ፈልግ

2018.11.04 Angelus 2018.11.04 Angelus 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ፡ “ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀሮቻችን ያለንን ፍቅር መግለጽ ብልሃት ነው!”

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በዕለቱ ሰረዓተ አምልኮ ወቅት በሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት ላይ ተመርኩዘው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መረዐ ግብር መሰረት በጥቅም 25/2011 ዓ.ም ያደረጉት አስተንትኖ በወቅቱ ከማርቆስ ወንጌል 12፡28-34 ላይ ተወስዶ በተነበበው እና ከጻፎችም መካከል አንዱ ቀርቦ ኢየሱስን “ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የተኛው ነው? ብሎ በጠየቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደርገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ለእግዚአብሔር እና ለባልንጀሮቻችን ያለንን ፍቅር መግለጽ ብልሃት ነው” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ- ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥቅምት 25/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘት እንደ ምከተለው ተርጉመነዋል አብራችሁን በመሆን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ዕለተ ሰንበት የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 12፡28-34) መአከላዊ ይዘቱ እግዚኣብሔርን ውደድ፣  ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ የሚል የፍቅር ትዕዛዝ እናገኛለን። ከጻፎችም አንዱ ቀርቦ ኢየሱስን “ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የቱ ነው? (ማር. 12፡28) በማለት ኢየሱስን ይጠይቀዋል። ኢየሱስም ሁሉም እስራኤላዊ የራሱን ቀን የሚጀምርበት እና ቀኑ ሲጠናቀቅ ደግሞ ቀንኑን የሚዘጋበትን በቃላት የሚጀምረውን እና የእነርሱ እምነት መግለጫ የሆነውን “እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” (ዘዳግም 6፡4) የተጠቀሰውን በመገለጽ መልስ ይሰጣል። በዚህ መንገድ የእስራኤል ሕዝቦች የእመነታቸውን መሠረታዊ የሆነ እውነታ ጠብቀው ቆይተዋል፣ እነርሱ “የእኛ” የሚሉት አንድ አምላክ ብቻ አለ፣ ምክንያቱም እርሱ የወደደን፣ የሚወደን፣ ለወደፊቱም እስከ ዘለዓለም የሚወደን መሆኑን በማሳየት እርሱ ከእኛ በፍጹም የማይነጠል መሆኑን ለማሳየት ነው። ከዚህ አስተሳሰብ ውስጥ “በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ (. . .)  ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” (ማር. 12፡30-31) የተባሉ ሁለት ትእ|ዛዛት ይመነጫሉ።

እግዚኣብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን እነዚህን ሁለት ትእዛዛት አንድ አድርጎ በማቀናጀት ኢየሱስ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እነዚህ ሁለት ትእዛዛት የማይነጣጠሉ መሆናቸውን፣ ይልቁንም አንዱ አንደኛውን የሚደግፍ መሆኑን በመግለጽ ያስተምራል። እነዚህ ትእዛዛት ምንም እንኳን በቅደም ተከተል ቢቀመጡም እነሱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው፣ እነዚህን ሁለት ትእዛዛት በአንድነት አቀናጅቶ ለመኖር ከተሞከረ ለአማኙ እውነተኛ ጥንካሬ ይሰጣሉ። አምላክን መውደድ በእርሱ ውስጥ እና ለእርሱ፣ ለእርሱ ሕልውና እና እርሱ ለሚሰራው ሥራ መኖር ማለት ነው። አምላካችን ያለ ምንም ገደብ የሚሰጠን ጸጋ ነው፣ ያለምንም ገደብ ይቅርታ የሚያደርግልን ነው፣ እኛን የሚደግፍ እና ወደ ፊት እንድንጓዝ የምያደርገን ግንኙነት ነው። እግዚአብሔርን መውደድ ማለት የእርሱ ተባባሪዎች በመሆን  ያለምንም ገደብ ባልንጀራዎቻችንን ለማገልግል መነሳሳት፣ ያለገደብ ይቅር ለማለት እና የጋራ መግባባት በመፍጠር እና የወንድማማችነት ግንኙነቶችን ለማዳበር በመፈለግ በየቀኑ ኃላችንን እና ሐብታችንን አሟጠን መጠቀም ማለት ነው።

ወንጌላዊው ማርቆስ ባልንጀራችን ማን መሆኑን ለማብራራት ብዙም አልተጨነቀም፣ ምክንያቱም ባልነጀራ የሚባሉ ሰዎች በዕየለቱ በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙን ሰዎች በመሆናቸው የተነሳ ነው። ባልነጀራችን ማን እንደ ሆነ አስቀድሞ ለመግለጽ አልፈለገም፣ ነገር ግን በዕየለቱ ዓይናችንን እና ልባችንን ከፍተን የእነሩሱን መልካምነት መመኘት እና መፈለግ ማለት ነው። ነገሮችን በኢየሱስ እይታ መመልከት ያስችለን ዘንድ እራሳችንን የምናለማምድ ከሆነ፣ በችግር ላይ ያሉትን ሰዎች መመልከት እና ማዳመጥ እንችላለን ማለት ነው። የባልንጀራዎቻችን ችግሮች እነርሱ ከመናገራቸው በፊት እንኳን ውጤታማ የሆነ መፍትሄዎች ያስፈልጉታል። ይህንንም የምናደርገው ለተቸገሩ ባልንጀራዎቻችን ዳቦ በመስጠት ብቻ ሳይሆን ልንወጣው የሚገባው ነገር ግን በፈገግታ፣ በማዳመጥ እና በጸሎት እነዚህን ሁሉ ነገሮች አንድ ላይ በማቀናጀት ሊሆን ይገባል። እጅግ በጣም ድሃ ለሆኑ ወንድሞቻችን ሁሉ አስቸኳይ የሆነ እርዳታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን ነገር ግን ከሁሉም በላይ ለሕይወታቸው ስሜት እዲሰጡ መርዳት እና በወንድማማችነት መንፈስ እነርሱን መቅረብ አስፈላጊ እንደ ሆነ የዛሬው እለት ቅዱስ ወንጌል ሁላችንንም ይጋብዘናል። ይህም የክርስቲያን ማኅበርሰብን እየገጠመው የሚገኝ ፈተና ነው፡ ብዙ ተነሳሽነት ብቻ የምታይበት ማኅብረሰብ በማስወገድ በተቃራኒው ደግሞ ብዙ እና መልካም የሆነ ግንኙነት ያለው ማኅበረሰብ መፍጠር ያስፈልጋል፣ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ብቻ ማዳበር ሳይሆን አብሮ በአንድነት መጓዝን በአጠቃላይ በተሟላ ሁኔታ ክርስቲያናዊ የሆኑ ስሜቶች የሚንጸባረቁበት ማኅበረሰብ መፍጠር ይገባል። ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር እኛን የፈጠረው ለፍቅር ነው፣ ምክንያቱም በእርሱ በመኖር ሌሎችን ማፍቀር እንድንችል ነው። እግዚአብሔርን ሳንወድ በተቃራኒው ደግሞ ባልንጀሮቻችንን እንወዳለን ብለን ብናስመስል ይህ የተሳሳተ ሐሳብ ነው፣ በተመሳሳይ መልኩም እግዚኣብሔርን እንደ ምንወድ ብናስመስል እና ነገር ግን በተቃራኒው ባልንጀሮቻችንን ባንወድ ይህም የተሳሳተ ሐሳብ ነው። የእነዚህ ሁለት የፍቅር ማለትም እግዚአብሔር እና ባልንጀሮቻችንን መውደድ የተሰኙ ትእዛዛት በአንድ ላይ ሲተገበሩ ትክክለኛ የክርስቶስ ደቀ-መዛሙርት እንደ ሆንን ይመሰክራሉ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ውብ የሆነ አስተምህሮ በእየለቱ ሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ እንችል ዘንድ እርሷ ትርዳን።

ይህንን ዘገባ በድምጽ ለመከታተል ከዚህ በታች ያለውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!

 

Photogallery

ምዕመናን የጥቅምት 25/2011 ዓ.ም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
05 November 2018, 15:59