ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ መናኒያን እያበረከቱ ለሚገኙት አስተዋጾ ቤተ ክርስቲያን ምስጋና ታቀርባለች

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በትላናትናው እለት ማለትም በሕዳር 12/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አሰትምህሮ በመቀጠል በእለቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅነቷ በወላጆቿ በሐና እና በእያቄም አማካይነት ለእግዚኣብሔር ልጅ ማደሪያ ትሆን ዘንድ የተገባች እንድትሆን በማሰብ ወላጆቿ ማርያምን በሕጻንነቷ ወደ ቤተ መቅደስ በመውሰድ እንድትቀደስ ማድረጋቸውን የሚያስታውስ ቀን ተዘክሮ ማለፉን ምክንያት በማደረግ እና በተመሳሳይ መልኩ በተመሳሳይ ቀን የተከበረውን ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን አስመልከተው ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት እንደ ገለጹት ዓለማቀፍ የመናኒያን ቀን ስናከብር ያለምንም ስስት ሕይወታቸውን በምስጢር በምልኣት ለእግዚኣብሔር በመስጠት እየኖሩ የሚገኙ በጣም ብዙ ወንድ እና ሴት መናኒያን እንደ ሚገኙ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ይህም ድርጊት እግዚኣብሔርን እንድናመሰግን እድሉን ይሰጠናል ብለዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባስተላለፉት መልእክት የሚከተለውን ብለዋል . . .

ዛሬ (ሕዳር 12/2011 ዓ.ም የአውሮፓዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ፣ በላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት) እምቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የተወሰደችበትን እለት በምንዘክርበት ወቅት፣ በተመሳሳይ መልኩ ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር የሰጡ መናኒያን ቀን በመከበር ላይ ነው፣ እነርሱም ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው! ይህም እግዚኣብሔርን እንድናመሰግን እንድሉን የሚከፍት አጋጣሚ ሲሆን በየገዳማቱ እና በየሸለቆዎች ውስጥ በጸሎት መንፈስ በምልኣት ሕይወታቸውን ለእግዚኣብሔር በመስጠት፣ በዝምታ እና በስውር የሚኖሩ መናኒያን ለቤተ ክርስቲያን እያበረከቱ ለሚገኙት አስተዋጾ እግዚኣብሔርን እናመስግናለን። ለመናኒያን ያለንን ፍቅር እና አጋርነት በመግለጽ ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊውን ነገር በማድረግ ከእነርሱ ጎን እንደ ምትቆ ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

21 November 2018, 14:09