ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ጋብቻ ከ”እኔ” ወደ “እኛ” መንፈስ መጓዝ ማለት ነው”!

“ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳትና ራሱንም ስለ እርሷ አሳልፎ እንደ ሰጠ፣ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ ባሎችም እንደዚሁ ሚስቶቻቸውን እንደገዛ ሥጋቸው መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል። ስለዚህም ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ”። 32ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እናገራለሁ” (ኤፌሶን 5፡25.28.31-32) ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተመርኩዘው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ምያደርጉ ይታወቃል። በዚህም መሰረት በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 21/2011 ዓ.ም ያደርጉት የትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም በዐስርቱ ትዕዛዛት ዙርያ የጀመሩት አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በዛሬው እለት ያደርጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም ባለፈው ሳምንት የጀመሩት እና “አታመዝር”  በምለው በስድስተኛ ትዕዛዝ ላይ ትኩረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “መጋባት ማለት ጋብቻን መፈጸም ማለት አይደለም ነገር ግን ከ “እኔ” ወደ “እኛ” መንፈስ መጓዝ ማለት ነው” ማለታቸውን ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ታዳሚዎች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዛሬው ዕለት ማለትም በጥቅምት 21/2011 ዓ.ም በቫቲካን በምገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል አባራችሁን በመሆን እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደ ምን አረፈዳችሁ!

ከዚህ ቀደም ከዐስርቱ ትዕዛዛት አንዱ በሆነው “አታመንዝር” በሚለው በ6ኛው ትዕዛዝ ዙርያ የጀመርነውን አስተምህሮ በመቀጠል የክርስቶስ ታማኝ ፍቅር የሰው ልጅ ሰብዐዊ ውበቱን ጠብቆ እንዲኖር ማድረግ የሚያስችል ብርሃን መሆኑን በማመልከት ዛሬ ለማጠናቀቅ እፈልጋለሁ። በእርግጥ የእኛ ስሜታዊ የሆኑ ምዕዳሮች በታማኝነት፣ እርስ በእርስ በመቀባበል እና በምሕረት እንድንኖር የቀረበልን የፍቅር ጥሪ ነው።

ነገር ግን ይህ ስድስተኛው ትዕዛዝ በባለትዳሮች መካከል ስላለው መተማመን የሚያመለክት መሆኑ በፍጹም መረሳት የሌለበት ነገር ሲሆን በዚህም የተነሳ ይህንን ትዕዛዝ በዚሁ ማለትም በባለትዳሮች መካከል ስላለው ግንኙነት የተመለከተ ትርጉም ላይ ብቻ ተመርኩዞ መመልከት ተገቢ ነው። ይህ ታማኝ መሆን እንዳለብን የሚያመለክተው ትዕዛዝ ማንን ነው የሚመለከተው? ራሳችንን መጠየቅ እንችላለን። ባለትዳሮችን ብቻ ነው ወይ የሚመለከተው? በእርግጥ ይህ ትዕዛዝ የሚመለከተው ሁላችንን ነው፣ እግዚኣብሔር ለሁሉም ወንዶች እና ሴቶች የሰጠው አባታዊ የሆነ ቃል ነው።

የሰው ልጆች ብስለት እንክብካቤን ከመፈለግ ወይም ከመቀበል ሌሎችን ወደ መንከባከብ፣ ሕይወትን ከመቀበል ሕይወትን ወደ መስጠት የሚደረግ ወደ ፍቅር የሚመራ የፍቅር ጎዳን ነው። ጎልማሳ ወንድ እና ጎልማሳ ሴት መሆን ማለት በተለያዩ የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገለጠውን በትዳር ውስጥ ይሁን በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ያለውን ትክክለኛ የጋብቻ እና የቤተሰብ ሕይወት መኖር የሚያስችል ዝንባሌ ላይ መድረስ ማለት ነው፣ ይህም በተለያዩ የሕይወት ሁኔታዎች ውስጥ የሚከሰቱትን የሌሎች ሰዎችን ሸክም መሸከም እና አሻሚ ባልሆነ ሁኔታ መውደዳችንን የመቀጠል ችሎታ ማዳበር ማለት ነው። ስለዚህ እውነታን እንዴት እንደሚቀበል እና ከሌሎች ጋር ጥልቅ ግንኙነት እንዴት መመስረት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ያለውን ዓለማቀፋዊ የሆነ አስተሳሰብ ማዳበር ማለት ነው።

እንግዲህ አመንዝራ፣ የማይጨበጥ እና ታማኝ ያልሆነ ሰው ማነው? እሱ ሕይወቱን ለራሱ ብቻ የሚኖር፣ በእራሱ ደህንነት እና እርካታ ላይ ተመሥርቶ ሁኔታዎችን የሚተረጉም ያልበሰለ ሰው ነው። ስለዚህ ትዳር ለመመስረት ሥርግ መደገስ ብቻ በቂ አይደለም! ከ "እኔ" ከሚለው ስሜት ወደ "እኛ" ወደ ሚለው ስሜት መጓዝ አለብን። ራሳችንን ብቻ ማዕከል ማድረግ ስናቆም ሁሉንም ነገር ማለትም ስንሠራ፣ ስንናገር ፣ሌሎች ሰዎችን በመልክም ሁኔታ ስናስተናግድ በአጠቃላይ ሁሉም ነገር ትዳርን ማዕከል ያደረገ ይሆናል ማለት ነው።

በዚህ ረገድ የእያንዳንዱ ክርስቲያን ጥሪ ትዳር ይሆናል ማለት ነው። ክህነት ማለት ክርስቶስን እና የቤተ ክርስቲያንን ማኅበረሰብ በፍቅር ለማገልገል ተጨባጭ በሆነ መልኩ እንክብካቤን ማድረግ የሚያስችል ክርስቶስ የሚሰጠን ሙሉ ጥንካሬ እና ጥበብ የሚሰጠን ጸጋ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የካህናትን ሚና መሻት ብቻ በቂ አይደለም፣ ነገር ግን የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን  ለማገልገል መንፈስ ቅዱስ ልቡን የነካው፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ሚልከው ስፍራ የሚሄድ መሆን ይኖርበታል። ካህን በክህነቱ ሁሉንም የእግዚኣብሔር ልጆች በአባታዊ ፍቅር ይወዳል፣ በርኅራኄ፣ በትዳር ውስጥ እናዳለው ኃይል እና እንደ አንድ አባት ሁሉንም ይወዳል። ራሳቸውን ለመንፍሳዊ ሕይወት ያስገዙ ደናግላን ሕይወት ተመሳሳይ ነው በክርስቶስ አማካይነት በታማኝነት መኖር፣ በትዳር ሕይወት ውስጥ  እንዳለ ዓይነት ግንኙነት በደስታ በመኖር፣ በእናትነት ፍቅር ተሞልቶ መኖር ያስፈልጋል።

ይህንን ነገር በድጋሚ ለመናገር እፈልጋለሁ! የእያንዳንዱ ክርስቲያን ጥሪ በትዳር ውስጥ እንዳለው ዓይነት ጥሪ ነው፣ ምክንያቱም እያንድንዳችንን የሚያስተሳስረን እና እያንዳንዳችን በድጋሚ ሕይወት እንዲኖረን ያደረገው የፍቅር ውጤት በመሆኑ፣ ዛሬ የተነበበልን የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት እንደ ሚያስታውሰን ከክርስቶስ ጋር የሚያስተሳስረን ፍቅር በመሆኑ የተነሳ ነው። ከታማኝነት፣ ልባዊ ከሆነ ፍቅር፣ ከልግስና በመነሳት ጋብቻ እና በእያንዳንዱ ጥሪ በእምነት ስንመለከት ስለ-ስነጾታ ሙሉ የሆነ ትርጉም እናገኛለን።

የሰው ልጅ ተፈጥሮ፣ በማይነጣጠለው በመንፈስ እና በአካል መካከል ባለው አንድነት እና በወንድ እና ሴቷ መካከል ያለው ስፊ ልዩነት ለመውደድ እና ለመወደድ ግብ የተቀመጠለት በጣም ጥሩ እውነታ ነው። የሰው ልጅ አካል ጊዜያዊ ደስታን የምናገኝበት መሳርያ አይደለም፣ ነገር ግን ወደ ፍቅር መንገድ እንድንጓዝ የምንጠራበት ቦታ፣ በእውነተኛ ፍቅር ለምንም ዓይነት ግብዝነት ቦታ የማይሰጥ የፍቅር መገለጫ ቦታ ነው። ወንድ እና ሴት ደግሞ ከዚህ የበለጠ ይገባቸዋል።

 

 

Photogallery

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ
31 October 2018, 12:23