እና የኢኮኖሚ እደግት ብዙዎቹን የዓለም ሕዝቦች ተጠቃሚ ያደርግ ዘንድ፣ በሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በመንጸባረቅ ላይ የሚገኘው የጎሎባላይዜሽን ስርዓት እና ሐስተሳሰብ ባህላዊ የሆኑ መሰረታዊ እሴቶችን በከፍተኛ ደረጃ እንዲሸረሸሩ በማደረግ፣ ስነ-ምግባራዊ የሆኑ የሰው ልጅ እሴቶችን እና ማኅበራዊ ሕይወትን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ በመንሰራፋት ላይ የሚገኘውን የጥላቻ እና የመከፋፈል መንፈስ በጋራ መዋጋት እንችል ዘንድ የጌታን ቃል በማዳመጥ ወደ ፊት በጋራ መራመድ ይገባናል ብለዋል።

በኤማሁስ እንደ ተደረገው እና የኤማሁስ መንገደኞች የጀመሩትን ጉዞ ያጠቃለሉት ከጌታ ጋር አብሮ በጽናት ጸሎት ባደረጉበት ወቅት እንደ ነበረ ሁሉ እኛም በዚህ ረገድ የምናደርገው ጉዞ ሊጠናቀቅ የሚገባው በዚሁ መልክ ሊሆን እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው እንጀራውን በቁረሰበት ወቅት የተገለጸው ጌታ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ለማከናወን፣ አንደኛው ሌላውን ለማገልገል እንዲነሳሳ፣ ስለእግዚኣብሔር ከመናገራችን በፊት እግዚኣብሔርን መስጠት እንችል ዘንድ፣ በተባበረ ክንድ በጋራ ተግባራችንን ማከናወን እንችል ዘንድ እንዲረዳን ልንጠይቀው የገባል ብለዋል።

በዚህ ረገድ የሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በጋራ ለሕዝቡ እያበረከቱት የሚገኘው አገልግሎት በአብነት ሊጠቀስ ይገባዋል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ መልካም ግንኙነት ሊፈጠር የቻለው እርስ በእርስ በመተማመን እና በእየጊዜው እያደገ በመጠው መልካም ግንኙነት የተነሳ እና እርስ በእርስ ተጨባጭ በሆነ መልኩ መቀባበል በመቻላችን፣ እንዲሁም በመደጋገፋችን እና በኅብረት በመሥራታችን የተነሳ ነው ብለዋል። በዚህ መልካም ግንኙነት የተነሳ በሮማኒያ የሚገኙ የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምዕመናን እርስ በእርሳቸው በመተማመን እንደ ወንድም እና እህት እየተያዩ መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም መልካም አብነት ያሳየ ተግባር ነው ብለዋል።

ወደ አዲሱ ጴንጤቆስጤ በጋራ የሚደረግ ጉዞ

አሁን ያለንበት የፋሲካ ወቅት ወደ ጴንጤቆስጤ በዓል የሚመራን መሆኑን በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ደቀ-መዛሙርቱ ፍርሀትና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜት ይታይባቸው የነበረ ቢሆንም ቅሉ ፋሲካ የአዲስ ጉዞ ጅማሬ ምልክት ሆኖላቸው እንደ ነበረ ገልጸው ደቀ-መዛሙርቱ የእግዚኣብሔር እናት ከሆነችው ከማርያም ጋር በላይኛው ክፍል ውስጥ በአንድነት ተሰብስበው በነበረበት በጴንጤቆስጤ ቀን መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ መወረዱን እና ሁሉም የተለያየ ዓይነት ቋንቋዎች የመናገር ችሎታ ከሰጣቸው በኋላ ነበር ከሙታን የተነሳውን ጌታ በቃል እና በሕይወታቸው መመስከር የቻሉት ብለዋል። የእኛ ጉዞ ከሙታን በተነሳው በአንድኛው በጌታ ላይ በተመሰረተ መልኩ ወንድማማቾች እና እህታማማቾች በመሆን በእርግጠኛነት በአንድ መንፈስ ጀምረናል ያሉት ቅዱስነታቸው ከፋሲካ በዓለ እስከ ጴንጤቆስጤ እለት ድረስ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ ሥር ሆነን የምንጸልይበት ወቅት ሊሆን ይገባል በዚህ ጸሎታችን ደግሞ አንዱ በሌላው ላይ መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ዘንድ የምንጸልይበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል። መንፈስ ቅዱስ እኛን በማደስ እኛ አንድነትን ለማሳየት እና በጣም ውብ እና የተቀናጀ የተለያየ ብዝሃነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ይኖረን ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን በመጠየቅ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በጋራ በመሆን ምስክርነት እንዳንሰጥ የሚያግደንን መንፈስ እንዲያስወግድ እና ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን ማከናወን እንችል ዘንድ፣ አንደኛችን ከአንደኛችን ጎን መጓዝ እንችል ዘንድ፣ በውስጣችን አዲስ መንፈስ ይፈጥር ዘንድ፣ የተሰጠንን ተልዕኮ በጋራ ማከናወን እችንል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ልንለምነው ይገባል ብለዋል።

ውድ ወንድሞቼ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ኢየሱስን ለማየት እንዲችሉ ለመርዳት በመጣር አብረን ለመጓዝ እንችል ዘንድ ቅድስት ሥላሴ እንዲረዳን መጸለይ የገባል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በድጋሚ በግሌ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ስም ጭምር ለእናተ ምስጋናዬ እያቀረብኩኝ በተጨማሪም በጸሎት ከእናተ ጋር መሆኔን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እና የሮማኒያ የኦርቶዶክስ ቤተ/ቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ዳኒኤል
31 May 2019, 18:07