ር.ሊ.ጳ. ፍራንችስኮስ የቅ. ጴጥሮስን መካነ-መቃብር ከጎበኙት ጋር ሆነው መስዋዕተ ቅዳሴን ተካፈሉ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

15ኛው የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2011 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ፣ 20ኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገ ሲሆን፣ ከዚህ ጉባኤ አስቀድሞ ጠዋት በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ፣ የ15ኛ ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የሚያወጣውን የመጨረሻ ሰነድ የሚገመግም ወይም የሚመረምር የጳጳሳት ምክር ቤት ምርጫ መካሄዱ ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ አባላትና በድምሩ 300 የጉባኤው ተካፋዮች ከሮማ ቁምስናዎች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በመሆን ከሮም በ6 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኘውን ወደነበረበት ስፍራ መንፈሳዊ ጉዞን ማድረጋቸ ታውቋል። ይህን መንፈሳዊ ጉዞ ያዘጋጀው በጳጳሳዊ ምክር ቤት አዲስ የወንጌል ስርጭት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የንግደቱ ተካፋዮች በሙሉ ከስፍራው በመነሳት በቫቲካን ከተማ ወደሚገኘው ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከደረሱ በኋላ፣ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ሎሬንሶ ባልዲሰሪ በሚመሩትና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የተገኙበትን መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ታውቋል። በዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ 192 የሲኖዶሱ ብጹዓን አባቶች፣ ከእነዚህም መካከል 101 ብጹዓን ጳጳሳት፣ 9 ብጹዓን ካርዲናሎች፣ የሲኖዶሱን ጉባኤ የተሳተፉት 82 ወጣቶችና የተለዩ ባለሙያዎች እንደዚሁም ከሮም ሀገረ ስብከት የመጡ 100 ምእመናን መካፈላቸውን፣ በጳጳሳዊ ምክር ቤት ውስጥ አዲስ የወንጌል አገልግሎት ፕሬዚደንት ብጹዕ አቡነ ሪኖ ፊዚኬላ ገልጸዋል።

25 October 2018, 18:12