ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “የስብከተ ገና ወቅት በልባችን ውስጥ መንገድ የምናዘጋጅበት ወቅት ነው”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እውሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በሚነበቡ የእግዚኣብሔር ቃላ ላይ መሰረቱን ያደርገ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በትላንታንው እለት ማለትም በኅዳር 30/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ያደርጉት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተንትኖ የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት የሁለተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ላይ ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 3፡ 1-6 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ” በሚለው የመጥመቁ ዮሐንስ ቃል ላይ ትኩርቱን ባደርጉ ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “በእነዚህ የስብከተ ገና ሳምንታት ውስጥ ‘የሚመጣውን ጌታ በሚገባ ለመቀበል ያስችለን ዘንድ’ መንገድ ማዘጋጀት ይኖርብናል” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 30/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳድችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ባለፈው ሳምንት እሁድ እለት የነበረው የስርዓተ አምልኮ የስብከተ ገናን ወቅት በአግባቡ እንድንኖር እና ጥንቃቄ በተላበሰ ባሕሪ በመዘጋጀት ጌታን በመጠባበቅ ነቅተን እንድንኖር ጥሪ አቅርቦልን ነበር። ዛሬ የጀመርነው ሁለተኛው የስብከተ ገና ስንበት ደግሞ እነዚህን ጥንቃቄዎች በማደርግ መጓዝ የምንችልበትን መንገዶች በመጠቆም መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስችለን ጉዞ መጓዝ እንዴት እንደ ምንችል ተምረናል። ለዚህ ጉዞ እንደ መመሪያ ሆኖ የቀረበው ደግሞ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰው “ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ” (ሉቃ. 3፡3) የሚለው የመጥመቁ ዮሐንስ ቃል ነው። ወንጌላዊው ሉቃስ የመጥምቁ ዮሐንስን ተልዕኮ ለመግለጽ የጥንቱን የኢሳያስ ትንቢት በመደርደሪያነት በመጠቀም “ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል የተስተካከል ይሁን” የሚለውን በማጣቀሻነት ሲጠቀም እናያለን።

ለሚመጣው ጌታ መንገድን ለማዘጋጀት መጥምቁ እኛን የሚጋብዘንን የለውጥ ጥያቄዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ እኛን በከፍተኛ ደረጃ ተብትበው የያዙንን የመቀዝቀዝ ስሜት እና ከቸልተኝነት የሚመነጩን የተስፋ መቁረጥ ስሜቶችን ለይተን በማውጣት ኢየሱስ ለእኛ የምያሳየንን ዓይነት ስሜት ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ያንን ስሜት በመላበስ ራሳችንን ለባልንጀሮቻችን ፍላጎቶች በመክፈት ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ክርስቶስ ለእኛ በምያሳየን ዓይነት ስሜት መንከባከብ ይኖርብናል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በችግር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ማገዝ ተገቢ ነው። በኩራት እና በትዕቢት ስሜት በሕይወታችን በተከሰቱት ስህተቶች የተነሳ የቀዘቀዘውን ሕይወታችንን ከወንድሞቻችን ጋር ተጨባጭ በሆነ መልኩ እርቅ በመፍጠር እና ለሰራናቸው ኃጢኣቶቻችን ይቅርታን  በመጠየቅ ልንኖር ይገባል። በእርግጥ የእኛን ስህተቶች፣ እምነትን ማጉደላችንን እና አለመታዘዛችንን በትህትና በመቀበላችን የተነሳ የተሟላ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እንችላለን።

አማኝ የሚባል ሰው ተጨባጭ በሆነ መልኩ ወንድሞቹን የሚቀርብ ሰው፣ መጥምቁ ዮሐንስ በበራሃ ውስጥ መንገድ እንደ ከፈተ ሁሉ መጥፎ በሚባሉ የሕይወት ገጠመኞች ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ተስፋ እንዲያደርጉ መንገድ በማመላከት ሰዎች ከውድቀት እና ከአሰቃቂ ሽንፈት ነጻ ሆነው እንዲኖር ተጨባጭ በሆነ መልኩ የሚሰራ ሰው እርሱ አማኝ የሆነ ሰው ነው ለማለት እንችላለን። አሉታዊ እና አፍራሽ ወደ ሆኑ ነገሮች ተመልሰን መግባት የለብንም፡ የእኛ የህይወት ማዕከል ኢየሱስ እና የእሱ በብርሃን የተሞሉ ቃላት፣ፍቅር እና የእርሱ መጽናኛ በመሆኑ የተነሳ እኛ የአለም አስተሳሰብ መቀበል የለብንም። መጥምቁ ዮሐንስ በወቅቱ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ በብርታት፣ በመጸጸት እና በትህትና መንፈሳዊ የሆን አለውጥ እንዲያመጡ ሲጋብዝ እናያለን። ሆኖም ግን እርሱ እንዴት መስማት እንዳለበት ያውቅ ነበር፣ ኃጢአታቸውን ለመናዘዝ እና በኃጢአተቸው ተጸጽተው ከኃጢኣታቸው ለመንጻት በማሰብ ለመጠመቅ ወደ እሱ የሚመጡትን ብዙ ወንዶችና ሴቶችን በርኅራኄ እንዴት ማስተናገድ እንደ ሚገባውም በሚገባ ያወቅ ነበር።

ስለ ህይወቱ የሰጠው ምስክርነት፣ ኑፁዕ የሆነ አዋጅ በማወጁ፣ እውነቱን ለማወጅ ያለው ድፍረት እና ብርታት ለረጅም ጊዜ ሲዘገይ የቆየውን የመሲህ ተስፋዎችን በድጋሚ እንዲለመልም በማድረግ እና ተስፋዎችን እንደገና በማነሳሳት ያደርገው ከፍተኛ ጥረት ተሳክቶለታል። ዛሬም ቢሆን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በሙሉ በታላቅ ብርታት የእርሱን ተስፋዎች እንደ ገና ለማለምለም ከሁሉም በላይ ደግሞ  የእግዚአብሔር መንግሥት በየቀኑ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየተገነባ እንደ ሚሄድ በመረዳት የእርሱ ትሁት እና ደፋር ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከራሳችን በመጀመር በእየለቱ ለእግዚኣብሔርን መንገድ ማዘጋጀት እንችል ዘንድ እንድትረዳን እና የትዕግስት፣ የሰላም፣ የፍትህ እና የወንድማማችነት ዘርን በእየአከባቢያችን መዝራት እና ማሰራጨት እንችል ዘንድ እድትረዳን አማላጅነቷን መማጸን ይገባል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
09 December 2018, 16:21