ር.ሊ.ጳ ፍራነችስኮስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበትን 6ኛ አመት አከበሩ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 04/2011 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበትን 6ኛ ዓመት አከበሩ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በታኅሳስ 17/1936 ዓ.ም የአርጄንቲና ዋና ከተማ በሆነችው በቦይነስ አይረስ መወለዳቸው የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የ82 አመት ባለጸጋ የሆኑ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።
የዚህ ዘገባ አዘጋጅ እና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ በስድስት አመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ሚስዮናዊ የሆነ ተግባሯን አጠናክራ እንድትቀጥል እና ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ እንድታበስር፣ በማነኛውም የቅዱስ ወንጌል የማብሰር ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በመፍቀድ ማከናውን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው አበክረው መናገራቸው እና አሁንም ቤተ ክርስቲያን በእዚሁ መንገድ እንድትቀጥል ማሳሰባቸውን በፍጹም አላቋረጡም።
ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስድስት ዓመታት ውስጥ በላቲን ቋንቋ Lumen Fidei በአማሪኛው “የእመንት ብርሃን” የተሰኘ እና በእምነት ዙሪያ ላይ ያጠነጠን ሐዋርያዊ መልእክት እንዲሁም Laudato si በአማሪኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በሚል አርእስት የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን የመንከባከብ ኃላፊነት ሁላችንም እንዳለብን በማስመልከት የጻፉት ደግሞ ሁለተኛው ሐዋርያዊ መልእክታቸው እንደሆነ ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእነዚህ ስድስት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ሦስት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳኖችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም በላቲን ቋንቋ “Evangelii Gaudium” በአማሪኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” በሚል አርእስት እ.አ.አ በኅዳር 24/2013 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ተልዕኮዋን ለማከናወን እና ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ነው።
በሁለተኛነት ደግሞ አሁንም በላቲን ቋንቋ “Amoris Laetitia” በአማሪኛው “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት እ.አ.አ. በመጋቢት 19/2016 ዓ.ም ለንባብ ያበቁት ቃለ ምዕዳን ሲሆን ይህ ቃለ ምዕዳን በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር፣ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለቤተሰብ ማድረግ ሰለሚጠበቅባቸው ሐዋርያዊ እንክብካቤ የሚያወሳ ድህረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል። በእዚህ ቃለ ምዕዳን በተለይም የሐይማኖት አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በጥንቃቄ እና ብስለት በተሞላበት መልኩ፣ በጥንቃቄ በመመርመር በቤተሰብ ውስጥ የሚያግጥሙ ችግሮችን በችኮላ ከማውገዝ ይልቅ በእግዚኣብሔር ምሕረታዊ ጸጋ በመታገዝ የመፍትሄ ሐሳቦችን መጠቆም እንደ ሚገባቸው እና ይህንንም ክህሎት ቀሳውስት ማዳበር እንዲችሉ ቤተሰብን የተመለከተ ትምህርቶች ከዘረዐ ክህነት ጀምሮ መስጠት አስፍላጊ መሆኑን የሚገልጽ ቃለ ምዕዳን ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእነዚህ ስድስት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ ለንባብ ያበቁት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን እ.አ.አ በመጋቢት 19/2018 ዓ.ም በላቲን ቋንቋ “Gaudete et Esultate” በአማርኛው “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት ለንባብ ያበቁት ቃለ ምዕዳን ሲሆን ይህ ቃለ ምዕዳን “በአሁኑ ዓለማችን ውስት የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ወደ ቅድስና መንገድ እንዲመለሱ የሚጋብዝ ጥሪ” የተካተተበት መልእክት ሲሆን በአሁኑ ዘመን በሚገኘው ዓለማችን ውስጥ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን፣ የተለያዩ የሕይወት ተግዳሮቶች እየገጠሙዋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም አሁን ባለው ዓለማችን ውስጥ ያለውን መልካም እድል መጠቀም ያልቻላችሁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ልጆቻችሁን በታላቅ ፍቅር ተንከባክባችሁ እያስደጋችሁ የምትገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ ለቤተሰባችሁ የሚሆን እንጀራ በእየለቱ ለማግኘት የምትኳትኑ፣ የምትለፉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ የምትሰሩ የማኅበረስብ ክፍሎች፣ በእድሜያችሁ ዘመኑ ሁሉ ለራሳችሁ፣ ለቤተሰባችሁ ለአገራችሁ፣ በአጠቃላይ ለማኅበረሰቡ መልካም የሆነ ተግባር ያከናወናችሁ አረጋዊያን ሁላችሁ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” የሚል መልእክት የሚያስተላልፍ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ነው። ይህ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ቃለ ምዕዳን ሲሆን በምዕራፍ አንድ በአሁን ወቅት ባለው ዘመናዊ ዓለማችን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች እግዚኣብሔር ለእነርሱ ስላቀረበው የቅድስና ጥሪ ያመለክታል። በምዕራፍ ሁለት ላይ ደግሞ ሁለት ቀንደኛ የቅድስና ጠላቶች የሚላቸውን ያትታል። በምዕራፍ ሦስት በጌታ ብርሃን እይታ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ተቀምጡዋል፣ በምዕራፍ አራት ላይ ደግሞ በዛሬው ዓለማችን ውስጥ የሚታዩ የቅድስና ምልክቶች የምል አርእስት የተሰጠው ሲሆን በአምስተኛው እና በመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ መንፈሳዊ ውጊያ ማድረግ፣ ነቅቶ መጠበቅ እና በማስተዋል ጥበብ የተሞላ ውሳኔ ማድረግ በሚል አርእስት ስፊ ትንታኔ ይዞ ቀርቡዋል። በአጠቃላይ ይህ “ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ” በሚል አርእስት ቅዱስነታቸው ለንባብ ያቀረቡት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ይቅርታ፣ እባክህን እና አመሰግናለሁ የሚሉትን ሦስት በጣም ቀለል ያሉ ቃላትን በእለታዊ ኑሮዋችን ውስጥ በመጠቀም ወደ ቅድስና የሚወስደውን መንገድ መጀመር እንደ ሚቻል በሰፊው የሚተነትን ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በእነዚህ ስድስት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው 27 የሚሆኑ በላቲን ቋንቋ “Motu proprio” በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል) በእዚህም መሰረት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ግላዊ ተነሳሽነት 27 መልእክቶች መጻፋቸው ይታወቃል። እነዚህ በእርሳቸው የግል ተነሳሽነት የተጻፉ 27 መልእክቶች ወይም ባላቲን ቋንቋ “motu proprio” ሞቱ ፕሮፕሪዮ መልእክታቸው “የቅድስት መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች መማክርት ጥልቅ የሆነ ታዐድሶ እንዲያደርጉ የሚያሳስቡ መልእክቶች፣ በቅድስት መንበር ውስጥ በተለይም ደግሞ በፋይናንስ እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያሳስቡ መልእክቶች፣ በአንድ ባል እና በአንድ ሚስት መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን እንዴት ለመፍታት እንደ ሚቻል--ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማስቀመጥን የተመለከተ መልእክት፣ ለስርዓተ አምልኮ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ መንፈሳዊ መጽሐፍት በእየአንዳንዱ ሀገር ብጹዕን ጳጳሳት እውቅና አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚመጣጠን መልኩ ውጤታማ እንዲሆኑ ክለሳ እንዲደረግባቸው የሚጠይቅ መልእክት፣ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ አርእስቶችን ያቀፉ 27 ሞቱ ፕሮፕሪዮ በራሳቸው ተነሳሽነት በጣም ተጨባጭ እና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን በማንሳት ለመፍትሄ ማቅረባቸው ያታወቃል።
ቅዱስነታቸው በእነዚህ ስድስት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ውስጥ ቤተሰብን በተመለከት ሁለት ጳጳሳዊ ሲኖዶሶች እንዲደረጉ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ወቅታዊ በሆነ መልኩ በቤተሰብ መካከል አሁን የሚታዩ ተግዳሮቶችን በማንሳት እና ትኩረት በመስጠት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት በቤተሰብ ጉዳይ እንዲመክሩ በማድረግ ወቅታዊ ለሆኑ ችግሮች ወቅታዊ የሆነ ምላሽ በሀገረ ስብከት ደረጃ የሚሰጥበትን የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲቀይስ በር መክፈታቸው ይታወሳል።
ከታኅሳስ 01/2008 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 11/2009 ዓ.ም. ደርስ ለ349 ቀናት ያህል የቆዬው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤልዩ ማወጃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን ልዩ ቅድሱ የምሕረት ዓመት በወቅቱ በክርስቲያኖች እና በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በተነሳው እርስ በእርስ ግጭት ተጎሳቁላ በነበረች ሀገር በመገኘት የሁለቱንም የሐይማኖት ተቋማት ተወካዮች በአንድነት ፊት ለፊት አቀራርበው በማናጋገር እርቅ እንዲፈጥሩ መንገዱን በመክፈት በእዚያው በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በባንጉዊ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ተገኝተው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤሊዪን ማስጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም 349 ቀናት ውስጥ ምዕመናን መንፈሳዊ እና አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚፈጸሙበት ወቅት መሆኑን ገልጸው፣ በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ክርስቲያኖች እርቅን እና ሰላምን ይፈጥሩ ዘንድ ማሳሰባቸው ይታወቃል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስድስት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጣሊያን ውጭ 27 ሐዋርያዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በአፍሪካ አእጉር የሚገኙትን ኬኒያን፣ ሁጋንዳን እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ አንስቶ በኩባ በአሜሪካ፣ በላቲን አመሪካ በምስራቅ አውሮፓ እና በኤሺያ አህጉር፣ በመካከለኛው አሜሪካ እና በተባበሩት የአረብ ሔምሬትስ ዋና ከተማ የሆነችውን አቡዳቢን ድረስ በመጓዝ የሰላም እና የአንድነት መልእክት ማስተላለፋቸው የሚታወቅ ሲሆን 900 የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባትን አዛረበጃንን ጨምሮ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ወደ ሆኑባቸው ባንግላዲሽ እና የቡዳ እመንት ተከታይ ወደ ሚበዛባት ማያን ማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) ድረስ በመሄድ፣ በቅርቡ ደግሞ የተባበሩት አረብ ሔምሬትስ ዋና ከተማ ወደ ሆነችው አቡዳቢ በመሄድ የሰለም እና የአንድነት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በጣሊያን ውስጥ ብቻ 17 የጣሊያን ግዛቶችን በተለይም ደግሞ በተፈጥሮ አደጋ ለምሳሌም በርዕደ መሬት አደጋ ጉዳት የደረሱባቸውን እና ከአፍሪካ እና ከተለያዩ አገራት የተውጣቱ ስደተኞ ወደ አውሮፓ አህጉር መግቢያ በር አድርገው የሚጠቀሙበትን የላፓዱዛ ዴሰትን ጭምር በመጎብኘት ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ሰብዐዊ መብታቸው እንዲከበር ለዓለም ድምጻቸውን ማሰማታቸው እና ዓለም ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ስደተኞችም በበኩላቸው በእንግድነት የሚቀበሉዋቸውን ሀገሮች ማሕበራዊ ሕግጋቶችን በማክበር እንዲኖሩ፣ በእንግድነት የተቀበላቸውን ማኅበረሰብ ወግ እና ባሕል እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእነዚህ ስድስት የርዕሳነ ሊቃነ ጵጵስና አገልግሎታቸው ዘወትር ረቡዕ እለት ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ 9 ልዩ ልዩ አርእስቶችን በስፋት በመዳሰስ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ማደረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ የጠቅላላ የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ “የእመታችን መገለጫ ከሆነው የጸሎተ ሐይማኖት አንስተው ሰባቱን ምስጢራት፣ የመንፍስ ቅዱስ ስጦታዎችን የተመለከቱ፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቤተሰብን፣ ምሕረትን፣ የክርስቲያን ተስፋን እና በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ዙሪያ እና በቅርቡ “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ በተከታታይ እያደረጉት በሚገኘው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ጉዞ በመንፈሳዊነት እንዲጓዙ የሚያበረታቱ አስተምህሮዎችን ማደርጋቸው ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በስድስት ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ ባሳረጉዋቸው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ከ650 በላይ ስብከቶችን ማደርጋቸው የሚታወስ ሲሆን የስብከታቸው አጠቃላይ ይዘት በእለቱ በሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ላይ ባተኮረ መልኩ “ክርስትያኖች በሕይወት ጉዞዋቸው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች መጋፈጥ እንጂ መሸሽ የለባቸውም” የሚል አጠቃላይ እንድምታ ያላቸው ስብከቶች እንደ ሆኑ ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ at
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ተተኪ በመሆን የዛሬ ስድስት አመት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው መመረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በትውልድ አርጄንቲናዊ የሆኑ የ83 አመት እድሜ ባለጸጋ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ምዕረጋቸውን ከመቀበላቸው በፊት የነበራቸውን ካርዲናል በርጎሊዮ የሚለውን የመጠሪያ ስማቸውን በመቀየር በ13ኛ ክፍለ ዘመን የኖረውን እና “የድሆች አባት” በመባል የሚታወቀውን የአዚዚውን የቅዱስ ፍራንቸስኮ ፈለግ ለመከተል በማሰብ የእርሱን የመጠሪያ ስም የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን መጠሪያ እንዲሆን መምረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መስረት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም በሯን ክፍት ያደርገች፣ ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ ማወጅ እና ማብሰር እንደ ሚገባት ምኞታቸው መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጻቸው ይታወቃል።
“ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም የሰው ልጆች ማስተናገድ የሚትችል የሰው ልጆችን እንደ ሕይወታቸው ፈተና እና ድካም ቦታ ልትሰጣቸው የምትችል ቤተ ክርስቲያን እንደ ሚመኙ መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን በጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ መሆን ይገባታል፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ የሕይወት ጫናዎች ምክንያት ከቆሰሉ ሰዎች ጋር በመሆን የፈውስ ሂደት አካል ልትሆን ይገባታል የሚል ጽኑ አቋም እንደ ሚያንጸባርቁ ያታወቃል። “አንድ በምቾት ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን በራሷ ምቾት ብቻ ራሱና ቆልፋ የምትኖር ከሆነ ያቺ ቤተ ክርስቲያን ጤናማ ቤተ ክርስቲያን ልትባል አትችልም” በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የመሳሰሉ አሉታዊ ባሕርይ ያልቸው አብያተ ክርስቲያናት ይህንን አፍራሽ የሆነ ባሕሪይ በማስወገድ ሰውን ከእግዚኣብሔር ለማገናኘት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በመወጣት በእምነት የሚገኘውን ውበት እና ደስታ ለሰው ዘር በሙሉ ማሳየት እንደ ሚኖርባት ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ Evangelii Gaudium በአማሪኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ”በሚል አትእስት በጻፉት ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን ለማከናወን እና ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያንን መንፈስ ቅዱስ እንድያስገርማት መፈቅድ ይገባታል የሚል ጭብጥ ያዘለ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በቀጣይንት ድምጹዋን እንድታሰማ እና አዳዲስ ነገር በቤተ ክርስቲያን እንዲከሰት የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ስለ ሆነ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን እንድያንቀሳቅስ ልንፈቅድለት ይገባል የሚል አጠቃላይ የሆነ ምልእክት የያዘ ቃለ ምዕዳን ነው።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚህ በስድስት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በዋነኛነት እና በማዕከላዊነት “ምሕረት” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ መጠቀማቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት “የሰማይ አባታችሁ መሐሪ እንደ ሆነ እናንተም ምሕረት አድራጊዎች ሁኑ” የሚለው የክርስቲያኖች የእለት ተእለት መፈክር ሊሆን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ ማስታወሳቸው ይታወሳል። ሁላችንም የመጨረሻ ቀን ፍርድ እንደ ሚጠብቀን በመጨረሻው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመለአክቱ ጋር በዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ በጎቹን ከፊየሎቹ በመለየት በማቴዎስ ወንጌል 25 እንደ ተጠቀሰው “ተርቤ አብልታችሁኛል፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛል፣ ታርዤ አልብሳችሁኛል፣ እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል. . .” ወዘተ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያቀርብልን ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከአሁኑ መዘጋጀት ይኖርብናል በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን በመጨረሻው ሰዓተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠን ፍርድ አሁን በሕይወት እያለን በምናከናውነው የምሕረት ወይም የበጎ አድራጎት ተግባር ላይ በተመሰረተ መልኩ በመሆኑ ከአሁኑ በጎ ተግባራርትን ማከናወን ይኖርብናል በማለት መናገራቸውም ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእነዝህ ስድስት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በቤተ ክርስቲያን የቀሳውስት ብቻ ሳትሆን መላው ምዕመን በተገቢው መልኩ ይሳተፍ ዘንድ መፍቀድ እንደ ሚገባ በተደጋጋሚ ማሳሰባቸው የሚታወቅ ሲሆን ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ሚና በሚገባ እንዲወጡ ማስቻል ያስፈልጋል፣ በማነኛውም የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች ውስጥ ምዕመናን በትኩረት እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም እንዳላቸው ይታወቃል። በተለይም ደግሞ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ስላላቸው ይህንን አዎንታዊ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ መፍቀድ ያስፈልጋል በማለት በተደጋጋሚ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ማርያም ከኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት በላይ እንደ ነበረች በማንሳት ሴቶች ለቤተ ክርስቲያን ሊያበረክቱት የሚችሉትን ከፍተኛ አስተዋጾ ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ መገለጻቸው ይታወሳል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእነዝሁ ስድስት አመታት የጵጵስናቸው ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ መጫወት እንደ ሚገባቸው በመገለጽ ክርስቲያኖች በመንፍስ ቅዱስ በመሞላት ቅዱስ ወንጌልን “በድፍረት፣ ጮክ ብሎ እና በማነኛውም ጊዜ እና ቦታ ለማወጅ መዘጋጀት ይገባቸዋል ማለታቸውም የሚታወስ ሲሆን “በተለይም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በስቃይ ላይ የሚገኙትን ሰዎች ተጨባጭ በሆነ መልኩ በማገዝ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ በማድረግ ተስፋቸው እንዲለመልም የሚያደርጉ የምሕረት ተግባራርትን ማከናወን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወቃል።