ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከላቲን አሜርካ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከተወጣጡ ሰልጣኞች ጋር ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ከላቲን አሜርካ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከተወጣጡ ሰልጣኞች ጋር  

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በላቲን አሜርካ የካቶሊካዊያን የፖለቲካ ተሳትፎ አስፈላጊ እንደሆነ ገለጹ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሰልጣኞቹ እንደገለጹት የክርስቲያን ጥሪ እና በተለይም የፖለቲካ ጥሪ ከማሕበረሰቡ ዘንድ ይመነጫል ብለው የመጀመሪያ ምልክቱም በማሕበረሰቡ መካከል የሚታይ የእርስ በእርስ ወዳጅነት ነው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የላቲን አሜርካ ጳጳሳዊ ምክር ቤት የተወጣጡ ስልጠናን ሲከታተሉ የቆዩትን 26 ወጣቶችን ተቀብለው ያነጋገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን አሜርካ ካቶሊካዊ ምእመናን በፖለቲካ መሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።  

ፖለቲካ ማለት ስልጣንን መያዝ ብቻ እንዳልሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው ፖለቲካ ሁለገብ ማሕበራዊ እድገትን ያማከለ የአገልግሎት ጥሪ መሆኑን በላቲን አሜርካ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ አስመልክቶ ሲሰጥ የቆየውን ሴሚናር ተከታትለው የጨረሱትን ሰልጣኞችን ተቀብለው ባነጋገሩበት ጊዜ አስረድተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሰልጣኞቹ እንደገለጹት የክርስቲያን ጥሪ እና  በተለይም የፖለቲካ ጥሪ ከማሕበረሰቡ ዘንድ ይመነጫል ብለው የመጀመሪያ ምልክቱም በማሕበረሰቡ መካከል የሚታይ የእርስ በእርስ ወዳጅነት ነው ብለዋል።  ቅዱስነታቸው ገለጻቸውን በመቀጠል ይህ ፍቅር እና ወዳጅነትም የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋን በመልበስ ነው ብለዋል። ይህን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋን በመልበስ ለቤተክርስቲያን የገለጠውን የፍቅር እና የወዳጅነት መንገድ ወደ ሌሎችም ዘንድ በመውሰድ በተግባር መግለጽ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የፖለቲካ ቁርጠኝነት ቅድመ ሁኔታዎች፣

ካቶሊካዊ ምእመናን በፖለቲካው ዓለም መሳተፍ ማለት በፓርቲ ወይም በድርጅት መደራጀት ማለት ሳይሆን እውነተኛ ፍቅርን እና ወዳጅነትን በተግባር እየገልጹ በሕብረት መኖር በመሆኑ እንደ ቀዳሚ ቅድመ ሁኔታ መታየት ያስፈልጋል ብለዋል። 

በቤተክርስቲያን ማሕበራዊ አስተምህሮ ራስን የሚያሳድጉ ከሆነ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር በመታገዝ ከሌሎች የማሕበሩ አባላት ጋር የመሆን አስፈላጊነትን መገንዘብ የማይችሉ ከሆነ፣ ራስን ከሌሎች የክርስቲያን ማሕበረሰብ በመለየት የፖለቲካ መሪነት ከባድ ሸክም ለመወጣት ብቻ፣ የሥራ እቅዶችን በማውጣት እና ተግባራዊነታቸውን ለማረጋገጥ ጥረት በማድረግ ብቻ ወደ ከፍተኛ የፖለቲካ ስላጣን ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል። ይህ ደግሞ ወደ ብቸኝነት ሕይወት ውስጥ ይከትታል።

ሁለ ገብ ማሕበራዊ ጥቅምን የሚገኝበትን መንገድ ማሳደግ፣

የአንድ ክርስቲያን የፖለቲካ ሕይወት አቅጣጫ ሁለ ገብ ማሕበራዊ እድገት የሚገኝበትን መንገድ ማሳደግ እንደሆአን ያስረዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይህ ሊሆን የሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያሳየንን አዳዲስ የጊዜውን ሁኔታ ከመረዳት ነው ብለዋል። እንዲህ የሚለውን የቅዱስ ኦስካር ሮሜሮ ንግግር ጠቅሰዋል። “እውነተኛ ክርስቲያን እምነቱን በማስቀደም፣ ፍትህን ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት ከእግዚአብሔር መንግሥት የሚመጣ ፍትህ እንጂ ከሌላ ወገን እንዳልሆነ በግልጽ ማሳየት ይኖርበታል”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ቅዱስ ኦስካር ሮሜሮ ይህን ያለበትን ምክንያት ሲያስረዱ ክርስቲያን ምእመናን በፖለቲካው ዓለም ተሰማርተው ለሕዝባቸውን ነጻነትን ማምጣት የችሉት ከቅዱስ ወንጌል ከሚያገኙት መልካም ዜና እንጂ ከሌላ ርዕዮተ ዓለም አለመሆኑን አስረድተዋል።

የፖለቲካ ስልጣን ሌሎችን የማገልገል ጥሪ ነው፣

የፖለቲካ አስተሳሰብን ማወቅ የሚቻለው በቅዱስ ወንጌል ብርሃን በመታገዝ እንደሆነ ያስረዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሕዝቦች ወይም በፖለቲካው ዓለም የተሰማሩት ሰዎች የራሳቸውን ታሪክ በማስቀደም ግንባር ቀደም ተዋናይ ሊሆኑ የሚችሉት ስልጣን ሁሉን ነገር ለመወሰን የሚያስችል መሣሪያ አለመሆኑን ሲያውቁ ነው ብለዋል።

በላቲን አሜርካ የለውጥ ምዕራፍ፣

ላቲን አሜርካን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ሊያሸጋግሩ እና የእድገት ውጥኖችን ወደ ተግባር ሊለውጡ የሚችሉ ሦስት የተለመዱ እውነታዎች እንዳሉ የገለጹት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ፣ የላቲን አሜርካ ተስፋ የሆኑት ሴቶች፣ እውነተኛ ለውጥን በድፍረት ሊያመጡ የሚችሉ የወጣቱ ትውልድ እና በመጨረሻም ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ መሆኗን በታማኝነት ለመግለጽ የሚያስችላት ከድሆች እና ከማሕበረሰቡ ከተገለሉት ጋር በምታደርገው የቀረበ ግንኙነት እንደሆነ አስረድተዋል።   

ካቶሊካዊ ምእመናን በፖለቲካው ዓለም መሳተፍ አስፈላጊ ነው፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን በመቀጠል፣ ካቶሊካዊ ምእመናን በፖለቲካው ዓለም በስፋት እንዲሳተፉ ጠይቀው ይህም ቁጥርን ለማሳደግ ሳይሆን የሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ድምጽ የሚሰማበትን አዲስ መድረክ ለማግኘት እና ለነጻነት ለፍትህ እና ለእድገት የሚያደርጉት እውነተኛ ትግል በግልጽ እንዲታይ ለማድረግ ነው።

የተባበረ ጥረትን ይጠይቃል፣

ክርስቲያናዊ እምነት ልዩ ልዩ ጥረቶችን እንድናደርግ ይጋብዘናል በማለት አስምረው የተናገሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ እምነትን በነጻነት መኖር ያስፈልጋል ብለው ለካቶሊካዊ ምእመናን አንድ ብቻ ሳይሆን ልዩ ልዩ የፖለቲካ ጥረቶች እንዳሉ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም ሰልጣኞችን ባርከው ከማሰናበታቸው አስቀድመው፣ ላቲን አሜርካ ወይም ደቡብ አሜርካ ጻሬም፣ ነገም፣ ወደ ፊትም የልዩ ልዩ ሕዝቦች ውሕደት ያለባት አህጉር ሆና ትዘልቃለች፣ ይህም የእርሷ እጣ ፈንታ ነው ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
04 March 2019, 17:45