የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊጉሪ ከፍተኛ የነገር መለኮት ተቋም ተማሪዎች የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊጉሪ ከፍተኛ የነገር መለኮት ተቋም ተማሪዎች 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በሮም ከተማ ለሚገኝ ከፍተኛ የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊጉሪ የነገር መለኮት ተቋም ተማሪዎች ንግግር አደረጉ።

በሕዝቦች ላይ በሚፈጸሙ በርካታ ግፎች ምክንያት ድህነት እንዳልተወገደ፣ ሕዝቡን በመከፋፈል፣ አንዱን ከሌላው መለየት እና በራስ የመተማመን ስሜት እንዲጠፋ በማድረግ ወደ ከፋ ስቃይ ውስጥ እየተገባ መሆኑን አስረድተው ጥረታችንም ይህን ሁሉ ተመልክተን ስናበቃ ፍርድን ለመስጠት ሳይሆን ነገር ግን ሕዝብን ከደረሰበት ስቃይ ለመፈወስ እና ነጻ ለማውጣት ነው ብለዋል። ነጻ ማድረግ የምንችለውም ኢየሱስ ክርስቶስ የተጓዘበትን የምሕረት መንገድ በመጓዝ ነው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በሮም ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና ከተቋቋመ ዘንድሮ 70 ዓመትን ያስቆጠረውን የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊጉሪ ከፍተኛ የነገር መለኮት ተቋምን መጎብኘታቸው ታውቋል። ቅዱስነታቸው ይህን ከፍተኛ የስነ ምግባር ነገረ መለኮት አስተምህሮ ተቋምን በጎበኙበት ጊዜ ተቋሙን በበላይነት የሚመሩትን የረደንቶሪስት ገዳማዊያን ማህበር አባላትን፣ መምህራንና ተማሪዎችን አግኝተው ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። በ1941 ዓ. ም. የተቋቋመ የቅዱስ አልፎንሶ ማርያ ደ ሊጉሪ ከፍተኛ የነገረ መለኮት ተቋም ከ1952 ዓ. ም. ጀምሮ በሮም ከሚገኘው የላቴራን ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ የስነ መለኮት ፋካልቲ ሥር በመሆን ተማሪዎችን በስነ መለኮት ትምህርት እንደሚያስመርቅ ታውቋል። 

በ1941 ዓ. ም. ተቋቁሞ ከፍተኛ የስነ ምግባር ነገረ መለኮት አስተምህሮን በመስጠት ላይ የሚገኘው ይህ ተቋም፣ የስነ ምግባር ነገረ መለኮት አስተምሮ ባልደረባ የሆነውን የቅዱስ አልፎንሶ መርህ በመከተል ካህናትን፣ ደናግልን እና ምመናን በስነ ምግባር የነገረ መለኮት ትምህርት ለከፍተኛ ደረጃ እንደሚያዘጋጃቸው ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተቋሙ 70ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ተገኝተው ለተቋሙ አባላት በሙሉ ባደርጉት ንግግር እንደገለጹት በቆራጥነት እና በድፍረት ወደ ፊት በመጓዝ፣ የወንጌል ተልኮ አገልግሎትን ለእግዚአብሔር ሕዝብ ከደረስንበት የባሕል ለውጥ ጋር በማዛመድ በፍሬያማነት እንዲያበረክቱ አደራ ብለዋል።

ካቶሊካዊ ዩኒቨርስቲዎች እና መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት፣ መላዋ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ በማንኛውም ዘርፍ ውይይቶችን ለማድረግ የተነሳችበትን ቆራጥ ውሳኔን በመከተል፣ ከረጅም ዓመታት ወዲህ ከእግዚአብሔር ሕዝብ በኩል ለሚነሱት ጥያቄዎች በቂ ምላሾችን በመስጠት የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም ይህን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረ በቂ ቅድመ ዝግጅትን እንደሚያስፈልግ አሳስበው፣ ከማሕበረሰቡ እና በተለይም ከቤተሰብ አካላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ቅድሚያን በመስጠት ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ ቅዱስነታቸው አሳስበው በሕዝቦች ላይ በሚፈጸሙ በርካታ ግፎች ምክንያት ድህነት እንዳልተወገደ፣ ሕዝቡን በመከፋፈል፣ አንዱን ከሌላው መለየት እና በራስ የመተማመን ስሜት እንዲጠፋ በማድረግ ወደ ከፋ ስቃይ ስቃይ ውስጥ እየተገባ መሆኑን አስረድተዋል። ጥረታችንም ይህን ሁሉ ተመልክተን ስናበቃ ፍርድን ለመስጠት ሳይሆን ነገር ግን ሕዝብን ከደረሰበት ስቃይ ለመፈወስ እና ነጻ ለማድረግ ነው ብለዋል። ነጻ ማድረግ የምንችለውም ኢየሱስ ክርስቶስ የተጓዘበትን የምሕረት መንገድ በመጓዝ ነው ብለዋል።  የስነ ምግባር ነገረ መለኮታዊ አስተምህሮ ዓላማም ከቅዱስ ወንጌል የምናገኛቸው ከፍተኛ እሴቶች በእግዚአብሔር ቸርነት የተሰጡን ስጦታዎች እንደ ሆኑ በማስተማር የእግዚአብሔር ሕዝብ ብርታትን እንዲያገኝ ማገዝ ያስፈልጋል ብለዋል። በተጨማሪም የወንጌልን መልካም ዜና በማብሰር ሰዎችን ከሐጢአት ቀንበር ነጻ ማድረግ፣ ወደ ሞት ከሚወስድ መንገድ መመለስ ያስፈልጋል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ንግግራቸውን በመቀጠል ከቅዱስ ወንገጌል የሚገኝ ነጻነት ማንንም ሳይለይ፣ በተለይም እነዚያን እውነተኛ ነጻነት ለሚያስፈልጋቸው የሚዳረስ መሆን አለበት ብለዋል። የግለኝነትን መንፈስ በማስወገድ፣ የተባበረ ዓለምን መገንባት የሚቻልበትን  መንገድ ማዘጋጀት ግድ ነው ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የተባበረ ዓለምን በመገንባት የጥቂት ግለኛ ሰዎች ፍላጎቶችን ለማስቀረት እንደሚረዳ አስረድተው፣ እነዚህን የግል ፍላጎቶችን ለማስወገድ የሚያስችሉ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ማሕበራዊ ችግሮችን ለማቃለል ጥረት ማድረግ እደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት እንደገለጹት ማሕበርዋኢ ችግሮችን ለማስወገድ የሚያግዙ በርካታ ሕጎች እና መንገዶች ወደ ጎን እንደሚባሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያነሱት ሌላው ርዕስ ለምድራችን የሚደረገውን እንክብካቤን የተመለከተ ሲሆን ቅዱስነታቸው እንዳሳሰቡት የምንኖርባት ምድር በሰዎች ግድ የለሽነት ምክንያት በደረሰባት ችግር የተነሳ የምታሰማውን ጩሄት በማዳመጥ አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። የስነ ምግባር ነገረ መለኮታዊ አስተምህሮ፣ በእያንዳንዱ አገር በድምሪቱ ለሚደርሱ ችግሮች ፈጣን መፍትሄን ለማግኘት የሚያስችሉ መንገዶች በሕብረት ሆኖ በመፈለግ፣ ለሰው ልጅ ሁለገብ ማሕበራዊ እደገት በትጋት መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ስነ ጤናን በተመለከተ ተመሳሳይ የጋራ ጥረት መደረግ እንደሚያስፈልግ ያሳሰቡት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የስነ ምግባር ነገረ መለኮታዊ አስተምህሮ ለሰነ ሕይወት ትኩረትን በመስጠት በተለይም እርዳታን ለተነፈጉት እና አቅመ ደካማ ለሆኑት የማሕበረሰብ ክፍሎች አስቸኳይ ድጋፍ ለመጠት ተጠርተናል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመጨረሻም የስነ ምግባር ነገረ መለኮት አስተምህሮ በዓለማችን የሚታዩትን ችግሮች በሚገባ በማጤን፣ መንገድ፣ እውነትን እና ሕይወት የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መመስከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

                          

09 February 2019, 16:01