ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አቡ ዳቢ አቀኑ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አቡ ዳቢ አቀኑ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አቡ ዳቢ አቀኑ

“ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ በሚካሄደው ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም ወደ እዚያው በማቅናት 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በተባበሩ የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ እያደረጉት የሚገኘው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት “የሰላም መሳርያ አድርገኝ” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እ.አ.አ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬ 8 ምዕተ አመታት በፊት ቅዱስ ፍራንቸስኮስ እና በወቅቱ የገብፅ ሱልጣን የነበሩት ማሊክ አል ካሚል ጋር በጣሊያን በተገናኙበት ወቅት የተጠቀሙበት መሪ ቃል በድጋሚ ለማስታወስ እና አሁንም ቢሆን ከ8 ምዕተ አመታት በኋላም ቢሆን እንኳን ዓለማችን በከፍተኛ ግጭቶች ውስጥ ስለምትገኝ በዚህ በግጭቶች እና በጦርነቶች እየተናጠች በምትገኘው ዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታት የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማሳሰብ የተመረጠ መሪ ቃል እንደ ሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አቡ ዳቢ አቀኑ
03 February 2019, 16:35