ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ የሞት ፍርድን ከሚቃወመው ዓለማቀፍ ኮሚሽን አባላት ጋር በቫቲካን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ የሞት ፍርድን ከሚቃወመው ዓለማቀፍ ኮሚሽን አባላት ጋር በቫቲካን 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የሞት ቅጣት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

“እያንዳንዱ ህይወት የተቀደሰ በመሆኑ የተነሳ ያለምንም ገደብ ለሕይወት ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሳስ 08/2011 ዓ.ም በዓለማቀፍ ደረጃ የሞት ፍርድን ከሚቃወመው ዓለማቀፍ ኮሚሽን አባላት ጋር በቫቲካን መገናኘታቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በግንኙነቱ ወቅት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “የሞት ቅጣት ኢሰባዊ የሆነ ተግባር” መሆኑን መግለጻቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ ረገድ የሞት ፍርድን የሚቃወመው ዓለም አቀፉ ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት እያደርገው የሚገኘውን እና የሞት ፍርድን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስቀረት እየደረጉ የሚገኙት ከፍተኛ ጥረት ቅዱስነታቸው ያላቸውን አድናቆት በመግለጽ ምስጋና ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
“እያንዳንዱ ህይወት የተቀደሰ በመሆኑ የተነሳ ያለምንም ገደብ ለሕይወት ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል” በማለት በአጽኖት በመግለጽ ንግግራቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ውስጥ እንደ ተገለጸው የሞት ቅጣት ሰብአዊ ክብርን የሚጎዳ ቅጣት መሆኑን እንደ ሚገልጽ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “የሞት ቅጣት የቅዱስ ወንጌልን እሴቶች የሚቃረን ቅጣት ነው፣ ምክንያቱም በፈጣሪ ዓይን ሁሌም ቅዱስ የሆነውን ህይወት ማጥፋት በመሆኑ የተነሳ እንደ ሆነ” ገልጸው እውነተኛ ፈራጅ እና ለሕይወታችን ዋስትና የሚሰጠው እግዚኣብሔር ብቻ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል።
ለባለፉት በርካታ አመታት የነበሩት ሕጎች የሞት ቅጣትን አመክንዮኣዊ እና ትክክለኛ የሆነ ውጤት እንደ ምያስገኝ አድርገው ማቅረባቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው አለመታደል ሆኖ ቀደም ሲል የነበሩ በቤተ ክርስቲያን ይመሩ በነበሩ ተቋማት ውስጥ ሳይቀር ከሕጎች ሁሉ በላይ የሆነውን የእግዚኣብሔር ምሕረት ችላ በማለት ይህ ኢሰባዊ የሆነ የሞት ፍርድ ሲፈጸም እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት በአዲስ መልክ የተከለሰው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀደም ሲል በነበረው አስተምህሮ ምክንያት ለተፈጸሙት የሞት ፍርድ ቅጣቶች ኃላፊነት በመውሰድ እና የዚህ ዓይነቱ የሞት ፍርድ ቅጣት ሲፈጸም የነበረው በወቅቱ በነበረው የአስተሳሰብ ደረጃ ትክክለኛ ነው ተብሎ በመታሰቡ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህ አመለካከት ክርስቲያናዊ ከሆነ አስተሳሰብ ይልቅ ለሕግ ልዕልና የቆመ እና ሕግን ቅድስና ከምያላብሰው ሕጋዊ ከሆነ አስተሳሰብ የመነጨ እንጂ ከሰብዓዊነት እና ከምሕረት መንፈስ የመነጨ ባለመሆኑ የተነሳ እንዲወገድ መደረጉን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
“ምንም እንኳን ውስብስብ የሆኑ ፖለቲካዊ ሂደቶች ቢኖሩም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሁሉም ሀገራት በጭካኔ የተሞላውን የሞት ፍርድ ቅጣትን ከሕጋቸው ውስጥ እንደ ሚሰረዙ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩም ከፍርድ ሂደት ውጪ የሚፈጸሙትን በዘፈቀደ የሚደረጉ ግድያዎችን ይቆሙ ዘንድ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ጥሪ ለማቅረብ እፈልጋለሁ ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት ማንኛው ፍርድ በጥንቃቄ በተጠና መልኩ መከናወን እንደ ሚገባው ጠቅሰው በተጨማሪም በሲቪል እና በፖለቲካ ሂደቶች ውስጥ ያሉ የፍቅር ዓይነቶች የተሻለ ዓለም ለመገንባት በማሰብ በሚፈጸሙት ድርጊቶች ሁሉ ውስጥ ይገለጣሉ ማለታቸውን ከደረሰን ዜና ለመረዳት ተችሉዋል። ማነኛውንም ዓይነት ወንጀሎች ለመከላከል ያስችል ዘንድ ለኅብረተሰብ ያለንን ፍቅር እና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስከበር በትጋት መሥራት እና ቁርጠኛ በመሆን የሞት ፍርድ የምያስከትሉትን ወንጀሎች ለመከላከል የምያስችሉ ጥሩ ልምዶች መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው በግለሰቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ማሕበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንኙነቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጠናከሩ በማድረግ መልካም የሚባል ማኅበርሰብ በመመስረት አላስፈላጊ የሆኑ ቅጣቶችን ማስወገድ እንደ ሚችላ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 25/2010 ዓ.ም የካቶሊክ ቤተክርስትያን አንቀጸ እመንት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ በሆኑት በክቡር ካርዲናል ሉዊዝ ፍራንቸስኮስ ላዳሪያ የተፈረመ እና የሞት ቅጣትን በጽኑ የሚያወግዝ አስተምህሮ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ ውስጥ እንዲካተት ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ያቀረቡት ሰነድ በቅዱስነታቸው ተቀባይነትን አግኝቶ መጽደቁን መዘገባችን ይታወሳል።

እስከ ሐምሌ 25/2010 ዓ.ም ድረሰ በአገልግሎት ላይ በነበረው የካቶሊክ ቤተክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በቁጥር 2267 ላይ ብቻ የሚገኘውን “የሞት ቅጣት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት የፍትሕ ባለስልጣናት ተከሳሹ ፍትሃዊ የፍርድ ሂደትን ካለፈ በኋላ፣ ተከሳሹ የፈጸመው ከባድ ወንጀል መሆኑ ከተረጋገጠ እና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው፣ በጣም ከባድ እና የከፋ ወንጀል መሆኑ ከተረጋገጠ የማኅበርሰቡን ማኅበራዊ ደኅንነት ለማስጠበቅ በማሰብ ተፈጻሚ ይሆናል” በሚለው ቀደም ሲል የነበረው የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በሚከተለው አዲሱ አስተምህሮ ተተክቱዋል። በዚህ መሰረት ከሐምሌ 25/2010 ዓ.ም ጀምሮ በካቶሊክ ቤተክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ውስጥ በቁጥር 2267 ላይ የነበረው አስተምህሮ በሚከተለው አስተምህሮ ተተክቱዋል።
ይሁን እንጂ ዛሬ አንድ ሰው በጣም ከባድ የሆኑ ወንጀሎች ከፈፀመ በኋላም እንኳን ቢሆን ሰብዓዊ የሆነ ክብሩ እንዳለ እንደ ሚቀጥል ለመገንዘብ ተችሉዋል። በተጨማሪም ሀገራት ባስቀመጡዋቸው ከፍተኛ ቅጣቶች ትርጉም ላይ አዲስ ግንዛቤ ተገኝቷል። በመጨረሻም የዜጎች ደኅንነት መጠበቁን የሚያረጋግጥ የበለጠ ውጤታማ የእስር ማቆያ ስርዓት የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ነገር ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ታራሚው ወይም በዳዩ የጎድለውን ሰነ-ምግባር በፍጹም መልሶ መጎንጸፍ አይችልም የሚለውን ሐሳብ ግን የማረጋገጥ እድል የለውም”። በዚህም ምክንያት ቤተክርስትያን በወንጌል ብርሃን በመመራት "የሞት ቅጣት በፍጹም ተቀባይነት የለውም ምክንያቱም የሞት ቅጣት የሰውን ልጅ ተጋላጭ የሚያደርግ እና በሰው ልጅ ክብር ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው በማለት ታስተምራለች፣ ይህ ቅጣት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፋጻሚ እንዳይሆን በጽናት ትሠራለች”።

ይህንን ለውጥ እና ማሻሻያ በተመለከተ አስተያየታቸውን ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ ለተሰኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚኬላ እንደ ገለጹት “የሞት ቅጣት የሰው ልጅን ሰብዓዊ መብት ይቃረናል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።
አዲስ የስብከተ ወንጌል ዜዴዎችን የሚያስተዋውቀው ጳጳሳዊ ምክርበት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “በቅርቡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በካቶሊክ ቤተክርስትያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ውስጥ የሞት ፍርድን በተመለከተ ያደርጉት አዲሱ ማሻሻያ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስትያን ቀጣይነት ባለው መልኩ አስተምህሮዎቹዋን እያሻሻለች እንደ ምትሄድ ያሳየ ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑን” ጨምረው ገለጸዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ ቀደም ሲል የሞት ቅጣትን በተመለከተ የነበረውን አስተምህሮ በሐምሌ 25/2010 ዓ.ም የሞት ቅጣትን በሚያወግዝ አዲስ አስተምህር እንዲተካ በደረጉበት ወቅት እንደ ገለጹት “የሞት ፍራድ ሊገረሰስ የማይችለውን የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብር የሚቃረን በመሆኑ ቤተክርስትያን የሞት ፍራድን በጽናት ትቃወማለች!” ማለታቸውን ይታወሳል።
የእምነትን ይዘት የበለጠ ግልጽ እንዲሆን ያደርጋል
ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ ይህንን በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አማካይነት የተድረገውን ማሻሻያ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ጨምረው እንደ ገለጹት “እውነቱን ለመገር የአንቀጸ እመንት ማሻሻያዎች የእምነትን ይዘት የበለጠ ግልጽ እንዲሆን የሚያደርጉ ሂደቶች ናቸው” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ እምነትን በተመለከተ “አንድ ሰው የሞት ፍርድ በዘመናችን መፈጸም እንደ ሌለበት እንዲገነዘብ ያደርገ መልካም አጋጣሚ ነው” ብለዋል።
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ ሦስት ዋና ዋና እንድምታዎች እንዳሉት የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “ከሁሉም በላይ አስፈላጊው እና ጠቃሚ ጉዳይ ለሁሉም የሰው ልጆች ሰብዓዊ ክብር እውቅና መሰጠቱ፣ የሰው ልጅ ነብስ ምንም እንኳን በጣም ከባድ የሚባል ወንጄል ቢሰራም እንኳን የሰው ልጅ ነብስ በፍጹም መጥፋት እንደ ሌለበት በግልጽ ያስቀመጠ ለውጥ” መሆኑን ገለጸዋል።
በተጨማሪም የክርስትያን ማኅበረሰብ የሰው ልጆችን ነብስ በተመለከተ ያላውን ግንዛቤ "አዎንታዊ" በሆነ መልኩ ለውጥ እንዲያደርጉ ያስቻለ አጋጣሚ መሆኑን የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፍዚቄላ አሁን ያለው የወንጀለኛ አያያዝ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑ ስርዓቶችን እየተከተለ የሚገኝ በመሆኑ ይህም "በበደለኛ ሰዎች ላይ ይደረግ የነበረውን አሰቃቂ አደጋ እና ሰቆቃ በማስቀረት በወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ስነ-ምግባራዊ የሆነ ለውጥ እንዲያመጡ እና ከጥፋታቸው ተመልሰው መልካም ሰዎች በመሆን ማኅበርሰቡን ተመልሰው እንዲቀላቀሉ እድል የሚሰጣቸው አጋጣሚ ነው” ብለዋል።
እምነት ማለት ለእያንዳንዱ ትውልድ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ መፍቀድ ማለት ነው
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስትያን አስተምህሮዎቹዋን የምታሻሽለበት መንገድ አንዱ አካል መሆኑን የጠቀሱ ሊቀ ጳጳስት ሪኖ ፍዚቄላ “የተቀደሰውን የእምነት አስተምህሮ ጠብቆ መሄድ ማለት እምነትን እንደ አንድ ጥናትዊ የሆነ አጽም አድርገን ጠብቀን መያዝ ማለት ግን አይደለም” ካሉ በኋላ “ነገር ግን በተቃራኒው እመነት ከእራሱ ባህሪ ጋር ያለውን ተፈጥሮኣዊ ውህደት ወይም ትስስር የበለጠ ለመጥራት እና እውነተኛ እምነት ማለት ለእያንዳንዱ ትውልድ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ መፍቀድ ማለት ነው” ብለዋል።
ይህ አሁን በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የተደርገው ለውጥ “ቅዱስ ወንጌልን በይበልጥ በመረዳት” የተደረገ በጣም ወሳኝ የነበረ ለውጥ እንደ ሆነ የገለጹት ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚቄላ “በዚህ ረገድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በተመለከተ “ለረዥም ጊዜ የቆየውን የቤተክርስትያኗን አንቀጸ እመንት ትርጓሜ ለመቀየር በጣም ወሳኝ እርምጃ መወሰዳቸውን” አድንቀዋል።
የሞት ፍርድን ለመበየን የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት የሚያበቁትን “በጣም አደገኛ እና ኢሰባዊ የሆኑ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ቤተ ክርስትያን የተደበላለቀ ስሜት እንደሚፈጠር ትገነዘባለች” ካሉ በኋላ ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ብለዋል. . .

የሞት ቅጣትን ለማስወገድ መጣር ማለት የተጎጂዎችን ስቃይ እና የፈጸሙባቸውን ኢፍትሀዊ የሆኑ ወንጀሎችን መርሳት ማለት ግን አይደለም። ይልቁንም የፍትህ ስርዓቱ የራሱን ወሳኝ እርምጃ እንዲወስድ ይረዳል፣ በቁጣትና በበቀል ሳይሆን ነገር ግን አሁን ካለው ጊዜያዊ ችግር ባሻገር በመሄድ ኋላፊነት መውሰድ ያስፈልጋል”።

ሊቀ ጳጳሳ ሪኖ ፍዚቄላ በቅርቡ በካቶሊክ ቤተክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2267 ላይ የሞት ፍርድን በተመለከተ የተደረገውን ለውጥ በተመለከተ ኦዜርቫቶሬ ሮማኖ ከተባለ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እለታዊ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት መደምደሚያ ላይ እንደ ተናገሩት "ሰብዓዊ ሕይወትን በፍቃደኝነት መጨቆን" ከክርስቲያን ገልጸት ጋር የሚቃረን ተገባር ነው” ማለታቸውንም መዘገባችን ይታወሳል።

18 December 2018, 15:57