ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከብስራተ ገብርኤል ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኅዳር 23/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበስቡ ምዕመናን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው ካደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በመቀጠል  ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት እና በዕለተ ሰንበት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ከሚቀርቡ የመማጸኛ ጸሎቶች መካከል አንዱ እና ዋነኛ የሆነውን “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለውን የመልኣኩ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 23/2011 ዓ.ም የተጀመረውን የስብከተ ገና ሳምንት በማስመልከት ቅዱስነታቸው እንደ ተናገሩት የስብከተ ገና ሳምንታት የተስፋ ወቅት እንደ ሆኑ ገልጸው በተለይም ደግሞ በአሁኑ ወቅት በሶሪያ ላለፉት ስምንት አመታት ያህል በመካሄድ ላይ ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሕጻናትን በጸሎታቸው እንደ ሚያስቡ ገልጸው በዚህ ረገድ ተስፍ ሳንቆርጥ አንድ ቀን ሰላም እንደ ሚፈጠር በማሰብ መጠበቅ እንደ ሚገብ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። “በስቃይ ውስጥ የሚገኙ አባያተ ክርስቲያናትን” በመርዳት የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅት፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን በማስተባበር ለሶሪያ ሕጻናት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በማድረግ ላይ ላለው ጥረት ከፍተኛ ምስጋናን ያቀረቡት ቅዱስነታቸው በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዛቦች በሶሪያ ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲፈጠር የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ቅዱስነታቸው በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

በሶሪያ እና በአጠቅላይ በመካከለኛው ምስራቅ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ጥቃት ይቆም ዘንድ ሁላችንም በአንድነት መጸለይ ይጠበቅብናል ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህም መልኩ በዚያው የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ የምሕረት፣ የይቅርታ እና የእርቅ ሂደቶችን በሚገባ ማስኬድ ይችሉ ዘንድ በጸሎታችን ልንደግፋቸው የገባል ብለዋል። በቅርብም ሆነ በሩቅ በተለያዩ ጦርነቶች ምክንያት በመስቃየት ላይ ለሚገኙ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን አጋርነቷን ለመግለጽ ከእነሩስ ጋር በጸሎት እንደ ምትተጋ የገለጹት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይ መልኩም በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተለያዩ ጦርነቶችን በማቀጣጠል ላይ የሚገኙ ሰዎችን እግዚኣብሔር በምሕረቱ ይቅር እንዲላቸው በተጨማሪም የጦር መሳርያ የሚያመርቱትን ሁሉ እግዚኣብሔር ይቅር እንዲላቸው እና ልባቸውን ወደ መልካም ልብ እንዲቀይር መጸለይ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ከሳምንታዊ መልእክታቸው በመቀጠል በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕማናን፣ መንፍሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው እንደ ተለመደው “አባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትረሱ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ለእለቱ ያዘጋጁትን ሳምንታዊ መልእክት አጠናቀዋል።

02 December 2018, 16:36