ከጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ በኋላ ከምዕመናን ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ ከጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ በኋላ ከምዕመናን ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ  

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የአዲሱ ዓመት የሥራ ዕቅድ ይፋ ሆነ።

ከጥር 15 እስከ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ. ም. በመካከለኛዋ የላቲን አሜርካ አገር በሆነችው በፓናማ በሚከበረው 34ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል ላይ ቅዱስነታቸው እንደሚገኙ ለበዓሉ የወጣውን መርሃ ግብር ከቫቲካን የተገኘ ዜና አስታውሷል። ይህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል ባለፈው ጥቅምት ወር 2011 ዓ. ም. ከተካሄደው 15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ማግስት በመሆኑ፣ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያሳስብ ምልዕክት የሚተላለፍበት እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በአዲሱ የአውሮጳዊያኑ 2019 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሚያከናውኗቸው የሥራ ዕቅዶች ይፋ መሆናቸውን ከቫቲካን ከተማ የተገኘ ዜና አመልክቷል። በዚህም መሠረት ቅዱስነታቸው በዓመቱ መጀመሪያ በሆነው በጥር ወር አዲስ የተሾሙትን የተለያዩ አገሮች አምባሳደሮችን እንደሚቀበሉና በእነዚህ አምባሳደሮች በኩል ለዓለሙ ማሕበረሰብ መልዕክታቸውን እንደሚያስተላልፉ ታውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ መብት ድንጋጌን ያጸደቀበትን 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል ለማክበር በሚዘጋጅበት ባሁኑ ወቅት፣ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለይም በሕይወት ላይ እየደረሱ መሆኑን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው ዓመት መናገራቸውን ዜናው ገልጿል።

ከጥር 15 እስከ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ. ም. በመካከለኛዋ የላቲን አሜርካ አገር በሆነችው በፓናማ በሚከበረው 34ኛ ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል ላይ ቅዱስነታቸው እንደሚገኙ ለበዓሉ የወጣውን መርሃ ግብር ከቫቲካን የተገኘ ዜና አስታውሷል። ይህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል ባለፈው ጥቅምት ወር 2011 ዓ. ም. ከተካሄደው 15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ማግስት በመሆኑ፣ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ቀዳሚ ተዋናይ እንዲሆኑ የሚያሳስብ ምልዕክት የሚተላለፍበት እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። ባለፈው ህዳር ወር 2011 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለመላው የዓለም ወጣቶች በሙሉ ባስተላለፉት የቪዲዮ ምስል መልዕክታቸው፣ ወጣቶች ከራሳቸው አልፈው ወደ ሌሎች ዘንድ በመሄድ አገልግሎት እንዲያበረክቱ ማሳሰባቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በዚህ መልዕክታቸው ሕይወታችን ትርጉም ሊኖረው የሚችለው እግዚአብሔርንና የተቸገረን በማገልገል ብቻ እንደሆነና ይህንን ለማከናወን ብዙ ወጣቶች ምኞት እንዳደረባቸው መግለጻቸውን ከቫቲካን የተላከልን ዘገባ አስታውሷል። በማከልም የወጣቶች ሃይል እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው በሙሉ በሚያቀርቡት  አገልግሎት በኩል ዓለምን መለወጥ፣ የዓለማችንን ሃያላን ማሸነፍ እንደሚችል መናገራቸውንም አስታውሷል። 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተባበሩት አረብ ኤምረቶችን የሚጎበኙት በያዝነው የአውሮጳዊያኑ አዲስ ዓመት 2019 ዓ. ም.  ከጥር 26 እስከ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ. ም. እንደሆነ ከቫቲካን ከተማ ይፋ የተደረገ ዘገባ ያሳወቀ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ የተባበሩት አረብ ኤምረቶችን ሲጎበኙ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የመጀመሪያ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት እንደሚሆኑ ታውቋል። ቅዱስነታቸው በአረብ ኤምረቶች በሚያደርጉት ቆይታ “የሰው ልጆች ወንድማማችነት” በሚል ርዕስ፣ በአቡ ዳቢ ከተማ የሚካሄደውን የዓለም ሐይማኖቶች መሪዎች ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ክፍል ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ከእግዚአብሔር የሚገኝ እውነተኛ ሰላም በሰው ልጆች መካከል የሚታየውን ጥላቻ እንደሚያስወግድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ባወጀው መልካም ዜና አማካይነት መላው ዓለም በአንድ እግዚአብሔር ስም እርቅንና ሰላምን እንዲያገኝ መደረጉ ይታመናል። በተባበሩት አረብ ኤምረቶች፣ አቡ ዳቢ ከተማ የሚካሄደው የዓለም ሐይማኖቶች መሪዎች ጉባኤ የመወያያ ርዕስም፣ ቅዱስ ፍራንችስኮስ ለሰላም ካቀረበው ጸሎት የመነጨ በመሆኑ፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ተባበሩት አረብ ኤምረቶች የሚያደርጉት ጉብኝት ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ሰላም ለማጠናከር እገዛ እንዳለው፣ በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ አማካይነት በጎ ፈቃድ ባላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ የእግዚአብሔር ሰላም እንደሚመጣ ተስፋ ተጥሎበታል።

ከየካቲት 11 እስከ የካቲት 13 ቀን 2011 ዓ. ም. ድረስ በቫቲካን ውስጥ የሚካሄደው የካርዲናሎች ምክር ቤት ጉባኤ የሚከናወነው በታሕሳስ 23 በገባው የአውሮጳዊያኑ አዲስ ዓመት እንደሆነና ይህን ጉባኤ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በበላይነት እንደሚመሩት ታውቋል። ባለፈው ታህሳስ ወር 2011 ዓ. ም. ላይ ወንጌልን አብስሩ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሐዋርያዊ መመሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት መቅረቡ ይታወሳል። የዚህ ሐዋርያዊ ደንብ ዋና ዓላማ ቤተክርስቲያን ለዓለም በሙሉ በምታበረክተው የውንጌል ተልዕኮ ውስጥ የቤተክርስቲያን የበላይ አባቶች ትልቅ ሃላፊነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል።

በዚህ የአውሮጳዊያኑ አዲስ ዓመት 2019 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሰሜን አፍሪቃ አገር ወደ ሆነችውን ወደ ሞሮኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚያደርጉበት ዓመት እንደሆነ ከዚህ በፊት ይፋ መሆኑ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው ወደዚህች አገር የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት መጋቢት 21 እና 22 2011 ዓ. ም. እንደሚሆን ከቫቲካን የደረሰን ዘገባ ያመለከታል። ከ33 ዓመት በፊት ማለትም በመጋቢት 10 ቀን 1977 ዓ. ም. ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ወደ ሞሮኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቀዳሚ ተልዕኮ፣ የዚያች አገር ምዕመናን በእምነታችን እንዲጠነክሩ፣ ከዚህም በተጨማሪ ቅዱስነታቸው በሞሮኮ የምትገኝ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን በሚገባ ለማወቅ፣ ሕይወቷንም ለመጋራት፣ ሊያበረታቷት፣ ከምዕመናኑ ጋር አብረው ለመጸለይ እንደሆነ ታውቋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከሞሮኮ ሕዝብና ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት ምኞት እንዳላቸው ከዚህ በፊት የተገለጸ ሲሆን በተለይም ከሞሮኮ ንጉሥ፣ ግርማዊነታቸው መሐመድ 6ኛ ጋር በመገናኘት በሁለቱ እምነቶች መካከል ማለትም በክርስትናና በሙስሊም እምነት መካከል የሚታየውን የውይይት ፍላጎት የበለጠ ለማሳደግ፣ በተግባርም ለመግልጽ ነው ተብሏል። በሞሮኮ በሚገኙ ክርስቲያኖችም መካከል ያለው ሕብረት እንዲያድግ ትልቅ ፍላጎት በመኖሩና ከሮማው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የጠበቀ ግንኙነትን በመፍጠር ወደ መላዋ ቤተክርስቲያን አንድነት ለመድረስ የሚያስችል መንገድ ለማበጀት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደ ሞሮኮ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን ታምኖበታል።

02 January 2019, 15:55