ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የገናን በዓል ዓለማዊ በሆነ መንገድ ማክበር አይገባንም

“የገናን በዓል ዓለማዊ በሆነ መንገድ ማክበሩን ትተን የኢየሱስን አስገራሚ የሆኑ ስጦታዎች በደስታ ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርብናል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ እና እንደ አየሩ ሁኔታ በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሻ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት በታኅሳስ 10/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የጳውሎስ 6ኛ የስብሰባ አዳራሽ ያደርጉት የጠቅላላ የተምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስትያኖች ዘንድ ከስድስት ቀናት በኋላ በሚከበረው እና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ በሚዘክረው በገና በዓለ ዙርያ ላይ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “የገናን በዓል ዓለማዊ በሆነ መንገድ ማክበሩን ትተን የኢየሱስን አስገራሚ የሆኑ ስጦታዎች በደስታ ለመቀበል መዘጋጀት ይኖርብናል” ማለታቸው ተገልጹዋል። “እግዚአብሔር ለማርያምና ለዮሴፍ ያልተጠበቀ አዲስ ነገር በሕይወታቸው ውስጥ እንዳደረገ ሁሉ፣ ሁሉም ሰው የገናን በዓል በተሳሳተ መልኩ ዓለማዊ በሆነ ሁኔታ በማክበር ስጦዎችን በመለዋወጥ፣ አብሮ በመብላት እና በመጠጣት ብቻ ማክበር እንደ ማይገባው” ገልጸው ብያንስ ብያንስ እንኳን የእግዚኣብሔር መገለጫ የሆኑትን፣ በገና በዓለ ለእኛ ሲል ድሃ ሆኖ በከብቶች ማደሪያ በግርግም ውስጥ የተወልደው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምሳያ የሆኑትን ድሆች በመርዳት ማክበር ይገባል ብለዋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

በእለቱ የተነበበው ምንባብ

“ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ፥ እርሱ ብርሃን አልነበረም። ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር። በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም። የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው” (ዮሐ. 1፡9-12)።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 10/2011 ዓ.ም የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ ክርስትያኖች ዘንድ ከስድስት ቀናት በኋላ የሚከበረውን እና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ በሚዘክረው በገና በዓለ ዙርያ ያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል ተከታተሉን!

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!
ከስድስት ቀናት በኋላ የገናን በዓል እናከብራለን። በየቦታው የተሠሩት የገና ዛፎች፣ የተሰቀሉ ጌጣጌጦች እና ከተሰቀሉት መብራቶች ውስጥ የሚወጡ ብርሃኖችን ስንመለከት አንድ ትልቅ በዓል እየመጣ እንደ ሆነ ያስታውሰናል። የተለያየ ዓይነት ማስታወቂያዎች የሚለጠፉባቸው አውታሮች ሁልጊዜ ድንቅ የሆኑ አዳዲስ ስጦታዎችን በማስተዋወቅ እነዚህን ስጦታዎች ገዝተን እንድንለዋወጥ ይጋብዙናል። እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፣ የዚህ ዓይነቱ የበዓል አከባበር እግዚአብሔርን የሚያስደስት በዓል ነው ወይ? እርሱ የሚፈልገው የገና በዓል ምን ዓይነት ነው? ምን ዓይነት ስጦታዎችን እንድንለዋወጥ ነው የሚፈልገው? ምን ዓይነት ድንገተኛ የሆኑ ስጦታዎችን እንድሰጥ ነው የሚፈልገው?
የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ምርጫ ለማወቅ የመጀመሪያውን የገና በዓል ለአብነት እንመልከት። ያ ቀድሞ የነበረው የገና በዓል በአስገራሚ ነገሮች የተሞላ ነበር። የዮሴፍ እጮኛ ከነበረችው ከማርያም ይጀምራል፣ መልኣኩ ወደ እርሷ መጥቶ ሕይወቷን ይቀይራል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት እንደ ምትሆን ይነግራታል። ቀጥሎም ወደ ዮሴፍ በመሄድ ገና ልጅ ሳይወልድ የልጅ አባት ተብሎ እንደ ሚጠራ ይነግረዋል። ይህ የሚወለደው ልጅ የትዕይንቱ አንድ አካል በመሆን ቢያንስ ቢያንስ በተገቢው ወቅት መዳረሻ ላይ ይመጣል- ይህም ማለት ደግሞ- ማርያም እና ዮሴፍ እጮኛሞች የነበሩ እና በወቅቱ በነበረው ሕግ መሰረት ደግሞ አብሮ መኖር በማይችሉበት ወቅት ላይ የመጣ ልጅ ነው። በዚህ ምክንያት በደረሰበት የቅሌት ስሜት የተነሳ ዮሴፍ እጮኛው የነበረችውን ማርያምን በሥውር በመተው መልካም ስሙን ጠብቆ ለመኖር ያስባል፣ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህንን የማድረግ ሕጋዊ የሆነ መብት ቢኖረውም ቅሉ ነገር ግን አስገራሚ በሆነ ሁኔታ የማርያምን ሕልውና አደጋ ላይ ላለመጣል በማሰብ በተቃራኒው የእርሱን መልካም የነበረ ስም አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ በስውር ሊተዋት ፈለገ።
ከዚያም በኋላ ሌላ ያልተጠበቀ ነገር ይከሰታል፡ እግዚአብሔር በህልሙ ተገልጾ የዮሴፍን እቅዶች ይቀይራል፣ ዮሴፍ ማርያምን ወደ ቤቱ እንዲወስዳት ይነግረዋል። ኢየሱስ በዚሁ መልክ ከተወለደ በኋላም እንኳን ሳይቀር ዮሴፍ ለቤተሰቡ ማስተዳደሪያ ይሆን ዘንድ ያወጣውን እቅድ በመተው በተቃራኒው ቤተሰቡን ይዞ ወደ ግብፅ እንዲሄድ እግዚኣብሔር በሕልሙ ተገልጾ ይነግረዋል። በአጭሩ የገና በዓል ያልተጠበቀ የህይወት ለውጥ እንድናመጣ ያደርገናል። የገናን በዓል በሚገባ ማክበር ከፈለግን ልባችንን በመክፈት አስደናቂ የሆኑ ድንግተኛ ስጦታዎችን በመቀበል ያልተጠበቀ የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ማድረግ አለብን።
ይሁን እንጂ ትልቁ ያልተጠበቀ ድንገተኛ ስጦታ የሚመጣው በገና ዋዜማ እለት ነው፣ ታላቅ የሆነው በአንድ ትንሽዬ ሕጻን ልጅ ተመስሎ የመጣል። መለኮታዊ የነበረው ቃል ህፃን ይሆናል፣ ይህም በጥሬ ትርጉሙ "መናገር የማይቻል" ማለት ነው። መለኮታዊ የነበረው ቃል "መናገር አልቻለም”። አዳኙን ለመቀበል በጊዜው የነበሩ ባለስልጣናት ወይም አምባሳደሮች በዚያ ስፍራ በፍጹም አለተገኙም። ነገር ግን በዚያ ስፍራ በሌሊት ስራቸውን በማከናወን ላይ የነበሩ እና መልኣኩ አስገራሚ መልእክት እና ምልክት ካሳያቸው በኃላ በፍጥነት ወደ ሥፍራው የተጓዙት እረኞች ነበሩ። ማን ነበር እርሱን ሊጠባበቅ የሚገባው? የገና በዓል እግዚኣብሔርን የምናከብርበት ወቅት ነው፣ ይህም ከእኛ አመክንቶ ውጪ በመሄድ እርሱን በተስፋ መጠባበቅ ነው።
ስለዚህ በገና በዓል ወቅት በምድር ላይ ሆነን ከሰማይ የሚመጡትን ስጦታዎች መቀበል ማለት ነው። መንግሥተ ሰማያት አዲስ የሆኑ ስጦታዎችን ወደ ምድር ሲልክ እኛ ደግሞ ምድር ምድሩን ብቻ እያየን ለመኖር አንችልም። የገና በዓል ለተለየ ህይወት የምያዘጋጀን አድሲ ዘመን ነው፣ ሰው እንደ እግዚኣብሔር ፈቃድ ራሱን በስጦታ መልክ የሚያቀርብት ወቅት ነው፣ የገና በዓል ለራሳችን የምንኖርበት ወቅት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የምንኖርበት ወቅት ነው፣ ምክንያቱም በገና በዓል እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ነው፣ ከእኛ ጋር አብሮ ስለሚጓዝ እና አብሮ ሰለሚኖር ነው። የገና በዓል ትዕቢታችንን በትህትና የምናሸንፍበት ወቅት ነው፣ ከጩኸት ይልቅ ጸጥታን፣ ለራሳችን ብቻ ከመጸልይ ይልቅ እግዚኣብሔር ሌሎች ሰዎችን ይባክ ዘንድ የምንጸልይበት ወቅት ሊሆን ይገባል።
የገናን በዓለ ማክበር ማለት ልክ እንደ ኢየሱስ መሆን ማለት ነው፣ እርሱ ወደ እኛ እንደ መጣ ሁሉ እኛም ወደ ተቸገሩ ሰዎች መሄድ ወይም መወረድ ማለት ነው። የገና በዓል እንደ ማርያም፣ እግዚኣብሔር በሕይወታችን ምን እንደ ምያደርግ ሳንውቅ በፊት “እሽ” ብለን የእርሱን ቃል በእምነት የምንቀበልበት ወቅት ነው። የገናን በዓል ማክበር ማለት እንደ ዮሴፍ መሆን ማለት ነው፣ እንደ እርሱ እግዚኣብሔር የፈለገውን ነገር በተግባር ላይ ለማዋል መሞከር ማለት ነው፣ ለእኛ ልራሳችን እቅዶች ሳይሆን ለእግዚኣብሔር እቅዶች ቅድምያ መስጠት ማለት ነው። በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ቅዱስ ዮሴፍ የተናገራቸው አንድም ቃላት አናገኝም፣ ዮሴፍ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ምንም ዓይነት ቃል አልተናገረም፣ እግዚኣብሔር ነበር በጸጥታ ለቅዱስ ዮሴፍ ሲናገር የነበረው፣ የተናገረውም በሕልሙ ነበር። በገና በዓል ወቅት ቁሳቁሶችን በመግዛት ከመጠመድ ይልቅ ይህንን የእግዚኣብሔርን ድምጽ የምንፈልግበት ወቅት ሊሆን ይገባል። በገና ዛፍ ስር በዝምታ ተቀምጠን በምናሰላስልበት ወቅት እግዚኣብሔር ለእኛ የሚናገረን ነገር ይኖራል። በዚህ በገና በዓል ወቅት በገና ዛፍ ሥር በዝምታ እንድንቀመጥ እግብዛችኋለሁ። በገና ዛፍ ሥር በጸጥታ ተቀመጡ፣ ጊዜ ስጡ ከዚያም በኋላ እርሱ የሚሰጣችሁን ወይም የሚነግራችሁን ያልተጠበቃችሁን ነገር ታገኛላችሁ።
በሚያሳዝን ሁኔታ ግን የገናን በዓል የምናከብረው ከሰማይ ከሚላኩልንን መልካም ዜናዎች ችላ በማለት ምዳራዊ እና የተለመዱ ነገሮችን በማከናውን በተሳሳተ መልኩ እናከብራለን። የገናን በዓለ እንዲያው በተለመደ እና ባሕላዊ በሆነ መልኩ ብቻ የምናከብር ከሆነ የገና በዓል መአከል እርሱ እግዚኣብሔር ሳይሆን ራሳችን እንሆናለን፣ በዚህም እግዚኣብሔርን የመገናኘት መልካም አጋጣሚ እናጣለን። እባካችሁን የገናን በዓል አለማዊ በሆነ መልኩ አናክብረው። “የእርሱ ወደ ሆኑት መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም ግን አልተቀበሉትም” (ዮሐ. 1፡11) የሚል የቅዱስ ወንጌል ቃል በእኛ ውስጥ ተፈጻሚነት እንዲኖረው መፍቀድ የለብንም። የስበከተ ገናን ሳምንት ከጀመርንበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ቀን ድረስ ያሉት የቅዱስ ወንጌል ቃላት በሕይወት ውስጥ በሚገጥሙን ተግዳሮቶቻችን ተጠምደን ብቻ እንዳንኖር ሲመክሩን ቆይተዋል። ይህንን የገና በዓል እንደ ቅዱስ ዮሴፍ በዝምታ ማሳለፍ ይኖርብናል፣ እንደ ማርያም ለእግዚኣብሔር ጥሪ “እነሆኝ” በማለት ልናከብረው ይገባል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
19 December 2018, 15:47