ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 17/2011 ዓ.ም ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

የጎርጎስሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የገና በዓል በደማቅ ሁኔታ በትላንትናው እለት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ከተከበረበት የገና በዓል በመቀጠል ባያለው እለት የቤተ ክርስቲያን የመጀመርያው ሰማዕት የሆነው የቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ በተከበረው የቅዱስ እስጢፋኖስ አመታዊ በዓለ ላይ መስረቱን ያደርገ አስተንትኖ ካደርጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማርያምን አበሰራት” የሚለውን የብስራተ ገብሬል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ለዓለም ባስተላለፉት መልእክት በወቅቱ የመጀመርያው የቤተ ክርስትያን ሰማዕት የሆነውን የቅዱስ እስጢፋኖስን ዓመታዊ በዓል ለማክበር በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች ሰላምታ ማቅረባቸውን ከደረሰን ዜና ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዚህ አሁን ባለንበት እና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በማክበር ላይ በምንገኝበት የገና በዓል ወቅት በማርያም እና በዮሴፍ መካከል የሚገኘውን ሕጻኑን ኢየሱስን በሕይወታችሁ ውስጥ ማሰላሰላችሁን እንድትቀጥሉ በድጋሚ ጥሪ አቀርባለሁ ብለዋል።
በእነዚህ የገና በዓል ቀናት ውስጥ ከሮም እና ከሌሎች የዓለም ክፍሎች “ብዙ የእንኳን አደረስህ መልእክቶችን” መቀበላቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው “ለእያንዳንዱ የእንኳን አደረሰህ መልእክት ምላሽ መስጠት” ግን አለመቻላቸውን ገልጸው ዛሬ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሁላችሁም በማመስገን እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፣ በጸሎት ከእኔ ጋር ስለሆናችሁም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ብለዋል። ቅዱስነታቸው በመቀጠልም ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው መልካም የቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ለሁላችሁም ይሁን በማለት መልካሙን ሁሉ ከተመኙ በኋላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ አትዘንጉ” ካሉ በኋላ ሰላምታን አቅርበው መሰናበታቸውን ለቫቲካን ዜና ከደረሰው ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።


 

26 December 2018, 16:16