ፈልግ

የር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በፓናማ መገኘት በወጣቶች ላይ የተስፋ ስሜት አሳድሩዋል።

ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም እነሆኝ   የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን በፓናማ መከበር መጀመሩን መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን በዚህ በ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ከ167,000 በላይ ወጣቶች እይተሳተፉ እንደ ሚገኝ ይታወቃል።

ምንም እንኳን ይህ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በጥር 14/2011 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በፓናማ በተደርገ መስዋዕተ ቅዳሴ መጀመሩ የሚታወስ ሲሆን በዚያው የሚገኙ የበዓሉ ታዳሚ ወጣቶች የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን በእዚያው መገኘት በጉጉት እየተጠባበቁ ነበር፣ ይህ ጉጉታቸው እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለማየት ያላቸው ምኞት በትልናትናው እለት ማለትም በጥር 15/2011 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ፓናማ በደረሱበት ወቅት የወጣቱ ጉጉት እና ምኞት እውን መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በፓናማ ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም እነሆኝ   የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው 34ኛው ዓለማቀፍ የወጣቶች ቀን ተሳታፊ የሆኑ ከአምስት አህጉራት የተውጣጡ ከ167,000 በላይ ወጣቶች ይህንን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መንፈሳዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በተለያዩ ዝግጅቶች በማክበር ላይ እንደ ሚገኙ ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በፓናማ በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ለመሳተፍ ወደ እዚያው ያቀኑ እና የፓናማን መሬት የረገጡ ሁለተኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ከ36 ዓመታት በፊት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር በሚያዝያ 05/1983 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ዓለም በሶቪዬት ሕብረት ኮሚኒስት ርዕዮተ ዓለም ጫና ውስጥ በነበረበት ወቅት በዚያው ተገኝተው ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ለዚህ ለ34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከወጣው የጉዞ መርዐ ግብር ለመረዳት እንደ ተቻለው ዛሬ ማለትም ጥር 16/2011 ዓ.ም በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር 12፡40 ላይ  (በፓናማ እና በኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር መካከል የ8 ሰዓት ልዩነት አለ፣ ፓናማ ከኢትዮጲያ የሰዓት አቆጣጠር አንጻር ሲታይ  8 ሰዓታት ያህል ወደ ኋላ ትገኛለች) በፓናማ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት በመገኘት በዚያው የአገሪቷ ክቡር ፕሬዚደንት ሁዋን ካርሎስ፣ የተለያዩ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ የተለያዩ አገራት ልዑካን እና የሲቪል ማኅበርሰብ ተወካዮች በተገኙበት ንግግር እንደ ሚያደርጉ ይጠበቃል። ከእዚያም በመቀጠል አመሻሹ ላይ ከተለያዩ የመካከለኛው አሜሪካ ከተውጣጡ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ቤተ ክርስቲያኒቷን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በስፊው እንደ ሚወያዩ ይጠበቃል።

 ከጥር 14-19/2011 ዓ.ም “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ የተለያዩ መንፈሳዊ እሴቶችን የጠበቁ ዝግጅቶች በመካሄድ ላይ እንደ ሚገኙ ከስፍራው ከደረሰን ዜን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በፓናማ በሚገኙ የተለያዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቁምስናዎች ውስጥ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን ጨምሮ የምስጢረ ንስሐ አገልግሎት በሰፊው እየተሰጠ ይገኛል። በእዚህ 34ኛውን ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ላይ ተሳተፊ የሚሆኑ ወጣቶች ይህንን “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ “ በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ የሚገኘውን 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መሪ ቃል በጠበቀ መልኩ ማክበር ይችሉ ዘንድ የሚረዳቸው መንፈሳዊ ዝግጅት አንዱ አካል ሲሆን ይህም ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ፣ ሁሉም ሊግባቡበት የሚችል አንድ ቋንቋ የሚጠቀሙ ወጣቶችን በጋራ በማሰባሰብ በተለያዩ አርእስቶች ዙሪያ የትምህርተ ክርስቶስ አስተንትኖዎችን እና ትምህርቶችን በመስጠት፣ የእርቅ ምስጢር የሆነውን ምስጢረ ንስሐን ለወጣቶች ተደራሽ ማድረግ፣ ወጣቶች በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እና በተጨማሪም ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ ወጣቶች እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁ በማድረግ የመዝናኛ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ወጣቶችን ለዚህ ለታላቁ 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መደምደሚያ ቀን ማዘጋጀት እንደ ሆነ ከስፍራው የደረሰን ዜን ያመልክታል። 

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

Photogallery

የር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በፓናማ መገኘት በወጣቶች ላይ የተስፋ ስሜት አሳድሩዋል።
24 January 2019, 15:12