ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ስብሰባ ላይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ስብሰባ ላይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሰው ልጅን የሚጎዳውን የኑሮ ልዩነት ለማሸነፍ መዋደድ ያስፈልጋል አሉ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ 42ኛውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብሰባ በሮም በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ከየካቲት 7-8/2011 ዓ.ም አካሂዶ እንደ ነበር በተለይ ለቫቲካን ዜና ከደረሰን መረጃ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ የሁለት ቀን ስብሰባ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ገጠራማ አከባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች የምርት መጠንን እና ጥራትን ለማሳደግ እያደረጉት የሚገኘውን ከፍተኛ ጥረት በዚህ ረገድ “የድርጅቱ ተጨማሪ እገዛ ምን ሊሆን ይገባል?” በሚል ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ለቫቲካን ዜን የደረሰው መረጃ ያስረዳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ 42ኛው የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ይህ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተጨማሪ ምርት እንዲያመርቱ እያደረገላቸው ሰለሚገኘው ድጋፍ ድርጅቱን ማመስገናቸው እና ይህንን ተግባሩን አጠናክሮ በመቀጠል በአሁኑ ወቅት አሳፋሪ በሆነ መልኩ በሰው ልጆች እንዝላልነት የተነሳ በዓለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየታየ የሚገኘው የምግብ እጥረት ይቀረፍ ዘንድ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ማበረታታታቸው ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ 42ኛውን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ስብሰባ በየካቲት 08/2011 ዓ.ም በተጠናቀቀበት ወቅት በሥፋርው ተገኝተው የነበሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት እያከናወነው የሚገኘው ተግባር አንድ ዛፍ እንዲያድግ እና ሕይወት እንዲኖረው የሚያደርገው፣ ነገር ግን እኛ በዓይናችን የማናየው ሕይወት ሰጪ ከሆነው የዛፍ ሥር ጋር የዚህን ድርጅት ተግባር በማነጻጸር መናገራቸውን ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል።

ይህ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ላለፉት 40 ዓመታት ያህል በዓለም ዙሪያ ድህነት እንዲቀረፍ እና ብሎም ረሃብ ከዓለም ላይ እንዲወገድ እያደርገው የሚገኘውን ተግባር ቅዱስነታቸው እንደ ሚያድንቁ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህ ዓለማቀፍ ድረጅት 480 ሚልዮን ሕዝቦችን ተደራሽ ባደረገ መልኩ የድህነት መቅረፍ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉ ደግሞ ይህንን ዓለም አቀፍ ድርጅት የሚያስመሰግነው እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ከፍተኛ ሐብት በጣም በጥቂት ሰዎች እጅ ውስጥ እንደ ሚገኝ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህንን በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ በመታየት ላይ ያለውን አዝማሚያ በመቃወም የድህነት ቅነሳ ላይ ከፍተኛ ተሳፎ እያደርጉ የሚገኙ ግለሰቦችን እና ተቋማትን ጭምር ያመሰገኑ ሲሆን ይህም ደግሞ በጥቂት ሰዎች እጅ ውስጥ የተጠራቀመው ሐብት በፍጥነት እንዲቀንስ በማድረግ ለድሃው ሕዝብ ተደረሻ እንዲሆን ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ስለሚኖረው ይህ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ በጣሚ ጥቂት የሚባሉ ሰዎች የዓለማችንን ከፍተኛ ሐብት በእጃቸው ውስጥ አድርገው እንደ ሚገኙ፣ በሚያስገርም ሁኔታ ደግሞ የዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ በተቃራኒው በጣም ጥቂት የሚባል ሐብት ብቻ በእጃቸው እንደ ሚገኝ የገለጹት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ እየተንጸባረቀ የሚገኝ አሳዛኝ የሆነ አመክኒዮ ነው ብለዋል። በጣም ብዙ የሚባሉ የዓለማችን ሕዝቦች በቂ የሆነ ምግብ አያገኙም፣ በተቃራኒው ደግሞ በጣም ጥቂት የሚባሉ የዓለማችን ሕዝቦች ደግሞ ምግብ ተርፉዋቸው ሲጥሉ ይታያል ይህ ተመጣጣኝ ያልሆነ ከፍተኛ ልዩነት ያለው የኑሮ ሁኔታ ደግሞ በዓለማችን ውስጥ ያልተመጣጠነ እድገት እንዲከሰት በማድረግ የመጪው ዘመን የሰው ልጆች ኑሮን አስከፊ የሆነ ሁኔታ ውስጥ እንደ ሚከተው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።

16 February 2019, 10:07