ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ “ለድሃ መበለቶች ማሰብ ይኖርብናል” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በዕለቱ በሚነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተመርኩዘው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መረዐ ግብር መሰረት ቅዱስነታቸው በሕዳር 02/2011 ዓ.ም ያደርጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በዕለቱ ከማርቆስ ወንጌል 12፡38-44 ተወስዶ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ  መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አቅመ ደካሞችን የሚበድሉ ሰዎችን ኢየሱስ ያጋልጣቸዋል፣ ኢየሱስ ሁሌም ቢሆን ከአቅመ ደካሞች ጎን ይቆማል ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 02/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

የዛሬው የቅዱስ ወንጌል ክፍል (ማር 12 38-44) ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ውስጥ እያደርገ የነበረውን ተከታታይ አስተምህሮዎች በመቀጠል ተቃራኒ ገጽታ ያላቸውን የአንድ ጸሐፊ እና የአንድ መበለት ታሪክ በመጠቀስ ይጠናቀቃል። ነገር ግን ተቃራኒ የሆነ ገጽታ አላቸው የምንለው ለምንድነው? በአንድ በኩል አስፈላጊ፣ ሀብታም፣ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች የሚገልጽ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መበለት - የተናቁ፣ ድሆችን፣ አቅመ ደካሞችን ሰለ ምያመልክት ነው። በእውነቱ ኢየሱስ ጸሐፍትን በተመለከተ ተሰጠው ፍርድ ሙሉ በሙሉ ሁሉንም ጸሐፍት የሚመለከት ባይሆንም ነገር ግን ከእነርሱ መካከል በማኅበርሰቡ ውስጥ የበላይነት ለማሳየት፣"ራቢ" ማለትም "መምህር" በመባል መጠራት የሚፈልጉትን፣ የክብር ቦታ ለመያዝ የሚፈልጉትን ሰዎች ለመጥቀስ ፈልጎ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ የሚጸልዩበት ምክንያቱ ሃይማኖታዊ የሆነ እሴት የለውም ምክንያቱም ኢየሱስ እንደ ሚለው “በሰዎች ፊት ለመታየት ፈልገው ረጅም ጸሎት ያደርጋሉ”፣ ሕግን በማስከበር ብቻ በእግዚኣብሔር የሚያምኑ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ። እንደዚህ ዓይነት የበላይ ለመሆን መፈለግ እና የኩራት አስተሳሰብ ሌሎች ደካም እንደ ሆኑ አድርጎ በመቁጠር ወይም በጣም አቅመ ደካማ ለሆኑ እና ዝቅተኛ ለሆኑ መበለቶች እና እንደ እነርሱ ዓይነት ለሆኑ ሰዎች ንቀት እንዲያሳዩ አድርጓቸዋል።

ኢየሱስ እንዲህ ዓይነቱን ብልሹ የሆነ አሰራር ያጋልጣል፡ ሀይማኖትን ሽፋን ያደርገ እና በሐይማኖት ተነሳሽነት ላይ ተመስርቶ አቅመ ደካም የሆኑ ሰዎችን መጨቆን አይገባም በሰተመጨረሻ እግዚአብሔር ከአቅመ ደካሞች ጎን ይቆማል። እናም ይህን ትምህርት በደቀ መዛሙርቱ አእምሮ ውስጥ በደንብ ተቀርጾ ይቀር ዘንድ ኢየሱስ ሌላ ተጨማሪ ሕያው የሆነ ምሳሌ ለደቀ-መዛሙርቱ ይሰጣቸዋል፡ ድሃ የሆነች መበለት፣ መብቷን ሊያስከብርላት ይችል የነበረው ባሏ በመሞቱ የተነሳ በማኅበርሰቡ ውስጥ እዚህ ግባ የሚባል ቦታ የሌላት፣ የሚረዳት ሰው ባለመኖሩ የተነሳ ብር መበደር እንኳን የማትችል፣ ባለ ሐብቶች አቅመ ደካማዎችን በማሳደድ የሚበዘብዙዋቸው አቅመ ደካሞችን የተመለከተ ምሳሌ ይነግራቸዋል። ይቺ መበለት በቤተመቅደስ ውስጥ በሚገኘው የምጽዋት ማስቀመጫ ውስጥ  ያላትን ሁሉ ምንም ሳታስቀር ሁለት የናስ ሳንቲሞችን ታስቀምጣለች፣ ይህንንም መጽዋት የሰጠጭው ተደብቃ ማንም ሰው ሳያያት ነበር፣ በጣም ትንሽ የሚባል ስጦታ በመሆኑ የተነሳ እፍረት ተሰምቱዋት ነበር። ነገር ግን በዚህ ትህትና ውስጥ እጅግ በጣም ትልቅ ትርጉም ይገኛል፣ ሐይማኖታዊና መንፈሳዊ በሆነ መንፈስ የተፈጸመ አስፈላጊ የሆነ ድርጊት ነው። ይህ በታላቅ መስዋዕትነት የተደርገ የመበለቷ ተግባር ከኢየሱስ እያታ አላመለጠም፣ በእርግጥ ይህ ተግባር ሁለንተናዊ የሆነ ስጦታ መስጠት አስፈላጊ እንደ ሆነ የሚገልጽ አስተምህሮ ለደቀ-መዛሙርቱ እንድያደርግ ያነሳሳዋል።

ኢየሱስ ዛሬ ለእኛ የሰጠው ትምህርት በሕይወታችን ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር ለይተን እንድናውቅ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ዕለታዊ በሆነ መልኩ ንጹህ የሆነ ግንኙነት እንድንመሰረት ይረዳናል። ወንድሞቼ እና እህቶቼ የእግዚኣብሔር መመዘኛ ከእኛ መመዘኛ በእጅጉን ይለያል። እርሱ ሰዎችን እና የሰዎችን ተግባር የሚመለከተው ለየት ባለ መልኩ ነው፡ እግዚኣብሔር ብዛትን ሳይሆን የሚመለከተው ጥራትን ነው፣ ልባችንን ይፈልጋል፣ የጸዳ አስተሳሰብ እንዲኖረን ይፈለጋል። ይህም ማለት በጸሎት ለእግዚኣብሔር መሰጠት ማለት እና ለሌሎች ሰዎች ደግሞ እንዲሁ ሐይማኖታዊ የሆኑ ስነ-ስረዓቶችን ለሟሟላት እና እንዲሁ ለይስሙላ በሒሳብ ስሌቶች ከተሞላ ስነ-አመክንዮ ነጻ የሆነ ልገሳ ማድረግ ማለት ነው፣ ኢየሱስ ለእኛ እንዳደረገው እኛም በነጻ የተቀበልነውን በነጻ መስጠት ማለት ነው፣ እርሱ እኛን በነጻ ነው ያዳነን፡ በገንዘብ አይደለም ያዳነን። እንዲሁ በነጻ ነው ያዳነን። እኛም ነገሮችን ስናከናውን በዚሁ መልክ እንዲሆን ያስፈልጋል። ኢየሱስ የእዚያች ድሃ የሆነች መበለት ልገሳ የክርስትና ሕይወት አርዓያ እንዲሆን በምሳሌነት የተጠቀመው በዚሁ ምክንያት ነው። እኛ የዚህች መበለት ስም ማን እንደ ሆነ ባናውቅም ነገር ግን ልቧን በደንብ አውቀነዋል-በእርግጠኛነት በመንግሥተ ሰማይ እናገኛታለን-በዚያም ሰላም እንላታለን-በእግዚኣብሔር ዘንድ መልካም የሚያሰኘው የዚህ ዓይነት ተግባር ነው። ራሳችንን ለራሳችን ብቻ በመክፈት እና የምንሰራቸውን መልካም ነገሮችን የምንቆጥር ከሆነ፣ ሌሎችን ለመመልከት በጣም ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ስናሳይ፣ . . . ይህንን ቃል እንድጠቀም ፍቀዱልኝ እንደ “ፒኮክ” እዩኝ እዩኝ የምንል ከሆነ የድሃዋን መበለት ተግባር ማሰብ ይኖርብናል። መልካም እንድንሆን ያደርገናል፣ አስፈላጊና ዋና ወደ ሆነው ነገር እንድንሄድ እና ትሑት ሆነን ለመኖር እንድንችል ይረዳናል።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
11 November 2018, 15:30