ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከጋዜጠኞች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከጋዜጠኞች ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ጋዜጠኞች እውነትን እና በጎነትን የሚያንጸባርቁ ትሁት እና ነፃ ሊሆኑ ይገባል”

ባለፈው ቅዳሜ ግንቦት 10/2011 ዓ.ም ከ400 በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች በቫቲካን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ባደርጉት ንግግር እንደ ገለጹት “ጋዜጠኞች እውነትን እና በጎነትን የሚያንጸባርቁ ትሁት እና ነፃ ሊሆኑ ይገባል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ትሁት እና ነፃ ጋዜጠኝነትን በማበረታታት ጋዜጠኞች "የተበላሸ ምግብ የሚመስለውን የተሳሳተ መረጃ ከመሸጥ" ይልቅ “እውነት እና መልካም የሆነ እንጀራ” የሚመስል መረጃ ለሕዝቡ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

“መረጃ ለማፍረስ ሳይሆን መልካም ነገሮችን ለመገንባት፣ ስወችን እንዲያጣላ ሳይሆን ሰዎችን እንዲያገናኝ፣ ሰዎችን ለመጫን ሳይሆን ሰዎች እንዲወያዩ ለማደርግ፣ አፍራሽ የሆኑ ነገሮችን ለማስተላለፍ ሳይሆን ለማነጽ፣ አለመግባባትን ሳይሆን መግባባትን ለመፍጠር፣ ጥላችን ለመዝራት ሳይሆን ወዳጅነትን ለመፍጠር፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለሚጮኹ ሰዎች ሳይሆን ድምጽ አልባ የሆኑ ሰዎችን ድምጽ ለማስተጋባት በእውነት እና በፍትህ ላይ ተመርኩዛችሁ የጋዜጠኝነት ሙያችሁን ማከናወን ይገባችኋል” ብለዋል።

በወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮስ ከተለያዩ አገራት ለተውጣጡ በጣሊያን ለሚኖሩ የጋዜጠኞች ማኅበር አባላት እንደ ገለጹት “እርሳቸው በግላቸው እና እንዲሁም ቤተክርስቲያን ጋዜጠኞች እውነትን ፍለጋ እያበረከቱት የሚገኘውን ከፍተኛ አዎንታዊ የሆነ አስተዋጾ እንደ ሚያደንቁ የገለጹ ሲሆን “እውነት ብቻ ነው ነጻ ሊያወጣን የሚችለው” ብለዋል።

ትህትና እና እውነት

ትህትናን እንደ የጋዜጠኝነት ሙያ መሠረታዊ ነገር አድርገው መቁጠር እንዳለባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እውነትን ለመፈለግ የሚደረግ ጥረት በብዙ ችግሮች ውስጥ ማለፍን እና ትህትናን የሚያካትት ተግባር ነው ብለዋል። “ሁሉን ነገር አስቀድሜ አውቃለሁ” የሚል አስተሳሰብ እውነትን ለመፈለግ የምዲረገውን ጥረት እንደ ሚያዳክመው የገለጹት ቅዱስነታቸው አንድ ጽሑፍ፣ የቲዊተር መልእክት ወይም ደግሞ አንድ የቀጥታ ስርጭት አዎንታዊ የሆኑ መልእክቶችን ለማስተላለፍ ልንጠቀምበት እንችል ይሆናል ነገር ግን ጥንቃቄ ካልተደረገ ግን ሌሎችን ሊጎዳ እና ክፉ ነገር ሊያደርስባቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባዋል ብለዋል።

የተወሰኑ "ጩኸት" የሚመስሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት እውነታውን በሚገባ አስቀድማችሁ ሳያረጋግጡ ማቅረብ እንደ ማይገባቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ጋዜጠኞች በቂ የሆነ ማረጋገጫ ያላገኙባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ከማስተለፍ መታቀብ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ይልቁንም ትሁት የሆነው ጋዜጠኛ መረጃውን ከማስተላለፉ በፊት የመረጃውን ትክክለኛነት አስቀድሞ ለማረጋገጥ እንደ ሚሞክር በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው እንዲህ ዓይነቱ የጋዜጠኝነት ሙያ ደግሞ ትክክለኛ የሆኑ ዘገባዎችን ለድማጮቹ ለማቅረብ ያስችለዋል ብለዋል።

ጎጂ የሆኑ ቋንቋዎች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፋራንቸስኮስ በጣሊያን ከሚገኘው ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ የጋዜጤኞች ማኅበር አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደ ገለጹት ኃይለኛ እና አስጸያፊ ቋንቋዎችን በመጠቀም ሰዎችን ከመጉዳት እና ሰዎች እርስ በእርስ እንዲጠፋፉ ከማደረግ መቆጠብ እንደ ሚገባቸው የገለጹ ሲሆን ብዙ ሰዎች ስለሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር እንደ አንድ የባሕሪያቸው ክፍል አድርገው በመቁጠር በሚናገሩበት በአሁኑ ወቅት እያንዳንዱ ሰው በፍጹም ሊገረሰስ የማይችል የራሱ የሆነ ልዩ መለያ ባሕሪይ ወይም ሰብዓዊ ክብር እንዳለው በመገንዘብ በቃላት አጠቃቀም ረገድ ጥንቃቄ ማደረግ ተገቢ ነው ብለዋል።

ብዙ ሰዎች የሐሰት ዜና በሚያሰራጩበት በአሁኑ ወቅት  "ትሕትና የተዛባ እና የተሳሳተ መረጃ እንዳታስተላልፉ እናንተን በመርዳት በምላሹ እውነተኛ ዜና ብቻ እንድታቀርቡ ይረዳችኋል ብለዋል። “ሐሳብን በነጻ የመግለጽ እና መረጃን በነጻ ማስተላለፍ” አንድ አገር ጤናም አገር መሆኑ የሚለካበት ዋነኛው መስፈርት እንደ ሆነ አጽኖት በመስጠት የገለጹት ቅዱስነታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ሙያዊ ግዴታቸውን በብርታት እና አንዳንድ ጊዜም በጦርነት ውስጥ እና አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ በመሆን ተግባራቸውን በማከናወን ላይ በነበሩበት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ ጋዜጠኞች የተሰማቸውን የሐዘን ስሜት ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

“ጋዜጠኞች ጥቃት፣ ስደት እና መገለል እየደረሰባቸው ከሚገኙ ሰዎች ጎን እንዲቆሙ” ጥሪ ያቀረቡት ቅዱስነታቸው ጋዜጠኞች እንደ ሮንጋያን እና እንደ ያዚዲ ሕዝቦች የመሳሰሉ የመከራና የጦርነት ሁኔታዎችን በድጋሚ በማስታወስ መዘገብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ከመወለዳቸው በፊትም እንኳ ሳይቀር ታፍነው እንዲቀሩ የተደርጉትን የሕጽናት ሁኔታ ጨምሮ ከተወለዱ በኋላ በረሃብ፣ በመከራ፣ በጦርነት በውትድርና አገልግሎት ውስጥ አስገዳጅ በሆነ መልኩ እንዲሳተፉ የተደርጉትን የሕጻናት ሁኔታ ለዓለም እንዲታወቅ ያደረጉትን ጋዜጠኞች ቅዱስነታቸው ያመሰገኑ ሲሆን ጋዜጠኞች በተለያዩ ምክንያቶች ስደት የሚደርሳብቸውን ሰዎች እና እንዲሁም በእምነታቸው፣ በዘር ሐረጋቸውም ጭምር የተነሳ ለስደት እና ለመከራ የተጋለጡ የሚገኙትን ሰዎች ሁኔታ ለዓለም ማስወቃችሁን መቀጠል ይኖርባችኋል ብለዋል።

“ዓለም ሊያውቀው የሚገባው እና እንደ ባህር ጥልቅ የሆነ እጅግ የሚበዙ መልካም የሆኑ ነገሮች በዓለማችን ውስጥ እንደ ሚገኙ፣ እነዚህ መልካም የሆኑ ነገሮች ደግሞ ለዓለም ሕዝብ ጥናካሬ እና ተስፋ እንዲሰጡ” ለማስቻል በዓለማችን ውስጥ የሚገኙ መልካም እሴቶችን ማስተዋወቅ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህ ረገድ ሴት ጋዜጠኞች ለየት ባለ ሁኔታ እንደ እነዚህ ላሉ ዘገባዎች ትኩረት እንደ ሚሰጡ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጣሊያን አገር ከሚገኙ ከተለያዩ አገራት ከተውጣጡ ጋዜጠኞች ማኅበር አባላት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ካጠናቀቁ በኋላ እርሳቸው ለዓለም የኮሚንኬሽን ቀን “መልካሙን ዘገባ ማሰራጨት” በሚል አርእስት ይፋ አድርገው የነበረውን መልእክት ሙሉ ይዘቱን በስጦታ መልክ ለጋዜጠኞቹ ማበርከታቸው ተገልጹዋል።

18 May 2019, 18:19