ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሞት ፍርድ ሊቀር የሚገባው ዓይነት ቅጣት ነው”

የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና ግለሰቦች በየጊዜው ተደጋጋሚ በሆነ መልኩ ሳይቀር ማኅበርሰቡን አደጋ ላይ የሚጥሉ አስከፊ ወንጀሎችን እንደ ሚፈጽሙ ይታወቃል፣ በዚህም የተነሳ የግለሰቦች እና በአጠቃላይ የማኅበረሰቡ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎች እንደ ሚፈጸሙም ይታወቃል፣ ይሁን እንጂ ዛሬም ቢሆን በወንጀል ምክንያት እየደረሰ የሚገኘውን ጉዳት እና ወንጀልን ለማስወገድ የተለያዩ የማረሚያ ጣቢያዎች ተከፍተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፣ እነዚህ የማረሚያ ቤቶች በወንጀል ምክንያት በግለሰቦች እና በማኅበረሰቡ ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳቶች በመከላከል ማህበረሰቡን ለመጠበቅ ውጤታማ የሆኑ ተቋማት በመሆናቸው የተነሳ የሞት ፍርድን ተፈጻሚ ማደርጉ ተገቢ አይደለም ።

“በሌላ በኩል ደግሞ የሞት ፍርድ በወንጀል ድርጊት ውስጥ ተሳትፎ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ሰው በሰራው ጥፋት እና በመፈጸመው ከፍተኛ በደል የተነሳ በጥፋቱ እና በበደሉ አዝኖና ተጸጽቶ እንዳይመለስ አጋጣሚውን የሚዘጋ እንደ ሆነ፣ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ወቅት በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ አገራት ሕግ ውስጥ ተካቶ የሚገኘው የሞት ፍርድ የሰው ልጅ በፈጸመው በደል ተጸጽቶ የመመለሱን አጋጣሚ የሚዘጋ በመሆኑ የተነሳ ሊወገድ ይገባዋል”።

“ቤተ ክርስቲያን ሁልጊዜም ቢሆን ለሕይወት ጥበቃ ይደረግ ዘንድ በማሳሰብ የሞት ፍርድን በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ምትቃወም” የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህንን የቤተ ክርስቲያኗን አቋም በሚገባ ለማንጸባረቅ በማሰብ በቅርቡ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ የሞት ቅጣትን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የነበረው አስተምህሮ እንዲሻሻል መደረጉን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
በቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውስጥ ሳይቀር ለበርካታ አመታት ያህል ከፍተኝ እና አሰቃቂ የሆነ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት እንዲጣልባቸው የሚደነግግ ሕግ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ግለሰቦች እና ቡድኖች ከፍተኛ እና አሰቃቂ የሆኑ ውነጀሎችን የሚፈጽሙ ቢሆንም ነገር ግን እነርሱን ለመቅጣት ታስቦ የሚፈጸሙት የሞት ቅጣቶች ወይም ቅጣቶች መሰረታዊ ከሆኑ የሰው ልጆች የመኖር መብት ጋር የሚጣረዙ በመሆናቸው መቀየር እንደ ሚገባቸው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ የሞት ቅጣት እንዳይፈጸም ማደርግ በራሱ የሰው ልጆች መሰርታዊ የሆኑ ሕግጋትን ማክበር እንደ ሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው በዚህም መልኩ እኛ ሁላችን የሰው ልጆች መሰረታዊ መብታቸውን የማክበር ግዴታ እንዳለብን በመገንዘብ የሞት ቅጣት በሌላ አስተማሪ በሆኑ መነገዶች ይቀየር ዘንድ ሁላችንም የበኩላችንን ጥረት ማደርግ ይጠበቅብናል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

28 February 2019, 11:52