34ኛው የወጣቶች ቀን ከፓናማ አጠቃላይ ሁኔታና ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጉብኝት ጋር በንጽጽር ሲታይ 34ኛው የወጣቶች ቀን ከፓናማ አጠቃላይ ሁኔታና ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጉብኝት ጋር በንጽጽር ሲታይ 

34ኛው የወጣቶች ቀን ከፓናማ አጠቃላይ ሁኔታና ከር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጉብኝት ጋር በንጽጽር ሲታይ

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ እንደሚከበር ቀደም ሲል በነበሩን የተለያዩ ዝግጅቶቻን መግለጻችን ይታወሳል። ፓናማ ይህንን 34ኛውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለማክበር ዝግጅቱን ከሁለት ዓመታት በፊት መጀመሯ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ከአምስት አህጉራት የተወጣጡ የተለያየ ዓይነት ባሕል እና ቋንቋ ያላቸው ወጣቶች ለአንድ ዓላማ በዚያው መገኘታቸው ይታወቃል። በዚህ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ተሳታፊ ከሆኑት ወጣቶች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት የካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑ ወጣቶች እንደ ሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም ባሻገር የአይሁድ እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወጣቶችም ተሳታፊ ሆነዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በዚህ በ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ተሳታፊ የሆኑት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነገው እለት ማለትም በጥር 16/2011 ዓ.ም በፓናማ የሚገኘውን የታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት ተገኝተው እንደ ሚጎበኙ ለቅዱስነታቸው ከወጣው መረዐ ግብር ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ይህም በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ በእስር ላይ የሚገኙ ወጣቶች በዚህ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ በአካል መገኘት ስለማያስችላቸው እንድሉ እንዲደርሳቸው ታቅዶ የተዘጋጀ ጉብኝት እንደ ሆነ ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ የታዳጊ ወጣቶች ማረምያ ቤት በሚያድርጉት ጉብኝት የምስጢረ ንስሐ አገልግሎት እንደ ሚሰጡ ተገልጹዋል።

ይህ በፓናማ ዋና ከተም የሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት 14-25  የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ 143 ታዳጊ ወጣቶች የሚገኙበት ማረሚያ በት ሲሆን እነዚህ ወጣቶች በፈጸሙዋቸው ከፍተኛ ወንጀሎች አማካይነት በትንሹ እስከ 12 ዓመት የእስር ቅጣት የተፈረደባቸው ወጣቶች ይገኙበታል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚሁ በፓናማ ዋና ከተማ በሚገኘው ማረሚያ ቤት በሚያደርጉት ጉብኝት ላይ 150 የሚሆኑ ታዳጊ ወጣት ታራሚዎች እንደ ሚገኙ ተገልጹዋል።

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የፍቅር መልእክት እንደ ሚያስተላልፉ ይጠበቃል

በታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት የሚገኙ ወጣቶች በዚህ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጉብኝት በሕይወታቸው ውስጥ የሚፈልጉትን ሰላም እና መረጋጋት እንደ ሚያስገኝላቸው ተስፋ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ የተገለጸ ሲሆን ይህም የዚህ ጉብኝት አዘጋጅ ለሆኑ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት የሚፈጥርባቸው እንደ ሆነ፣ ይህንን ወጣቶቹ የሚያልሙዋቸውን የሰላም እና የመረጋጋት መንፈስ በምልኣት ለማስገኘት ፈተና እንደ ሚሆንባቸው መግለጻቸው የታወቀ ሲሆን እነዚህም ተግዳሮቶች የመነጩት በዚህ በታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት ውስጥ ከሚገኙት ታራሚ ታዳጊ ወጣቶች መካከል አብዛኛዎቹ የካቶሊክ እመነት ተከታዮች ሳይሆኑ የተለያዩ የፕሮቴስታንት የእመት ተቋማት አማኞች በመሆናቸው የተነሳ እንደ ሆነ ተገልጹዋል። በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ የካቶሊክ እመነት ተከታይ ባለመሆናቸው ጭምር ስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቂ የሚባል ግንዛቤ ስለሌላቸው፣ በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ የሆነ ሚና ስለማይረዱት እንደ ሆነ ከስፍራው የደርሰን ዜና ያስረዳል።

ሁሉም ነገር በእግዚኣብሔር ኃይል ይቻላል

በዚህ በፓናማ ዋና ከተማ በሚገኘው የታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት ውስጥ ከ14-25 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታራሚ ወጣቶች ከፓናማ የተለያዩ አከባቢዎች የተውጣጡ እና ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመው እስከ 15 ዓመት የእስር ቅጣት የተበየነባቸው ታዳጊ ወጣቶች እንደ ሆኑ ከስፍራው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አብዛኛዎቹ በዚህ በታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች  የፓንማ ቀደምት የአገሬው ተወላጅ ዘር ተተኪ (Indigenous) የሆኑ ወጣቶች እንደ ሆኑ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል። በዚሁ አከባቢ በከፍተኛ ደረጃ እየተባባሰ የሚገኘው ወንጀል እየተከሰተ የሚገኘው አከባቢው በጣም ድሃ በመሆኑ የተነሳ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረጉ የተለያዩ ሕገ ወጥ ድርጊቶች የተነሳ መሆኑም ተገልጹዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ የታዳጊ ወጣቶች ማረሚያ ቤት መገኘታቸው ወጣቶቹ በእግዚኣብሔር ቃል ተጽናንተው፣ ከወንጀል በመራቅ መጪው ጊዜያቸው በብርሃን እና በተስፋ የተሞላ እንዲሆን እንደ ሚረዳቸው ይጠበቃል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
24 January 2019, 15:34