ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ንግግር ባደረጉበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ንግግር ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “አንድ ማኅበረሰብ አቀመ ደካማ የሆኑ ግለሰቦችን አቅፎ መያዝ ይገባዋል” አሉ

ቅዱስ አባትችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም ግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. እ.ኢ.ዘ.ኣ. በሮማኒያ ዋና ከተማ ቡካሪስት 30ኛውን ሓዋርያዊ ጉዞ በማድድረግ ላይ መሆናቸው ይታውቃል። ይህንንም ጉዞ ለማድረግ የጋበዟቸውን የሃገሪቱን ርእሰ ብሔር እና ጠቅላይ ሚኒስቴሩን እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በቦታው የታደሙ የተለያዩ ኣገር ኣምባሳደሮችን በመቀጠልም የሲቭሉን ማኅበረሰብ እና ከተለያዩ ዓብያተ ክርስቲያናት ተወክለው የመጡትን ብጹኣን ጳጳሳትና ካህናትን እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችን አመስግነዋል ።

የእዚህ ዜና አቅራቢ ግርማቸው ተስፋዬ- ቫቲካን

በመቀጠልም ቅዱስ ኣባታችን ፍራንቼስኮስ ተመሳሳይ ሰላምታቸውን ለብጹዕ ፓትሪኣርክ ዳንኤል እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶሱ ውስጥ ላሉ ብጹኣን ጳጳሳትና እንዲሁም ካህናት ለሩማኒያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ምዕመናን ልባዊ ሰላምቸውን ኣቅርበዋል። በመቀጠልም በዚህ በሩማኒያ ለሚኖሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹኣን ጳጳሳትና ካህናት እንዲሁም ምዕመናን ልባዊ ምኞታቸውን ከገለጹ በኋላ ይህ ሓዋርያዊ ጉብኝታቸው ክርስቲያናዊ ጉዞና ክርስቲያናዊ ምስክርነትን ይበልጥ ለማረጋገጥና ለማጠናከር መሆኑን ኣስረድተዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተል ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ 2ኛ በሩማንያ ጉብኝት ካደረጉ ከ25ኛ ዓመት በኃላና በተለይም በዚህ ዓመት ሩማኒያ ወደ ኣውሮፓ ህብረት ከተቀላቀለች በኃላ የኣውሮፓን ህብረት ለመምራት ለመጀመሪያ ጊዜ ኃላፊነቱን በያዘችበት ወቅት ወደዝች መልካም ምድር መምጣታቸው ጉብኝቱን ታሪካዊ እንደሚያደርገውና እሳቸውንም እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል ይህ ኣሁን ያለንበት ጊዜ ሩማንያ ከ30 ዓመት በፊት የሲቭልና የሃይማኖት ነፃነትን ከሚፃረርና ሮማኒያን ከመላው ኣውሮፓ ኣገሮች ከለያት እንዲሁም በኢኮኖሚዋና ዕድገቷ ላይ ተፅዕኖ ካሳደረባት መንግሥት ነፃ የወጣችበትን ጊዜ ለማስታወስ ጥሩ ኣጋጣሚ የፈጠረ መሆኑን ኣስታውሰዋል።

በእነዚህ ዓመታት ሮማኒያ ከፖለቲካ እና ከማህበራዊ ኃይሎች ጋር በመቀራረብና በመወያየት እንዲሁም በመቻቻል የሃይማኖት ነፃነትን በማክበርና እና ተደጋግፎ በመሥራት እንዲሁም ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙሉ ተሳትፎ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን ኣውስተው ምንም እንኳን በዚህ ጉዞዋ የነበሩትን ከፍተኛ ችግሮች እና ጋሬጣዎች እንዲሁም እነዚህን ችግሮች እና ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የተደረጉትን ታላላቅ እርምጃዎችና ደረጃዎች እውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ኣስምረውበታል።

በመቀጠልም ሃገሪቱ እየተሳተፈችበት በምትገኘው ማለትም በተለያዩ የሲቪል ማህበራዊ, ባህላዊና ሳይንሳዊ ምሕዳር ውስጥ ለመሳተፍ መወሰኗ ታላላቅ የፈጠራ ስራዎችን እንድትፈጥር ከማስቻሉም ባሻገር ሀገሪቱ ኣሁን በመንገኝበት በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን  አዳዲስ ፈጠራዎችን ይዛ እንድትቀርብ ያስችላታል ካሉ በኃላ ቅዱስነታቸው ኣያይዘው ለዜጎች ህጋዊ ምኞቶች ምላሽ እንዲሰጡ የሚያስፈልጉትን መዋቅሮች እና ተቋማት ለማጠናከርና የአገሪቱን ህዝብ ሙሉ እምቅ እና እምቅ ችሎታውን እንዲያሳኩ ለማበረታታት እነዚህን ጥረቶች ወደፊት ኣጠናክረው እንድቀጥሉ ሓሳባቸውን ስንዝረዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ይላሉ ቅዱስነታቸው በዚህ ባለንበት ዘመን የተከሰቱት ለውጦች ሁኔታው የፈጠራቸው ማኅበራዊ ኣለመረጋጋትና አስተዳደራዊ ችግሮችን ለማስወገድ ብሎም ለሚከሰቱት ማኅበራዊ ቀውሶች መፍትሄ ለማምጣት ለሚደርገው ርብርብ እውቅና ሊሰጠው ይገባል ብለው በተለይም መኖሪያ ሀገራቸውንና ቄኣቸውን ጥለው በመሰደድ ሥራ እና የተሻለ ሕይወት ፍለጋ የሚንከራተቱትን በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ቦታ ማስያዝ እንደሚገባና ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚያሻ ኣሳስበዋል ።

እንደዚሁም ብዙ ነዋሪዎቻቸውን ያጡ በርካታ መንደሮች መኖራቸውንና በዚህም ምክንያት በተፈጠሩት ችግሮች የኑሮኣቸው ደረጃ በትንሹም ቢሆን መድከሙንና ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ጥልቅ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ሥርዓቶችን ኣደጋ ላይ ይጥላል ብለው በተለይ የሩማኒያ ሕዝብ ይህንን ችግር ለመፍታት ያሳየው ተጋድሎና ትጋት የተደራሹን ኣገር ብቻ ሳይሆን እንዲሁም በቤት ውስጥ የቀሩትን የራሳቸውን  ቤተሰብ በመርዳት ያሳዩት ከፍተኛ ጥረት እጅጉን የሚበረታታና ድንቅ ተግባር ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ኣያይዘው የእነዚህን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ችግሮች ለመጋፈጥ, ውጤታማ መፍትሔዎችን ለይቶ ማወቅና ዘለቄታ ያለው መፍትሄ ለማግኘት ከሀገሪቱ የፖለቲካ, የኢኮኖሚ, የማህበራዊና መንፈሳዊ ኃይሎች ጋር የበለጠ ትብብርና ምክክር ይጠይቃል ብለዋል።

እያንዳንዱ መንግሥት ሕዝብ የሚለውንና የሚሻውን የህዝቡን የጋራ ራእይና ኃላፊነት በመከተል ከፍተኛውን የሕዝብ ፍላጎትና ራእይ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይህም ማለት ለሰዎች የጋራ ብልጽግናና በኣንድነት ውጤታማ ሆኖ ለመጓዝ ከፍተኛ  የሆነ ውስጣዊ ተነሳሽነት ከማህበረሰቡ ጋር የተሳሰረና በእነርሱም ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ዕቅድ እንዲኖርና በተሻለ መልኩ ለማራመድ የሚያስችለውን ስምምነት ከማህበረሰቡ ጋር መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ይህም ማለት ሁሉም ሰው የራሱን ስጦታዎች እና ችሎታዎች  በትምህርት እና በፈጠራ በተደገፈ ሁኔታ, ለኅብረተሰቡ ጥቅም ሊያበረክት ይገባል ብለዋል ( በላቲን ቋንቋ Evangelii Gaudium ኤቫጀሊ ጋውዲየም, 192)።

በዚህ መልኩ ሁሉም ዜጎች ማለትም ደካሞች, ድሆችና ዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ, ኣንድ ወጥ በሆነ መሥመር ውስጥ ስለሚካተቱ ሁሉም በጋራ ለሚገነባው የኅብረተሰብ ክፍልና የጋራ ዕድገት የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ተሳታፊነታቸውን ያስመሰክራሉ። ይህ አጠቃላይ ሂደት ንጹህ ልብና ነፍስ እንዲሁም በግልጽ የተቀመጠ ግብ ሊኖረው ይገባል, ይህም ከሁሉ በላይ የምንደርስበትን የእድገት ጣራ ሳይሆን የሰው ልጅ እና የእሱ ወይም በእሱ የማይሻሩ መብቶቿን ግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባል ብለዋል (በላቲን ቋንቋ Evangelii Gaudium ኤቫጀሊ ጋውዲየም, 203)።

ሰላማዊና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የኅብረት እና የበጎ አድራጎት የማህበራዊ, እንዲሁም የፖለቲካ እና የፖለቲካ ኃይሎች ተጨባጭ ጥቅምን ለማራመድ ኢኮኖሚያዊ ንድፈ ሀሳቦችን, ወይም የባለሙያ ስሌቶችን እና ችሎታዎችን ዘመናዊ ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም. እነዚህ በራሳቸው አስፈላጊ ናቸው ነገር ግን ከሁሉ ነገር በላይ ሊታይ የሚገባው በኢኮኖሚ የማደግ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ህይወትና ክብር ከምነም ነገር በላይ ትኩረት ሊሰጠው እንድሚገባ ኣሳስበዋል።

በዚህ ረገድ የክርስትና አብያተ የክርስቲያናት በፖለቲካ እና በማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተንተርሰው በሰው ልጅ ክብር ላይ በመመሥረት ፍትሃዊነትን በማስፈን የተቸገረ ልብን እንደገና በማደስና በማጠናከር የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግቡ ይችላሉ ብለው እነዚህ እውነተኛ ወዳጅነት እና ትብብር እያደጉ ሲሄዱ እግዚአብሄር በሰዎች መሓከል የመገኘቱን ተዓማኒነት የሚያንፀባርቅ እና ለሥራውም የሚያምር ምስክር ለመሆን ይችላል ብለዋል።

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ይህንን መከተል ትፈልጋለች ለማኅበረሰቡ መገንባት አስተዋጽኦ ማድረግ ትፈልጋለች በአንድነት ተስፋን ለማጣጣም ብሎም በሰዎች ክብር እና በጋራ ጥቅም ላይ ለመድረስ ትመክራለች ከሌሎች ኣብያተክርስቲያናት እንዲሁም ከሁሉም የሰው ዘር ጋር በመተባበር ያላትን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለሰው ልጆች ለማካፈልና ለማገልገል ትፈልጋለች ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል ይህ ከቶውንም ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንግዳ ነገር አይደለም ካሉ በኃላ የአገሪቷን የወደፊት ቅርጽ ለማንፀባረቅና በመደበኛ ትምህርት ውስጥ ተመጣጣኝ የሆነ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ለማድረግ እአዲሁም መዋቅሮችን ለመዘርጋት ብሎም ለማጎልበት የሚታየውን ተነሳሽነትና ተሣታፊነት ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ  ትጋራለች በዚህ መንገድ በሩማንያ ውብ አገርዎ ህብረተሰብን ህዝባዊ እና መንፈሳዊ ህይወትን ለማጎልበት አስተዋፅኦ ማድረግ ትፈልጋለች ብለው ለኣገሪቱ መሪና ለሩማንያ ሕዝብ እንዲሁም እዛ ለተሰበሰበው እድምተኛ ሁሉ ሰላምና ብልጽግና ተመኝተው ንግግራቸውን ቋጭተዋል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ንግግር ባደረጉበት ወቅት
31 May 2019, 17:54