ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ትናንሽ የሚባሉ የልግስና ተግባሮች ልበ ሰፊ እንድንሆን ያደርጉናል!”

መልካም ነገር ለማድረግ መጨነቅ ይኖርብናል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነችስኮስ ቀሳውስት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ በሕዳር 17/2011 ዓ.ም ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በእለቱ ከሉቃስ ወንጌል (21፡1-4) ላይ ተወስዶ በተነበበው እና አንዲት ድሃ መበለት ሁለት ሳንቲሞችን በመጽዋዕት መስጫ ውስጥ ማስገባቷን ኢየሱስ በተመለከተበት ወቅት ይህቺ ድሃ ሴት ያላትን ሁሉ ሰጠጭ በማለት ኢየሱስ ማድነቁን በሚገልጸው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ተመርኩዘው ባሰሙት ስብከት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ትናንሽ የሚባሉ የልግስና ተግባሮች ልባችን እንዲሰፋ የማድረግ ብቃት እንዳላቸው ገልጸው የልግስና ጠላት የሆነው ደግሞ የፍጆታ ዕቃዎችን ገዝቶ የማካበት ባሕል መሆኑን ገልጸው ይህ አደገኛ በመሆኑ የተነሳ ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ገለጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ትንናንሽ የሚባሉ የልግሥና ተግባሮችን በማከናወን ሳይቀር ለድሆች ምጽዋዕት መመጽወት እንደ ሚገባ በማሳሰብ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የልግስና ተግባሮች ሁሉ ጠላት የሆነውን ሁሉንም ነገር ለራሳችን የማጋበስ አባዜ በመተው የልግስና ባሕል በማዳበር ካለን ለተቸገሩ ሰዎች ማካፈል ይጠበቅብናል ብለዋል። ልግስና ልብን እንደ ሚያስፋ እና ማራኪ የሆነ ሕይወት እንድንኖር እንደ ሚረዳን በስብከታቸው ወቅት የገለጹት ቅዱስነታቸው በበርካታ ጊዜያት በወንጌሉ ኢየሱስ በሀብታምና በድሃ መካከል ያለውን ልዩነት በንጽጽር በማሳየት የሀብታሙን ሰው እና አልዓዛርን ወይም ሀብታም የነበረ ወጣት ሰው ታሪክ በማስታወስ ያስተምር እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

“አንድ አብታም የሆነ ሰው ወደ መንግሥተ ሰማይ ከሚገባ ይልቅ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብታልፍ ይቀላል” በማለት ኢየሱስ መናገሩን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ ንግግሩ የተነሳ ኢየሱስ እንደ አንድ ኮሚኒስት ተደርጎ ተፈርጆ እንደ ነበረ ገልጸው “ነገር ግን ጌታ እነዚህን ነገሮች ሲናገር ከሀብት በስተጀርባ ሁልጊዜ የዓለም ጌታ የሆነው መጥፎ መንፈስ” እንዳለ ያውቅ ስለነበረ ነው፣ በዚህም ምክንያት ነው ኢየሱስ “አንድ ሰው የሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፣ እግዚኣብሔርን እና ሐብትን በአንድነት ማገልገል አይችልም” በማለት የተናገረውም በዚሁ ምክንያት ነው ብለዋል።

የልግስና መንፈስ የሚመነጨው በእግዚአብሔር በመታመን ነው

ዛሬ (ሕዳር 17/2011 ዓ.ም) ከሉቃስ ወንጌል 21፡1-4 ተወስዶ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ በንጽጽር እንደ ተገለጸው በጣም ብዙ የሆነ ገንዘብ በምጽዋት መስጫ ውስጥ ሲከቱ የነበረ ሐብታሞች መካከል እና 2 ሳንቲሞችን በጣለችው በድሃዋ መበለት መካከል ያለውን ልዩነት በንጽጽር እንደ ምያቀርብ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል። እነዚህ በዛሬው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱት አብታም የተባሉ ሰዎች በሉቃስ ወንጌል 16፡19-31 ላይ እንደ ተጠቀሰው “አልዓዛር የተባለ ድሃ ሰው በደጁ ላይ ቁጭ ብሎ ስለምን እንደ ነበረው ቀይ ልብስና ቀጭን የተልባ እግር የለበሰ አንድ ባለ ጠጋ ሰው “ክፉ” የሆኑ ባለ ጠጋ ሰዎች እንዳልነበሩ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በአንጻሩ በዛሬው ቅዱስ (ሉቃስ ወንጌል 21፡1-4) ወንጌል ውስጥ የተጠቀሱ ባለ ጠጋ የተባሉ ሰዎች “ቤተመቅደስ በመሄድ ምጽዋዕት የሰጡ ሰዎች በመሆናቸው የተነሳ መልካም የሚባሉ ባለ ጠጋ ሰዎች ናቸው” በዚህም የተነሳ የእነርሱ ጉዳይ የሚገመገመው በተለየ ሁኔታ ሊሆን እንደ ሚገብ የገለጹት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ የመረጠበት ዋነኛው ምክንያት “ያቺ ደሃ የሆነች መበለት ከተረፋት ሳይሆን ልኑሮዋ ያለትን በሙሉ መስጠቷን” ለማመላከት ብሎ ኢየሱስ የተጠቀመበት ምሳሌ እንደ ሆነ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። በወቅቱ በእስራኤል ማሕበረሰብ ውስጥ መበለቶች፣ ስደተኞች፣ ወልጃ አልባ ልጆች በከፍተኛ ድህነት ከሚሰቃዮ ሰዎች መካከል ይመደቡ እንደ ነበረ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ በአስተምህሮዎቹ ድሃ ስለሆኑ ሰዎች መናገር ሲፈልግ እነዚህን የኅበረተሰብ ክፍል በዋቢነት እንደ ሚጠቀም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገለጸዋል። ይህች ሴት በአምላክ ላይ እምነት ስለነበራት፣ በብጽዕና የተሞላ ሕይወት የነበራት ሴት፣ በጣም ለጋስ የነበረች ሰው በመሆኑዋ የተነሳ "ጌታ ከሁሉም ነገሮች በላይ የሆነ መሆኑን በመረዳት ለቀሪው ሕይወቷ ሳትጨነቅ ያላትን ሁሉ መስጠቷን ቅዱስነታቸው አስታውሰው የዚህ የቅዱስ ወንጌል ክፍል ዋናው መልእክት ሁላችንም ለጋሾች እንሆን ዘንድ ጥሪ የሚያቀርብልን የቅዱስ ወንጌል ክፍል መሆኑን ቅዱስነታቸው ገለጸዋል።

መልካም ነገር ለማድረግ መጨነቅ ይኖርብናል

በዓለም ላይ ካለው የድህነት አሃዝ ጋር በተያያዘ መልኩ በረሃብ እየሞቱ የሚገኙ የሕጻናት ቁጥር መጨመር፣ በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ ሰዎች መብዛት፣ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት እና በአጠቃላይ ድሃ የተባለው የማኅበርሰብ ክፍል ቁጥር በእየለቱ እየጨምረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ይህ ዜና በእየለቱ በተለያዩ የመገናኛ ብዙዓን አውታሮች እና በየጋዜጦች ላይ በሰፊው እይተሰራጨ ባለበት በአሁኑ ወቅት “ይህንን ችግር እንዴት ነው ለመፍታት የምችለው?” በማለት ጥያቄ ማንሳት እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ከእያንዳንዱ አዎንታዊ ጭንቀት ውስጥ መልካም የሆነ ሐሳብ ሊመነጭ እንደ ሚችል በስብከታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው አንድ ጥቂት ገንዘብ ያለው ሰው ይህንን ገንዘብ በስጦታ ብለግስ በጣም ትንሽ በመሆኑ የተነሳ ምን ሊፈይድ ይችል? ብሎ ማሰቡ እንደ ማይቀር አስታውሰው በዚህ መልኩ መብሰልሰል አሰፍላጊ ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን በመባ መስጫ ውስጥ ሁለት ሳንቲም እንደ ጣላችሁ መበለት እግዚኣብሔር የዚህንም ሰው ስጦታ በዚሁ መልኩ ነው የሚቀበለው ብለዋል።

ከመጠን በላይ የሆነ ፍጆታ

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ውስጥ በስፋት ከሚታዩ በሽታዎች መካከል አንዱ ከመጠን በላይ በሆነ መልኩ የፍጆታ ዕቃዎችን መጠቀም እንደ ሆነ በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ለሕይወታችን ከሚያስፈልጉን ነገሮች ባሻገር ያልተገቡ ብዙም ጠቃሚ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ማገበስ በራሱ ለጋስ እንዳንሆን እንቅፋት እንደ ሚሆን ገልጸው ይህንን በአሁኑ ወቅት የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የፍጆታ እቃዎችን ከመጠን በላይ የመጠቀም ባሕል በመጠኑም ቢሆን ማስወገድ ከቻልን ካለን ለድሆች በማካፈል ለጋሾች እንድንሆን በማድረግ ልበ ሰፊ እንድንሆን ይረዳናል ብለዋል።

ልግስና ወደ ጽድቅ መንገድ ይመራል

ሁሉንም የሰው ልጆች ልያስተናግድ የሚችል ልበ ሰፊነትን መላበስ እንደ ሚያስፈልግ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በሉቃስ ወንጌል 21፡1-4 ውስጥ የተጠቀሱት “በቤተመቅደስ ውስጥ ምጽዋዕት የሰጡት ሐብታም ሰዎች በጣም መልካም የሚባሉ ሰዎች ሲሆኑ ነገር ግን በአንጻሩ ያላትን ሁሉ ሳታስቀር፣ ለሕይወቷ ሳትሳሳ ምን እበላለሁ፣ እንዴት እኖራለሁ ሳትል ያላትን ሁሉ የሰጠችው መበለት ደግሞ ያላትን በሙሉ በመስጠቷ የተነሳ ቅድስት ብለን ልንጠራት እንችላለን ያሉት ቅዱስነታቸው ከቤታችን ጀመሮ የምናደርጋቸው ትናንሽ በሚባሉ የልግሥና ተግባራት ላይ በመሳተፍ ይህንን ለጋስነታችንን ቀሰ በቀስ በማሳደግ ወደ ቅድስና የሚወስደውን ጎዳን መከተል ይኖርብናል ካሉ በኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 

 

26 November 2018, 15:38