ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራነስኮስ፦እግዚ/ር አባት መሆኑን የሚያምኑ ሁሉ በእርሱ በመታመን መጸለይ ይኖርባቸዋል

ር.ሊ.ጳ ፍራቸስኮስ፦እግዚ/ር አባት መሆኑን የሚያምኑ ሁሉ በእርሱ በመታመን መጸለይ ይኖርባቸዋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት በኅዳር 26/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉት የጠቅላላ የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ መሰረቱን ያደርገ የክፍል አንድ አስተምህሮ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን “ኢየሱስ ጸሎት መጸለይ እንዲይስተምረን ልንጠይቀው ይገባል” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በታኅሳስ 03/2011 ዓ.ም አሁንም “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙርያ ላይ ባደርጉት የክፍል ሁለት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “አባታችን ሆይ” የሚለውን ጸሎት “በእግዚኣብሔር በመተማመን ልንጸልየው የሚገባን ጸሎት ነው” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን በታኅሳስ 24/2011 ዓ.ም አሁንም “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙርያ ላይ ባደርጉት የክፍል ሦስት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ሳትለምነው  በፊት ምን እንደ ሚያስፈልግህ  በሚያውቀው አባትህ ፊት ሆነህ ጸልይ” (ማቴ. 6፡6) የእኛ አምላክ የሆነው እግዚኣብሔር እርሱ ከእኛ ምንም ነገር አይፈልግም፣ ነገር ግን እርሱ ከእኛ የሚፈልገው አንድ ነገር ቢኖር የእርሱ በጣም ተወዳጅ ልጆቹ የሆንን እኛ፣ በጸሎት ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር ለመገናኘት የሚያስችለንን የመገናኛ መስመር ሁልጊዜ ክፍት እንድናደርግ ብቻ ነው የሚጠይቀን” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በጥር 1/2011 ዓ.ም አሁንም “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙርያ ባደርጉት የክፍል አራት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ማነኛውም ዓይነት ጸሎት ወደ እግዚ/ር ዘንድ ሳይደርስ እንዲሁ በከንቱ አይቀርም!  እርሱ እግዚኣብሔር አባት በመሆኑ የተነሳ በመከራ ውስጥ ሆነው እርሱን የሚለምኑትን ልጆቹን በፍጹም አይረሳም” ማለታቸውን የሚታወስ ሲሆን በጥር 08/2011 ዓ.ም “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ባደረጉት የክፍል አምስት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ደግሞ አባ" ማለት እግዚአብሔርን "አባት" ብሎ ከመጥራት የበለጠ ልብ የሚነካ ስሜት እንደ ሌለ ያሳየናል”  ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው ከዚያም በመቀጠል በየካቲት 06/2011 ዓ.ም አሁንም በዚሁ “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙርያ ላይ ባደርጉት የክፍል ስድስት የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ገለጹት “እውነተኛ ጸሎት ተጨባጭ የሆነና በርኅራኄ መንፈስ የተሞላ ጸሎት ሊሆን የገባዋል!” ማለታቸውንም መዘገባችን ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 13/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አሁንም “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ባደርጉት የክፍል ሰባት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ!” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላያ ያተኮረ እንደ ነበረ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን “ማንም ሰው ሊወደን በማይችል መልኩ እግ/ሔር አባታችን ይወደናል”  ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በየካቲት 20/2011 ዓ.ም አሁንም “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ ቅዱስነታቸው ያደርጉት የክፍል ስምንት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ስምህ ይቀደስ” በሚለው የመጀመሪያው የመማጸኛ ጸሎት ሐረግ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “የኢየሱስ ስም ቅዱስ እና ኃያል በመሆኑ የተነሳ ክፉ መንፈስ ተሸንፏል!” ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በየካቲት 27/2011 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያደረጉት የክፍል ዘጠኝ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አሁንም “አባታችን ሆይ!  በሚለው ጸሎት ውስጥ ባለው  “መንግሥትህ ትምጣ” በሚለው ሁለተኛው የመማጸኛ ጸሎት ሐረግ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “የጌታ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን “ጌታ ሆይ በቶሎ ና!”፣ ጌታ ሆይ መንግሥትህ ይምጣ” ብላ መጸለይ ይገባታል”፣ “መንግሥትህ ትምጣ" ማለት አንተ "በእኛ መካከል ሁን! ማለት ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

በመጋቢት 11/2011 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም “አባታን ሆይ” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ በተከታታይ ሲያደርጉት የነበረው የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል የነበረ ሲሆን በዚህ በክፍል ዐስር የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ፈቃድህ ይሁን” በሚለው “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ውስጥ በሚገኘው ሦስተኛው የመማጸኛ ጸሎት ሐረግ ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “የእግዚ/ር አባት መሆኑን የሚያምኑ ሁሉ ‘መንግሥት ትምጣ’ ብለው መጸለይ ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 11/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ከዚህ ቀደም “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ የጀመርነውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በዚሁ ጸሎት ውስጥ በሚገኘው “ፈቃድህ ይሁን” በሚለው ሦስተኛው የመማጸኛ ጸሎት ሐረግ ላይ ትኩረታችንን እናደርጋለን። ይህ የመማጸኛ የጸሎት ሐረግ የሚደገመው ከዚህ በፊት ከነበሩት ከሁለቱ ማለትም “ስምህ ይቀደስ” እና “መንግሥትህ ትምጣ” ከሚሉት የመማጸኛ ጸሎቶች በመቀጠል የሚደገም የጸሎት ሐረግ ሲሆን በዚህ መልኩ "ስምህ ይቀደስ"፣ "መንግሥትህ ይምጣ"፣ "ፍቃድህም ይሁን" የሚሉትን ሦስት መግለጫዎችን በቅደም ተከተል በአንድነት በማካተት የሚደገም ጸሎት ነው። ዛሬ በሦስተኛው የመማጸኛ ጸሎት ሐረግ ላይ እናተኩራለን።

የሰው ልጅ ዓለምን መንከባከብ ከመጀመሩ በፊት አምላክ ለሰውና ለዓለም የሚጠቀም የማያቋርጥ እንክብካቤ አድርጉዋል። መላው የቅዱስ ወንጌል አመለካከት የዚህን ሐሳብ አመለካከት መቀልበሱን ያንጸባርቃል። ኃጢአተኛው ሰው የነበረው ዘኬዎስ ኢየሱስን ለማየት ስለ ፈለገ አንድ ዛፍ ላይ ወጣ፣ ነገር ግን ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ እግዚአብሔር እርሱን እየፈለገ እንደ ነበረ ግን አላወቀም። “ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና። ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው”። በመጨረሻም ኢየሱስ “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና” (ሉቃስ 19፡5,10) በማለት ጨምሮ በአጽኖት ይናገራል። በእኛ ሕይወት ውስጥ ይፈጸም ዘንድ በመማጸን የምናቀርበው ጸሎት ይህ ነው! በኢየሱስ ውስጥ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፍቃድ ምን ነበር? የጠፋውን መፈለግ እና ማዳን ነው። እናም እኛ ይህንን የመማጸኛ ጸሎት በምናቀርብበት ወቅት የእግዚአብሔር ፍለጋ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ፣ የእርሱ አጠቃላይ የደህንነት እቅድ በቅድሚያ በእኛ ውስጥ፣ ከእዚያም ቀጥሎ ደግሞ በመላው ዓለም ውስጥ ስኬታማ እንዲሆን በመመኘት የምናቀርበው የመማጸኛ ጸሎት ነው። እግዚአብሔር እኔን እየፈለጎኝ ነው፣ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አስባችሁ ታውቃላችሁ ወይ? እያንዳንዳችን የሚፈልገን እግዚአብሔር ነው ወይ? ብለን ጥያቄ ልናነሳ እንችል ይሆናል። አዎን አንተን ይፈልጋል፣ እኔንም ይፈልጋል እያንዳንዳችንን በግለሰብ ደረጃ ይፈልገናል። እግዚኣብሔር ታላቅ ነው! ከዚህ ሁሉ ፍለጋ በስተጀርባ ያለው ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፍቅር ይሆን!

እግዚአብሔር አሻሚ አይደለም፣ ከኋላም አይሸሸግም፣ የዓለምን የወደፊት ዕቅድ አሻሚ እና በሚለዋወጥ መልኩ አላዘጋጀም። በፍጹም እንዲህ አላደረገም። እርሱ በጣም ግልጽ ነው። ይህንን የማንረዳ ከሆንን “አባታችን ሆይ” በሚለው ጸሎት ውስጥ በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠውን የመማጸኛ ጸሎት ጭብጥ ለመረዳት ያዳግተናል። በመሠረቱ መጽሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር ለዓለም ስላለው አዎንታዊ የሆነ ፈቃድ የሚናገሩ መግለጫዎችን ይዞ ይገኛል። በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ ይህንን ታማኝና ታጋሽ መለኮታዊ የሆነ የእግዚኣብሔርን ፈቃድ በተመለከተ መለኮታዊ የሆነ ምስክርነት የሚሰጡ ጥቅሶችን እናገኛለን (ቁ. 2821-2827)። ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ጢሞቴዎስ በጻፈው የመጀመርያ መልእክቱ ላይ “እግዚአብሔር ሁሉም ሰዎች እንዲድኑ እና ወደ እውነት እውቀት እንዲደርሱ ይፈልጋል” (1ጢሞ 2፡4) ይላል። ይህ በእርግጠኝነት የእግዚአብሄር ፍቃድ ነው፣ የእያንዳንዱ የሰው ልጅ መዳን። እግዚአብሔር በፍቅሩ የልባችንን በር ያንኳኳል። ለምንድነው የሚያንኳኳው? እኛን ለመሳብ፣ ወደ እርሱ ሊስበን እና በደህንነት መንገድ ላይ እንድንጓዝ ሊያደርገን። እግዚአብሔር በደህንነት መንገድ ላይ እንጓዝ ዘንድ በፍቅሩ አማካይነት እጃችንን ይዞ ለመጓዝ ለእያንዳዳችን ቅርብ ነው። ከዚህ በስተጀርባ ያለው ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ይሆን?

ስለዚህ "ፈቃድህ ይሁን” እያልን የተማጽዕኖ ጸሎት በምናደርግበት ወቅት ልክ እንደ ባርያ ራሳችንን ባዶ አድርገን በማሰብ ራሳችንን በመነቀነቅ መጸለይ አይኖርብንም። በፍጹም! እግዚኣብሔር ነጻ ሊያወጣን ይፈልጋል፣ ነጻ የሚያወጣን ደግሞ የእርሱ ፍቅር ነው። በእርግጥ "አባታችን ሆይ!" የሚለው ጸሎት የልጆች ጸሎት እንጂ የባሪያዎች ጸሎት አይደለም፣ የአባትን ልብ የሚያውቁና የእርሱን የፍቅር እቅድ የሚገነዘቡት ልጆች ብቻ ናቸው። ይህንን ጸሎት በምንጸልይበት ወቅት አስቀያሚ የሆነ እጣ ፈንታ ከፊት ለፊታችን እንደ ሚጠብቀን በማሰብ በትከሻችን ላይ እጃችንን አድርገን እኛ በፍጹም እንደ ማንለወጥ አስበን በዚህ መንፈስ ይህንን ጸሎት የምናደርግ ከሆነ ወየውልን! በተቃራኒው ለእኛ እና ለሕይወታችን መልካም የሆኑ ነገሮችን፣ ደህንነትን እና ሕይወትን በመስጠት እኛን ለመዳን በሚፈልገው በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ የሆነ እመንት በማስደር በዚህም መንፈስ ተሞልተን የምንጸልየው ጸሎት ሊሆን ይገባል። በብርታት መንፈስ ተሞልተን ልናደርገው የሚገባው ጸሎት ነው፣ እንዲያውም በተግዳሎ መንፈስ ምክንያቱም በአለም ውስጥ የእግዚአብሄር እቅድ መሰረት የማይጓዙ በጣም ብዙ ነገሮች እና ብዙ እውነታዎች አሉ። ሁላችንም እናውቃቸዋለን። ይህንን ሐሳብ በሚገባ ለመግለጽ ነቢዩ ኢሳያስ ጠቅለል አድርጎ ያስቀመጠውን በመግለጽ እንዲህ ማለት እንችላለን “አባት ሆይ እዚህ ጦርነት አለ፣ ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም እና ብዝበዛ አለ። ነገር ግን የአንተ እኛን መልካምነት እንደ ምትፈልግ እናውቃለን፣ ስለዚህ የእናንተ ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ እንማጸንሃለን! ሰይፋችንንም ወደ ማረሻ ጦሮቻችንንም ወደ ማጭድ እንዲቀየር አድርግልን፣ ማንም ሰው ሰይፉን በሌላው ላይ አያንሳ!” እግዚኣብሔር የሚፈልገው ሰላም ነውና።

“አባታችን ሆይ!" የሚለው ጸሎት ኢየሱስ ለአብ ያለውን ዓይነት ፈቃድ በእኛም ውስጥ የሚለኩስ ጸሎት ነው፣ ዓለምን በፍቅር እንድንለወጥ የሚያነሳሳን የእሳት ነበልባል ነው። ይህንን ጸሎት የምንጸልየው እግዚአብሔር ክፉን በመልካም በማሸነፍ እውነታን መለወጥ እንደሚችል እናምናለን ብለን በማሰባችን የተነሳ ነው። በጣም ከባድ በሆነው የፈተና ሰዓት እንኳን ሳይቀር ራሳችንን ለእርሱ ታዛዥ ለማድረግ እና የእርሱ ፈቃድ የፈጸም ዘንድ ራሳችንን ለእርሱ በአደራ በመስጠት የምንጸልየው ጸሎት ነው። በጌቴሴማኒ የአትክልት ሥፍራ ኢየሱስ መከራ ውስጥ በነበረበት ወቅት ያደርገውን ጸሎት በዚህ ሁኔታ የተከናወነ ጸሎት ነበር፡ “አባት ሆይ! ፈቃድህ ከሆነ ይህን ጽዋ ከእኔ ውሰድ! ይሁን እንጂ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” (ሉቃስ 22፡42) በማለት የአባቱን ፈቃድ ፈጽሙዋል። “እግዚአብሔር ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?  እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን? እግዚኣብሔር የሚወደን በዚሁ መልኩ ነው።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
20 March 2019, 14:32