ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬውቬን ሪቪሊን ጋር ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬውቬን ሪቪሊን ጋር  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬውቬን ሪቪሊን ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 06/2011 ዓ.ም የእስራኤል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬውቬን ሪቪሊን ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው የታወቀ ሲሆን የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሬውቬን ሪቪሊን ይህንን ጉብኝት ያደረጉት በቅድስት መንበር እና በእስራኤል መንግሥት መካከል የዛሬ 25 ዓመት የተመሰረተውን የዲምሎማሲ ግንኙነት ለመዘከር እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በእነዚህ 25 ዓመታት ውስጥ በቅድስት መንበር እና በእስራኤል፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለፉት 25 ዓመታት የነበረው የዲፕሎማሲ ግንኙነት በአብዛኛው መልካም የሚባል እንደ ነበረ በግንኙነቱ ወቅት የተገለጸ ሲሆን ነገር ግን በእስራኤል ሀገር የሚገኙ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እና በእስራኤል ሀገር የመንግሥት ተቋማት መካከል የጋራ ጥቅምን በተመለከተ ያለው ግንኙነት ከቀን ወደ ቀን መሻሻል ባለበት ድረጃ እየሄደ እንዳልሆነ በወቅቱ መገለጹን ከቅድስት መንበር ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በሁለቱ ሀገራት መካከል መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል

በቫቲካን እና በእስራኤል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር በሁለቱም ሀገራት መካከል ጠንካራ የሆነ የመተማመን ስሜት መፍጠር እንደ ሚገባ በግንኙነቱ ወቅት የተገለጸ ሲሆን በተለይም ደግሞ በሁለቱ ሀገራት መካከል ብዙን ጊዜ ቅራኔ እንዲፈጠር የሚያደገው በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል በእየጊዜው የሚነሰው ግጭት በመሆኑ የተነሳ ይህንን ልዩነት ለመፍታት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን መተማመን ለማጠንከር በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ቀደም ሲል የተደርጉትን ስምምነቶች ማክበር እንደ ሚገባም ተገልጹዋል። በወቅቱ የአይሁዳዊያን፣ የክርስቲያኖች እና የሙስሊሞች መቀመጫ የሆነችው እና ለእነዚህ ሦስት የዓለማችን ዋና ዋና የሐይማኖት ተቋማት በጣሚ አስፈላጊ እና ታሪካዊ ገጽታ ያላት የእየሩሳሌም ጉዳይ መነሳቱ የተገለጸ ሲሆን እየሩሳሌም ለሁሉም ሐይማኖቶች አስፈላጊ የሆነች ስፍራ በመሆኑዋ የተነሳ የጦርነት እና የግጭት ሳይሆን የሰላም ከተማ ሆና መቀጠል እንደ ሚገባት በወይይቱ ወቅት ተገልጹዋል።

በሰላም ለመኖር ውይይት ማድረግ ያስፈልጋል

በመጨረሻም በቀጠናው ውስጥ በተለያዩ ግጭቶች እና በሰብአዊ ቀውሶች ምክንያት የተከሰተውን "የፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሁኔታ አስመልክቶ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነስኮስ እና የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሬውቬን ሪቪሊን መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህ ዐውደ ዙሪያ በመሥራት እና ሰላምን በቀጠናው ዘላቂ በሆነ መንገድ ለማስፈን ይችላ ዘንድ ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት ጋር ተገናኝቶ መወያየት እንደ ምያስፈልግ በሁለቱ ሀገራት መካከል መግባባት ላይ እንደ ተደረሰ ለመረዳት ተችሉዋል።

Photogallery

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእስራኤል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ሬውቬን ሪቪሊን ጋር
15 November 2018, 13:39