ፈልግ

“ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበልንበት ወቅት የገባነው ቃል ማስታወስ ያስፈልጋል” “ምስጢረ ጥምቀትን በተቀበልንበት ወቅት የገባነው ቃል ማስታወስ ያስፈልጋል” 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ምስጢረ ጥምቀት የተቀበልንበትን ቀን እና እለት ማስታወስ ይገባል” አሉ።

“ዛሬ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበትን የጥምቀት በዓል በምናከብርበት ወቅት እኛም ምስጢረ ጥምቀት በተቀበልንበት ወቅት የገባነውን ቃል ኪዳን በማስተውስ በተግባር ላይ ማዋል ይገባናል”

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዛሬው በምናከብረው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት ቀን የሚደመደም ሲሆን እኛም በዛሬው ቀን ስለ ጥምቀታችን እንድናስብ ይጋብዘናል። ኢየሱስ መጥምቁ ዩሐንስ የሰበከውን ጥምቀት እና በዮርዳኖስ ወንዝ ያደርገው ለነበረው ጥምቀት ራሱን ለማስገዛት ፈልጎ ተጠመቀ። ይህም ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ነበር፣ ወደ እዚያው የጥምቀት ቦታ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ ከኃጥአታቸው የመነንጻት ፍላጎቶቻቸውን እየገለጹ እና በእግዚኣቤርሔር እርዳታ አዲስ ሕይወት ለመጀመር በማሰብ ራሳቸውን ያስገዙ ነበር።
በዚህም አጋጣሚ ምንም ኃጢአያት የሌለበት፣ ነገር ግን ከኃጢኣን ጋር ለመጠመቅ አብሮዋቸው የተሰለፈውን፣ ከእነርሱ ጋር ተቀላቅሎ በዮርዳኖስ ወንዝ ለመጠመቅ የተሰለፈውን የኢየሱስን ታላቅ ትህትና እንመለከታለን። ኢየሱስ እጅግ ታላቅ የሆነ ትህትና ነበረው። ይህንንም ትህታና ባለፈው ባከበርነው የገና በዓል እለት አሳይቶት ነበር። የኢየሱስ ከሰዎች ጋር ለመጠመቅ መሰለፉ የስዎችን ድክመት እና ስሕተት ለመሽከም፣ ሰዎች የሚመኙትን ነጻነት ለማጎናጸፍ እና ከእግዚኣብሔር የሚያርቃቸውን ማንኛውንም ዓይነት ፈተናዎችን ለማሸነፍ የሚያደርጉትን ግብግብ ለማገዝ እና የባዶነት ስሜት የሚሰማቸውን ሁሉ ወደ እርሱ ለማቅረብ መጣ። ልክ እንደ ቤተልሔም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ እግዚአብሔር የሰውን ዘር ዕጣ ፈንታ እንደሚጠብቀው የገባውን ቃል ኪዳን ጠብቋል፣ ኢየሱስ ተጨባጭ እና ተገላጭ በሆነ ምልክት መጣ። ሁላችንንም ይንከባከበናል ሁላችንም በህይወታችን ይጠብቀናል። 

የዛሬው ወንጌል እንደሚያሳየው ኢየሱስ “ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አማሳል በእርሱ ላይ ሲወርድ ታየ” ይለናል (ማርቆስ 1፡10)። ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ ሲንቀሳቀስ የነበረው መንፈስ ቅዱስ፣ ሙሴንና ህዝቡን በበረሃ መምርት ጀምሮ የነበረው መንፈስ ቅዱስ፣ አሁን በዓለም ላይ ያለውን ተልዕኮውን ለመፈፀም ብርታት እንዲሰጠው በኢየሱስ ላይ ሙሉ በሙሉ ሲወርድ እናያለን። መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ ጥምቀትን የፈጠረ እና የጥምቀታችንም ፈጣሪ ነው። እውነትን እንድንመለከት ዓይኖቻችንን የሚከፍትልን መንፈስ ቅዱስ ነው፣ ህይወታችን ፍቅር መስጠት እንዳለባት እንዲሰማት የሚያደርገው መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ እግዚኣብሔር አባታችን በጥምቀታችን ቀን ለእያንዳዳችን የሰጠነ የጸጋ ስጦታ ነው። እግዚኣብሔር የሚደርግልንን ርኅራኄ ተቀብለን ለሌሎች ይህንን ርኅራኄ ማሳየት እንድንችል የሚያደርገው ይሄው መፈስ ቅዱስ ነው። አሁንም "አንተ የእኔ ልጅ ነህ" የሚለውን የፈጣሪን የአብ ቃል እንድነሰማ የሚያደርገን እና የሚገልጽልን መንፈስ ቅዱስ ነው።
የኢየሱስን የጥምቀት በዓል እያንዳንዱ ክርስቲያን የእራሱን ጥምቀት እንዲያስታውስ ይጋብዛል። አብዛኛዎቻችሁ በጥምቀታችሁ ወቅት በጣም ትናንንሽ ሕጻናት ልጆች ስለነበረችሁ የተጠመቃችሁበትን ቀን ታስታውሳላችሁ ወይ? ብዬ ጥያቄ ላቅርብላችሁ አልችልም፣ ምክንያቱ እኔም ብሆን፣ ሁላችንም በሕጻንነታችን ነው የተጠመቅነው። ነገር ግን እስቲ አንድ ጥያቄ ላቅርብላችሁ? የተጠመቃችሁበትን እለት ታስታውሳላችሁ ወይ? እስቲ እያንዳንዳችን ይህንን እናስብ። ቀኑን የማታስታውሱ ከሆናችሁ ግን ወይም ከረሳችሁት ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ እናታችሁን፣ አባታችሁን፣ አያታችሁን፣ አጎታችሁን አክስታችሁን፣ የክርስትና አባት እና የክርስትና እናታችሁን መቼ እና በምን ቀን ነው የተጠመኩት ብላችሁ ጠይቁ። ያንን የጥምቀታችንን ቀን በአዕምሮዋችን ውስጥ ሁል ጊዜም ልናስታውሰው ይገባናል፣ ምክንያቱም የበዓላችን ቀን ስለሆነ ነው፣ የቅድስናችን መጀመሪያ ስለሆነ ነው፣ ወደ ፊት እንድንራመድ የሚያነሳሳን መንፈስ ቅዱስን አብ ለእኛ የሰጠበት ቀን ስለሆነ ነው፣ ትልቅ ምሕረት ያገኘንበት ቀንም በመሆኑ ጭምር ነው፣ በእነዚ ምክንያቶች የተነሳ የተጠመቃችሁበትን ቀን እና እለት መርሳት በፍጹ አይኖርባችሁም።
ሁሉም ክርስቲያኖች በጥምቀታቸው ወቅት የተቀበሉትን ጸጋዎች ማስታወስ እንዲችሉ እና ይህንንም ከሕይወታቸው ጋር በተዛመደ መልኩ ይኖሩ ዘንድ፣ የእግዚኣብሔርን አብን፣ የልጁን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የመንፈስ ቅዱስን ፍቅር መመስከር እንችል ዘንድ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያም የእናትነት ጥበቃዋን መማጸን ያስፈልጋል።
ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ምዕመናን ዘንድ 2018 ዓ.ም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በተከበረበት ወቅት ካሰሙት ስብከት የተወሰደ።
 

18 January 2019, 16:45