ዘንድሮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የተከናወነው የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ስርዓት፣ ዘንድሮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ የተከናወነው የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ ስርዓት፣  

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ “ካህናት በክህነታዊ አገልግሎታቸው ለምእመናኑ ይበልጥ ቅርብ መሆን ይኖርባቸዋል”።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማሕበረሰቦች ዘንድ አምና ሚያዝያ 10/2011 ዓ.ም. የጸሎተ ሐሙስ ሥነ ስርዓት መከናወኑ ይታወሳል። ሥነ ሥርዓቱ በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚልካ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመሩት የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት መከናወኑ ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ ያደረጉት አስተንትኖ ትርጉም ሙሉ ይዘት የሚከተለው ነበር፦

“የተወደዳችሁ የሮም ሀገረ ስብከት ካህናት እና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሀገረ ስብከቶች የተወጣጣችሁ ካህናት!

በዛሬው እለት ስርዓተ አምልኮ የተነበቡትን ምንባባት፣ በተለይም በኦሪት ዘዳግሞ መጽሐፍ ውስጥ በአጽኖት የተገለጸው “በምንጠራው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር  ለእኛ ቅርብ እንደሆነ አማልክቱ የሚቀርቡት ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማነው?” (ኦ. ዘዳግም 4: 7) በአእምሮዬ አንድ ነገር ትዝ እንዲለኝ አድርጎኛል። የእግዚኣብሔር ቅርብ መሆን . . . የእኛ ሐዋርያዊ ቅርብነት።

በነቢዩ ኢሳያስ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር መልእክተኛውን አስቀድሞ በሕዝቡ መካከል እንዲሆን፣ ለድሆች፣ ለታመሙ፣ ለእስረኞች ቅርብ ይሆን ዘንድ “ቀብቶ እንደ ላከው” መንፈስ ቅዱስ በእርሱ ላይ እንደ ሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ፊት እንደ ሚመራው እና ከአገልጋዩ ጋር በጉዞ ላይ አብሮት እንደሚሆን የሚገልጸውን መልእክት እናገኛለን።

በመዝሙረ ዳዊት በምዕራፍ 88 ላይ እግዚኣብሔር ከልጅነቱ ጀምሮ ንጉሥ ዳዊትን በእጁ ይዞት ይመራው እንደ ነበረና የእግዚኣብሔር ክንድ ሁል ጊዜም ከእርሱ ጋር እንደ ነበረ፣ አሁን ደግሞ በስተ እርጅናው በሕይወቱ ሂደት ውስጥ እግዚኣብሔር ለእርሱ ቅርብ እና ታማኝ በመሆኑ የተነሳ እርሱም በስተ እርጅናው ታማኝ የሚለውን መጠሪያ ለማግኘት ችሏል።

በዮሐንስ ራዕይ ላይ ደግሞ ከጌታ ጋር ተጨባጭ ግለሰባዊ የሆነ ቅርበት በመፍጠር ከእርሱ ጋር ሕብረት እንድንፈጥር ይጋብዘናል። "እርሱን የሠቀሉትም እንኳ" ሳይቀር እርሱን እንደ ሚያዩት የሚያመለክተው የትንሳኤ ጌታ፣ ቁስሉ ምንጊዜም የሚታይ እንደሆነ እንዲሰማን ያደርገናል፣ እኛ ለእርሱ ቅርብ ለመሆን በምንፈልግባቸው ጊዜያት ሁሉ እርሱ እኛን ሊገናኘን እንደ ሚመጣ፣ በሥጋዊ ቁስል ለሚሰቃዩ፣ በተለይም ለሕጻናት ቅርብ ለመሆን ሁሌም እንደ ሚመጣ ይገልጽልናል። በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በማዕከላዊነት የተገለጸው ከጌታ ጋር የነበሩ ሰዎች “ትኩር ብለው እርሱን ይመለከቱ እንደ ነበረ” (ሉቃስ 4:20) የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናሰላስላለን። ኢየሱስ በናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ውስጥ ለማንበብ ተነሳ፣ የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል”(ኢሳያስ 61፡1) ንባቡን ያጠቃለለው ይህ ቃል እርሱን የሚያመለክት እንደ ሆነ በመግለጽ “እርሱም፣ “ይህ በጆሮአችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” (ሉቃስ 4፡21) ይላቸው ጀመር።

ኢየሱስ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመክፈት እንደ አንድ የሕግ መምህር ማንበብ ጀመረ። እርሱ አንድ የሕግ መምህር ወይም የሕግ ጸሐፊ የመሆን ችሎታ ነበረው ነገር ግን “ወንጌላዊ” መሆን ፈለገ፣ በየመንገዱ እየተዘዋወረ የሚሰብክ ሰው መሆን ፈለገ፣ ነብዩ ኢሳያስ (52:7) እንደ ገለጸው በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራች ይዘው የሚመጡ እግሮች እንዴት የሚያምሩ ናቸው? እንዳለው ሁሉ ኢየሱስም “መልካሙን ዜና” ለሕዝቡ እየተዘዋወረ መስበክ ፈለገ።

ይህ የእግዚአብሔር ምርጥ የሆነ ምርጫ ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ቅርብ የሆነ ሰው እንዲሆን መርጦታል። ሠላሳ አመታት የተደበቀ ሕይወት! ከዚያ በኋላ መስበክ ይጀምራል። ቃል ሥጋ የሆነበትን ምስጢር የማስተማር ዘዴ፣ ባሕልን በማዋሃደ የማስተማር ዘዴ፣ በእያንዳንዳችን ቁምስናዎች ውስጥ፣ አሁን ባለው በወጣቱ ትውልድ ባሕል ውስጥ ዘልቆ የሚገባ የማስተማር ዘዴ።

ለሰዎች ቅርብ መሆን ከአንድ የተወሰነ በጎነት በላይ የሆነ ተግባር ነው። ይህም በአጠቃላይ የግለሰብን፣ ከእርሱ ጋር ግንኙነት የመፍጠሪያ ሁኔታውን፣ በተመሳሳይ መልኩም እርሱ በራሱ መንገድ ላይ በቀጣይነት የሚጓዝ እና ለሌላ ሰው ትኩረት የመስጠት ባሕሪን ያጠቃልላል። ብዙን ጊዜ ሰዎች አንድ “ካህን” ለሕዝቡ ቅርብ መሆኑን በሚገልጹበት ወቅት ሁለት ነገሮች ላይ ተመስርተው ነው። በቅድሚያ “እርሱ በፍጹም በቦታው ተገኝቶ አያውቅም፣ እንዲያውም አንዳንዴ ‘አባ እርሶ እኮ በጣም በሥራ የተወጠሩ ሰው ስለሆኑ በፍጹም በሥራዎ ቦታ አይገኙም’ ከሚለው በተቃራኒው የሚገኘው “ሁል ጊዜም በቦታው ይገኛል” የሚለውን የሚያሰማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለእያንዳንዱ ሰው የሚሆን ቃል እንዴት መናገር እንደ ሚገባው የሚያውቅ “ከሁሉም ጋር የሚነጋገር፣ ከትላልቆች፣ ከትናንሾች፣ ከድኾች፣ እምነት ከሌላቸው ሰዎች ጋርም ሳይቀር የሚነጋገር ሰው የሚለውን ያሰማል። ቅርብ የሆኑ ካህናት ማለት ከሁሉም ጋር መግባባት፣ መነጋገር የሚችሉ፣ በየመንገዱ እየተዘዋወሩ ከሰዎች ጋር የሚገናኙ ካህናት ማለት ነው።

በመንገድ ላይ ቅዱስ ወንጌልን እንዴት መስበክ እንደ ሚገባ ከኢየሱስ ከተማሩ ሰዎች መካከል ፊልጶስ አንዱ ነበር። “በየከተማው እየተበታተኑ በሄዱበት ሁሉ ቃሉን እና መልካም የሆነውን ዜና ሰበኩ፣ ከዚህ የተነሳም በከተማዪቱ ታላቅ ደስታ ሆነ” (የሐ.ሥራ 8:4-8)። በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ስብከተ ወንጌል ካደርጉ ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ፊልጶስ ነበር። መንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ ወንጌልን እንዲሰብክ ወደ መራው ወደ ማንኛውም ሥፍራ በመጓዝ ይሰበክ ነበር። ከአንድ ቦታ ወደ ሌላም ይዘዋወር ነበር። የንግሥቲቷ ቧለሟል የነበረውን ኢትዮጲያዊውን ጃንደረባ እንዳጠመቀ ሁሉ መልካም ፈቃድ እና መልካም የሆነ እምነት ያላቸውን ሰዎች እየተዘዋወረ፣ መንፈስ ቅዱስ በሚመራው ሥፍራ ሁሉ እየተገናኘ መንገድ ለመንገድ እየሄደ ያስተምር፣ ያጠምቅም ነበር (የሐ. ሥራ 8፡5. 36-40)።

ለሕዝቡ ቅርብ መሆን ቅዱስ ወንጌልን በማወጅ ሂደት ውስጥ በጣም ወሳኝ የሚባል ቁልፍ የሆነ ሚና ይጫወታል። ለሕዝቡ ቅርብ መሆን ምሕረትን በማስገኘት ሂደት ውስጥ ቁልፍ የሆነ ሚና ይጫወታል። ምክንያቱም ርቀትን ለማስወገድ “መልካም ሰው እንደ ነበረው ሳማሪዊ” ለሕዝቡ ቅርብ በመሆን ምሕረትን ማስገኘት ይገባል። ለሕዝቡ ቅርብ መሆን እውነትን ለማግኘት ቁልፍ የሆነ ሚና እንዳለው መገንዘብ እንዳለብን አማናለሁ። በእውነት አማካይነት ርቀትን ማስወገድ ይቻላል ወይ? አዎን በሚገባ ይችላል። እንደ እውነቱ ከሆነ እውነት ማለት አንድን ሁኔታን ለመግለጽ የምንጠቀምበት እና ቦታዎችን እና ርቀቶችን ለመጥቀስ ምክንያትዊ በሆነ መልኩ የምንጠቀምበት ትርጉም ማለት ብቻ አይደለም።  እውነት ማለት ታማኝ መሆን ማለት ጭምር ሲሆን ይህም ጌታ እንዳደረገው የሰዎችን ነባራዊ ሁኔታ ሳንመለከት እያንዳንዱን ሰው በየስማቸው መጥራት መቻል ማለት ነው።

የተወሰኑ ተጨባጭ እውነቶችን ብቻ እንደ ጣዖታት አድርገን የመሥራት ፈተና ውስጥ እንዳንገባ መጠንቀቅ አለብን። እነሱ ትልቅ ክብር እና ኃይልን የሚሰጡ እና ለመገንዘብ አስቸጋሪ የሆኑ ምቹ፣ ጣፋጭ ጣዖታት ናቸው። "እውነተኛው ጣዖት" በስውር የወንጌልን ቃላት እንደ ልብስ እንድንለብስ በማድረግ የወንጌል ቃላት ልብን እንዳይነኩ ያደርጋል። እናም ከእዚህ የከፋ ጉዳይ ደግሞ፣ ተራው ሕዝብ ከቃሉ እና ከክርስቶስ ምስጢራት እንዲርቅ በማድረጉ ላይ ነው፣ የከፋውም ጉዳይ ይህ ነው።

በእዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ ከሆንን ደግሞ የካህናት እናት ወደ ሆነችው ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም መመልከት ይኖርብናል። “አንድ እውነተኛ የሆነች እናት፣ ከእኛ ጋር አብራ የምትጓዝ እናት፣ ከእኛ ጋር ሆና የምትታገል እናት፣ ያለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለእኛ ቅርብ ይሆን ዘንድ የምታግዘን እናት” የሆነችውን ማርያም “የቅርብ እናታችን” ብለን ልንጠራትም እንችላለን። በዚህም መልኩ ማንም ሰው ከእዚህ ውጪ ሳይሆን ለእርሱ ቅርብ እንዲሆን ማድረግ ትችላለች። የእኛ እናት በዚህ "እንክብካቤ" አማካኝነት እኛ ወደ አገልግሎት እንድንቀርብ ብቻ የምታደገን ሳይሆን ነገር ግን በተጨማሪም በእዚሁ ተመሳሳይ ቅርበት ወደ ሕዝቡ እንድንቀርብ እና ነገሮችን በቅርበት መናገር እንድንችል ትረዳናለች። በቃና ዘገሊላ የሠርጉ ግብዣ ላይ የወይን ጠጅ ባለቀባቸው ጊዜ “እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” ያለችበት ቋንቋ ትልቅ አብነት በመሆኑ የተነሳ የቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ሆኖ ቀርቷል። ነገር ግን እንደ እሷ ለመናገር ፀጋን ከመጠየቅ በተጨማሪ አስፈላጊዎቹን ነገሮች "እያንዳንዳችን" ለእያንዳንዱ ልብ፣ ቤተሰብ፣ ሁሉንም ባሕል ከግምት ያስገባ ቅርበት ልንፈጥር ይገባል። በዚህ ዓይነት አቀራረብ ብቻ ነው አንድ ሰው ምን እንደሚጎድለው እና ጌታ ሊሰጠው ከሚገባው ነገሮች ውስጥ አስፈላጊ እና መልካም የሆነው የቱ እንደ ሆነ መለየት የሚቻለው፣ ለሕዝቡ ቅርብ ሲንሆን ብቻ ነው።

በመቀጠልም ክህነታዊ ቅረበት መፍጠር የሚያስችላችሁን ሦስት ቃላት ወይም ሀረጎችን ለመጠቆም እፈልጋለሁ “ኢየሱስ የሚላችሁን ነገሮች ሁሉ አድርጉ” ይህንንም በተለያዩ ከሺህ በላይ በሚቆጠሩ መንገዶች ለማስተጋባት የምትችሉ ሲሆን፣ ነገር ግን በእዚህ አግባብ ትኩረት ማድረግ የሚገባችሁ የምትናግሩትን ሰው ልብ በሚነካ መልኩ፣ በእናትነት ባሕሪይ የተሞላ ንግግር፣ በመንፈሳዊ ሕይወት በሚደርገው ጉዞ አብራችሁ በመጓዝ በንስሐም ይሁን በስብከተ ወንጌል ተግባራችሁ ሁሉ ለሰዎች ቅርብ ሁኑ።

የመጀመሪያው ሰዎችን በመንፈሳዊ ውይይቶች አማካይነት መቅረብን በተመለከተ፣ ጌታ ራሱ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር አድርጎት የነበረውን ውይይት ማስላሰል እንችላለን። ጌታ በቅድሚያ ይህቺን ሳማሪዊ የሆነች ሴት በመንፈስ እና በእውነት እንዴት ማምለክ እንዳለባት አስተማራት። ከእዚያም ቀስ በቀስ ለሰራችው ኃጢኣት መጠሪያ ሰጠ፣ በስተመጨረሻም በእርሱ ስብከተ ወንጌል መንፈስ ውስጥ እንድትገባ በማድረግ ወደ መንደሩ ሂዳ በመንደሩ ለሚገኙ ሰዎች ቅዱስ ወንጌልን ለመስበክ በሄደችበት ወቅት በመንፈስ አብሯት ሄደ። ይህ ጌታ ያሳየን መንፈሳዊ ውይይት ተምሳሌት የሳምራዊቷን ኃጢአት በማጋለጥ በእርሷ አምልኮ ላይ ጥላ አላጠላም። በእርሷ የስብከተ ወንጌል ተልዕኮም ላይ ተጽዕኖ አለፈጠረም ነበር።

በሁለተኛ ደረጃ በምስጢረ ንስሓ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መቅረብን በተመለከተ ደግሞ ስታመነዝር በተገኘችው ሴት ታሪክ ላይ ማሰላሰል እንችላለን። በእዚህም ረገድ የሚደረገው ቅርበት በጣም ወሳኝ የሚባል ቅርበት ሲሆን በኢየሱስን ፊት ቀርበው ሁል ጊዜ እውነቱን መናገር በጣም ወሳኝ እንደ ሆነ በግልጽ ያሳያል። ስታመንዝር የተገኘችውን ሴት በኢየሱስ በፊቱ አምጥተው ባቆሙበት ወቅት ተንበርክኮ ወይም ቁጭ ብሎ ከነበረበት ቦታ ተነስቶ በመቆም ፊት ፊቷን ከተመለከተ በኋላ “እኔም አልፈርድብሽም” (ዩሐንስ 8:11) እንዳላት ሁሉ የሌሎችን ፊት መመልከት ያስፈልጋል። ይህም ሕግን ማፍረስ ማለት አይደለም። ነገር ግን በእዚህ ላይ “ ከእዚህ በኋላ ደግመሽ ኃጢኣት እንዳትሰሪ” ማለት ግን የሚቻል ሲሆን ይህንን የምናደርገው ልክ በአንድ ፍርድ ቤት እንደሚደርገው ዓይነት፣ ኃይል በተቀላቀለው ድምጽ ማድረግ ሳይሆን የሚጠበቅብን ነገር ግን የድምጻችን ኃይል የእግዚኣብሔርን መለኮታዊ ምሕረት በሚያንጸባርቅ መልኩ ሊደረግ ይገባዋል። ሰዎችን በእውነት ወደ እመንት የሚያመጣ ሊሆን ይገባዋል። ይህም ኃጢኣተኛውን ሰው ማትረፍ ይችላል። ትክክለኛው የድምጽ አወራረድ በመጠቀም “በድጋሚ ኃጢኣት አትሥራ” የሚለው ቃል አንድ ምስጢረ ንስሓ የሚያስገባ ካህን ሰባ ጊዜ ሰባት በመደጋገም የሚለው ቃል ሊሆን ይገባዋል።

ሦሰተኛው እና የመጨረሻው በስብከተ ወንጌል አማካይነት ሕዝቡን መቅረብ የሚለው ነው። ይህንን በተመለከተ ደግሞ በበዓለ ጴንጤ ቆስጤ ወቅት በተደርገው በመጀመሪያው የሐዋሪያው ጴጥሮስ ስብከት ላይ ማሰላሰል ይገባል። ሐዋርያ ጴጥሮስ የእግዚኣብሔር ቃል “የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ጌታ አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው፣ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነውና”(የሐዋሪያት ሥራ 2፡37) በማለት እና ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ልባቸው እጅግ ተነክቶ፤ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፤ ታዲያ ምን እናድርግ?” ብለው እስኪጠይቁ ድረስ ኃይል የነበረው ስብከተ ወንጌል ነበር። ይህም በሕዝቡ የተነሳው ጥያቄ ነገሮችን እንዴት እንደ ምንገልጽ፣ ነገሮችን እንዴት እንደ ምናከናውን እና ለምን ዓይነት ጥያቄ ምን ዓይነት መልስ መስጠት እንደ ሚገባን በሚገባ በመጥቆም ሁሉም ነገር ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድናመራ ማድረግ የሚችል እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል። ስብከተ ወንጌል በጣም ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሲሆን ይህም አንድ ካህን ለእዝቡ ምንኛ ቅርብ መሆኑን እና አንድ ካህን ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበት ወሳኝ የሆነ የመገናኛ መስመር ነው። በስብከተ ወንጌል ውስጥ እኛ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ምን ያህል እንደቀረብን እና በሕዝባችን እለታዊ ኑሮ ውስጥ ምን ያህል ቅርብ መሆናችንን እናያለን።

አንድ ካህን በማንኛውም መስፈርት ለሕዝቡ ቅርብ ሊሆን ይገባዋል፣ በሕዝቡ መካከል ሊጓዝ ይገባዋል፣ መልካም እረኛ ያለውን ዓይነት ርኅራኄ ሊኖረውም ይገባል፣ ሕዝቡም ይህንን በሚመለከትበት ወቅት አንድ ለየት ያለ ነገር እንዳለ ይገነዘባል፣ በካህኑ ውስጥ ኢየሱስ እንደ ሚገኝ ሊመለከት ይችላል።

“ቅርብ እንድንሆን የምትረዳን” እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ለእኛ ሁል ጊዜ ቅርብ እንድትሆን እና “ኢየሱስ የሚለንን ነገር ሁሉ በተግባር ላይ እንድናውል እንድትረዳን በልዩነታችንም ውስጥ ሳይቀር ለሰዎች ቅርብ መሆን የምንችልበትን እንደ እርሷ “እንዳልከኝ ይሁንልኝ!” ማለት እንድንችል እና ሁሌም ቢሆን ለኢየሱስ ቅርብ መሆን እንችል ዘንድ በአማላጅነቷ እንድትረዳን ልንማጸናት ይገባል”።

25 April 2019, 17:01