ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የኢየሱስ ስም ቅዱስ እና ኃያል በመሆኑ የተነሳ ክፉ መንፈስ ተሸንፏል!”

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!
ቀደም ሲል “አባታችን ሆይ!” በሚለው ጸሎት ዙሪያ ላይ የጀመርነውን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ በዚህ ጸሎት ውስጥ ከሚገኙ ሰባት የመማጸኛ ሐረጎች መካከል በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኘውን “ስምህ ይቀደስ” የሚለውን ሀረግ በጥልቀት እንመለከታለን።
"አባታችን ሆይ!" በሚለው ጸሎት ውስጥ የቀረቡት የመማጸኛ ጸሎቶች ሰባት ናቸው፣ እነዚህ የመማጸኛ ጸሎቶች በቀላሉ በሁለት ንዑስ ቡድኖች የተከፋፈሉ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ “አንተ/ያንተ” የሚለውን ቃል ማዕከል ባደርገ መልኩ የእግዚኣብሔር አባትን የሚያመልክቱ ናቸው፣ ቀሪዎቹ አራቱ ደግሞ “እኛ” የሚለውን ቃል ማዕከል ባደረገ መልኩ ሰብአዊ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን ያመለክታሉ። በመጀመሪያው ክፍል ላይ ኢየሱስ “ስምህ ይቀደስ፣ መንግሥትህ ይምጣ፣ ፈቃድህ በምድር ላይ ይሁን” በማለት እኛ አባቱ መንፈስ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፣ ለሁላችንም የአባቱን መንፈስ እንድንከተል ያመለክተናል፣ በሁለተኛው ክፍል ላይ ደግሞ “የእለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፣ ኃጢአታችንን ይቅር በልልን፣ ወደ ፈተና አታግባን እና ከክፉ ሁሉ አድነን” በማለት እኛ የእርሱ እርዳታ የሚያስፈልገን ሰዎች ውስጥ እግዚኣብሔር አባታችን እንዲገባ እርሱን መማጸን እንደ ሚገባን ያስተምረናል።
እዚህ ላይ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ጸሎት ምን መሆን እንዳለበት ይገልጻል-የእያንዳንዱ ሰው የጸሎት አገላለጽ ሊሆን የሚገባውን ነገር ያመለክታል- ይህም በአንድ በኩል እግዚአብሔርን በማሰላሰል፣ ስለ እርሱ ምስጢር በማሰብ፣ ስለ ውበቱ እና ስለ በጎነቱ በማሰብ ሁልጊዜም ቢሆን መደረግ ያለበት ጸሎት መሆኑን በመግለጽ እንዲደረግ የሚጠይቅ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ጥሩ ኑሮ ለመኖር የሚያስፈልጉንን ነገሮች በቅንነት እና በድፍረት የምንጠይቀበት ክፍል ይገኛል። ስለዚህ ቀለል ባለ እና መሰረታዊ በሆነ መልኩ "አባታችን ሆይ!" በማለት ቃላትን በመደርደር ከንቱ የሆነ ጸሎት እንዳናድርግ ያስተምረናል፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ራሱ እንደተናገረው "አባታችሁ ገና ሳትጠይቁት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ያውቃል" (ማቴ 6፡8) በማለት የተናገረውም በዚሁ ምክንያት ነው።
ከእግዚአብሔር ጋር ስንነጋገር በልባችን ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ገልጠን መናገር አንችልም፣ እኛ ራሳችንን ከምናውቀው እጅግ በላቀ መልኩ ያውቀናልና! እግዚአብሔር ለእኛ ምሥጢር ከሆነ፣ እኛ ደግሞ ከእርሱ ዓይን የተሰወርን ልንሆን በፍጹም አንችልም (መዝሙር 139፡1-4) ላይ እንደ ተጠቀሰው። ስለ ልጆቿ ሁሉንም ነገር ለመረዳት በጨረፍታ ብቻ ልጆቿን በመመልከት ልጆቻቸው ደስተኞች ወይም ሐዘንተኛ መሆናቸውን፣ ግልጽ ወይም የሆነ ነገር ደብቀው መያዝ አለመያዛቸውን በቀላሉ ለይተው እንደ ሚያውቁ እናቶች አምላክም እንዲሁ እኛን ያውቀናል።
በክርስቲያናዊ ጸሎት ውስጥ የመጀመሪያው እርምጃ ራሳችንን ለእግዚአብሔር እና ለእርሱ መለኮታዊ ጥበቃ ማስረከብ ወይም መስጠት ይሆናል ማለት ነው። ይህም ደግሞ ልክ እንደዚህ እንደ ማለት ነው "ጌታ ሆይ ሁሉንም ነገር ታውቃለህ፣ ሥቃዬን መናገር እንኳ አያስፈልገኝም፣ አንተ ከእኔ አጠገብ እንድትሆ ብቻ እጠይቅሃለሁ፣ አንተ የእኔ ተስፋ ነህ" እንደ ማለት ነው። ኢየሱስ በተራራ ሆኖ "አባታችን ሆይ" የሚለውን ጸሎት አስተምህሮ ከጨረሰ በኋላ ሰለነገሮች ከመጠን በላይ እንዳናስብ እና መጨነቅ እንደ ሌለብን አሳስቦናል። ይህ ደግሞ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ሐሳብ ይመስላል፣ በመጀመሪያ የእለት እንጀራን ይሰጠን ዘንድ እንድንጠይቅ ያስተምረናል ከዚያ ቀጥሎ ደግሞ “እንግዲህ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ” (ማቴ 6፡31) በማለት ይናገራል። በዚህ ረገድ ያለው ተቃርኖ በግልጽ የሚታይ ነው፣ የክርስቲያኖች ጥያቄዎች በአብ ላይ ያላቸውን መተማመን ይገልጻሉ፣ እናም ይህ መተማመን ነው የሚያስፈልጉንን ነገሮች በሙሉ ያለ ምንም ጭንቀትና መርበትበት እንድንጠይቅ የሚያደርገን ይህ በእርሱ ላይ ያለን መተማመን ነው።
"ስምህ ይቀደስ" ብለን የምንጸልየው በዚሁ ምክንያት ነው። የኢየሱስ አባቱ ያለውን ውበትና ታላቅነት በአድናቆት መንፈስ በመግለጽ፣ ሁሉም ሰው አባቱን እንዲያውቀው እና እርሱን በእውነት እንዲወዱት መፈለጉ በዚህ ውዳሴ ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ክፍል ነው። በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ስሙ በእኛ፣ በቤተሰባችን፣, በማኅበረሰባችን እና በመላው ዓለም ውስጥ የተቀደሰ ይሆን ዘንድ የሚማጸን የምልጃ ጸሎት ይገኛል። እኛን የሚቀድሰው፣ በፍቅሩ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናመጣ የሚያደርገን እርሱ ነው፣ ነገር ግን በተመሳሳይ መልኩ እኛ በበኩላችን የእግዚአብሔር ስም በዓለም ውስጥ ቅዱስ መሆኑን እና የእርሱ ስም ሕያው መሆኑን መመስከር ይገባናል።
የእግዚአብሄር ቅድስና የሕልውናችን ኃይል ነው፣ እኛ ይህንን የምንጠይቅበት ምክንያት ደግሞ በአለም ውስጥ የሚገጥሙንን መሰናክቶች በፍጥነት ስለሚያጠፋልን ነው። ኢየሱስ አስተምህሮውን የሚጀመረው የሰውን ልጅ የሚያሰቃየውን ክፉ ነገር በመቃወም ነው። “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፥ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደ ሆንህ አውቄአለሁ፥ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱሱ ነህ” (ማር1፡24) በዚህም የተነሳ እርኩሳን መናፍስት በስሙ የተረገሙ ናቸው። እነርሱ አንድ እንዲህ ቅዱስ የሆነ ሰው በፍጹም አይተው አያውቅም ነበር፣ ምክንያቱም ስለራሱ አልተጨነቀም ራሱን ለሌሎች ሰጠ። ከራሱ ውስጥ በመውጣት ለምሳሌም በአንድ ኩሬ ውስጥ እንደ ተወረወረ አንድ ድንጋይ ዓይነት በመሆን በዓለም ውስጥ ቅድሳናን አመጣ። ኃያል የሆነው እርሱ ከእኛ ጋር ስለሆነ ክፉ መንፈስ ተቆጥቶ ሊጎዳን አይችልም፣ ኃያል የሆነው የቤቱ ባለቤት ከእኛ ጋር ይኖራልና።
ጸሎት ሁሉንም ፍርሃቶች ያስወግዳል። አብ ይወደናል፣ ወልድ ደግሞ እጆቹን በዙሪያችን ላይ ይዘረጋል፣ ዓለምን ለመበዥት መንፈሱ በስውር ይሰራል። በስጋት ተውጠን አንቅበዝበዝ። አንድ እርግጠኛ የሆነ ነገር አለ፣ ክፉ ነገር ሁሌም ይፍራል!

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
27 February 2019, 14:28